በአዲስ አበባ ከ200 በላይ  ቦታዎች እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ለሊዝ ቻረታ ቀረቡ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የመሬት ሊዝ ዋጋ ንረት እየታየበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ባወጣው 13ኛው  የሊዝጨረታ በአዲስ አበባ፤በቦሌእና  በአቃቂቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 238 ቦታዎችን በሊዝለማስተላለፍ አቅርቧል። መንግሥት የመሬትችርቻሮውስጥከመግባቱጋርተያይዞየአንድካሬሜትርባዶቦታዋጋከ 150 እስከ 305 ሺብር  መሰቀሉ መንግሥትን በከፍተኛ ደረጃ ካስተቸው ወዲህ እንዲህ በብዛት ቦታዎች ለጨረታ ሲያቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በዚህጨረታበቦሌክፍለ ከተማ 116 ቦታዎችለጨረታየቀረቡሲሆንየአንድካሬሜትርመነሻዋጋ 191 ብር፤የሊዝዘመኑ 99 ዓመትነው፡፡በተመሳሳይሁኔታበአቃቂቃሊቲክፍለከተማ 122 ...

Read More »

የዓለም ባንክ የዓለማችን ደሀእና ባለጸጋ ሀገሮችን የሚያሳይ ጥናት ይፋአደረገ ።       

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በዓለም ባንክ አዲስ መረጃ መሰረት ፤ ከአስሩ የዓለማችን የመጨረሻ ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያነች ። በጥናቱ በድህነት ከ 1 እስከ 10 የተመዘገቡት እንደ ቅደምተከተላቸው ማላዊ ፣ ቡሩንዲ ፣ቻድ ፣ ኒጀር ፣ ላይቤሪያ ፣ ማዳካስካር ፣ ኮንጎ ፣ጋምቢያ ፣ኢትዮጵያና ጊኒናቸው። እንደተለመደው ሁሉ  በዘንድሮውም ጥናት በድህነት ተርታ የተመደቡት አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ ፤ ከነኚህ መካከል በመጨረሻዎቹ የድህነት ጠርዝ ላይ ...

Read More »

ጋሞጎፋ ዞን ከምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የተሰጠውን የፖለቲካ ስልጣና ተቃወሙ

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ባለፈው የክረምት ወር ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና ለከምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ ቢቆይም፣ ሰራተኞች ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አልተሰጠንም በሚል ፣ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ አስተያየት አንስጠም በማለታቸው ስብሰባው መተናቀቁን በስብሰባው የተገኙ ተስብሳቢዎች ተናግረዋል። “በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች መካከል ያለው የእርሻ ቦታ  ለኢህአዴግ አባላት ኢንቨስተሮች ለምን ተሰጠ? ኢትዮጵያ እየተበደረቸው ያለው ገንዘብ መጪውን ትውልድ በእዳ ጫና ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ባለፉት 3 ሳምንታት ከ6 ያለነሱ ኢትዮጵያን ተገደሉ

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊመንበር አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለጹት አንዳንድ ነዋሪዎች በውጭ አገራት ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ 6 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና ከ300 ያላነሱት ደግሞ ንብረታቸውን መዘረፋቸውን ተናግረዋል። ድርጊቱን ለማውገዝ የደቡብ አፍሪካ ሰራተኞች ማህበርና የተለያዩ የኮሚኒቲ አባላት ድርጊቱን አውግዘዋል።

Read More »

በምእራብ ሸዋ አንድ አባት የልጃቸውን የሙት አመት በማክበራቸው መታሰራቸው ታወቀ

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ወረዳ በመንዲዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባልቻ፣ በፌደራል ፖሊሶች በግፍ የተገደለባቸውን ደሜ ባልቻ የተባለውን ልጃቸውን የሙት አመት በመዘከራቸው፣ ለምን ይህን አደረጉ በሚል እርሳቸውና ሌሎች 10 ወጣቶች ባለፈው ሰኞ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። አቶ ባልቻ የልጃቸው ገዳዮች እንዲያዙ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም። የልጃቸውን ፎቶ ይዘው ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲያለቅሱ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  እረገብብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከጁማ ጸሎት በሁዋላ በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ በቅርቡ መንግስት በመጅሊስ ውስጥ ያካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ ነጻ መጅሊስ እንዲኖር ጠይቀዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን አሳይተዋል። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳውን የነጻ መጅሊስ ጥያቄ መርታችሁዋል በሚል ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።

Read More »

የኢህአዴግ ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ  ለመከላከያ ቀን እንዲወጣበማስፈራትላይ ናቸው

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ጥር 7 በባህርዳር በሚካሄደው የመከላከያ ቀን ላይ ነዋሪው በስፋት እንዲወጣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ስም እየመዘገቡና በበአሉ ላይ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እያስፈራሩ መሆኑን የከልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች። ሰሞኑን በየመንገዱ ላይ የተለያየ የሙዚቃ ትርኢት በማሳየት ህብረተሰቡን ለመቀስቀስ ቢሞክሩም የህዝቡን ትኩረት ለማግኘት ያልቻሉት የመከላከያ አመራሮች፣  መንገዱን በየ50 ሜትር በታጠቁ ወታደሮችና የፌደራል ፖሊሶች በማስጠበቅ ፣ ህዝቡን ሲያንጋላቱ መሰንበታቸው ...

Read More »

የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት በአባይ ጉዳይ ድንገተኛ  ስብሰባ አካሄዱ።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ተርኪሽ ፕሬስ እንዳለው፤ የሶስቱ ሀገራት ባለስልጣናት  ስብሰባቸውን ያደረጉት ባለፈው ረቡእ  በአዲስ አበባ ውስጥ ነው። የሀገራቱ ባለስልጣናት  ድንገተኛ ስብሰባ ለጋዜጠኞች ዝግ እንደነበርም  የአናሎዱ የዜና አገልግሎት ወኪል ዘግቧል። በስብሰባው   የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሳሜህ ሾርኪ፣ የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር  ሆሳም ሞጋሲ፣ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር  ሞታሳ ሙሳ እና  ከሶስቱም ሀገሮች የተውጣጡ  ኤክስፐርቶች  ተገኝተዋል። ኢትዮጵያና ...

Read More »

በአማራና በትግራይ ክልሎች የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ የተጠራው ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራና  በትግራይ  ድንበር  አካባቢ  የሚኖሩ  ነዋሪዎች  የትግራይ  ክልል  ህገወጥ በሆነ  መልኩ  ባደራጃቸው  ታጣቂ  ሚሊሺያዎች  አማካኝነት ፣ ሰፋፊ  የእርሻ  መሬቶችን  በጉልበት  እየቀማ  ነው  በሚል  ያስነሱትን  ተቃውሞ ለመፍታት  ከሁለቱም  ክልሎች  የተውጣጡ  ባለስልጣኖችና  ከ300  ያላነሱ  የህዝብ  ተወካዮች  ከሳምንታት  በፊት  ተሰብስበው  መግባባት  ባለመድረሳቸው  ለየካቲት  4  በድጋሜ  ቀጠሮ  ከተያዘ  በሁዋላ ፣ ትናንት  ሊካሄድ  የነበረው  ስብሰባ  በአንድ  ቀን  እንዲራዘም  ከተደረገ በሁዋላ ...

Read More »

በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የታሰሩ ከ200 በላይ ሰዎች እስካሁን አልተፈቱም

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በቁጫ  ወረዳ  የተነሳውን  ህዝባዊ  ተቃውሞ ተከትሎ  ከአመት  በላይ  ለሆነ  ጊዜ  በአርባምንጭ  እስር  ቤት  ታስረው  የሚገኙት  ዜጎች ፣ ፍትህ አጥተው  አሁንም ስቃይ ላይ  መሆናቸውን  የአካባቢው ምንጮች  ገልጸዋል። ባለፉት 3 ቀናት ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ 5 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ተቃውሞውን ለማዳፈን ሙከራ ቢያደርጉም፣ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ህዝቡ ጥያቄውን በድጋሜ ...

Read More »