ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን ለኢንቨስትመንት በሚል መሬት ከወሰዱት መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ደጋፊና አባላት መሆናቸው በኢሳት ከተጋለጠ በሁዋላ ህዝቡ በጸረ ሙስና ስብሰባዎች ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ለማስተባበል ሞክረዋል። አቶ አለማየሁ ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በልማቱ ገብቶ እንዲሳተፍ መሬት አዘጋጅተን ሰጥተናል ቢሉም፣ መሬቱ በአንድ አካባቢ ሰዎች ተይዟል ወይስ አልተያዘም ...
Read More »10 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአራት ወራት ጊዜያት ውስጥ ተዘጉ።
ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የውጭ ጉዲፈቻ ድርጅቶችን ጨምሮ የአለምአቀፍና የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በዋንኛነት በፋይናነንስ ችግር ምክንያት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ተዘግተዋል። እነዚህም ድርጅቶች ኤልሮኢ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ፖዘቲቨ ውሜን ማህበር፣ አዶፕትስ ጆንስ ፍረም፣ ሄይነሪች ቦል ፋውንዴሽን፣ ካናዲያን አድቮኬት ፎር ዘአዶፕሽን ኦፍ ችልድረን፣ ሴኬም የልማት ድርጅት፣ ለውጥ በህብረት የተቀናጀ የማህበረሰብ ...
Read More »በኢትዮጵያ በሕግ ሽፋን የዜጎችን መብት መጣስ ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይት ሊግ አስታወቀ
ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ሽብር ሕግን ከለላ በማድረግ መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎችን ማሰር፣ መግደልና ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን መፈጸም ተጠናክሮ መቀጠሉን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል። ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈው ዘግናኝ እልቂት በህወሃት ኢህአዴግ መራሹ ገዥ ቡድን የተቀነባበረ መሆኑን አስታውቋል። ይህን ኢሰብዓዊ እልቂት ተቃውመው ለመብታቸው የታገሉት ከ 22 በላይ የኦሮሞ ብሔር ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስጥ የትራፊክ አደጋ በ 11% መጨመሩ ተነገረ
(ሚያዚያ 24 ፥ 2008) ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች በትራፊክ አደጋ የደረሰ የሞት አደጋ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ11 በመቶ መጨመሩንና ወደ 5ሺ የሚጠጉ ሰዎችም ከባድ የአካል ጉዳት እንደ ደረሰባቸው በባለስልጣኑ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ሃላፊ የሆኑት አቶ ስሜ በላይ አስታውቀዋል። በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪም ከ 569 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረትም በዘጠኝ ወራቶች ውስጥ መውደሙን የተናገሩት ሃላፊው የሃገሪቱ የትራፊክ አደጋ ...
Read More »አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደኢትዮጵያ እየተላለፉ መሰጠታቸው አሳስቦኛል አለ
(ሚያዚያ 24 ፥ 2008) የኬንያ የደህንነት ሃይሎች በሃገሪቱ የፖለቲካ ጥገኝነትን ፈልገው የሚሰሰዱ ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያ መንግስት እያሳለፉ መስጠታቸው አሳስቦት እንደሚገኝ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ይኸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ኬንያ መዲና ናይሮቢ ድረስ በመጓዝ ከኬንያ አጋሮቻቸው ጋር በመተባበር ድርጊቱን እየፈጸሙ እንደሚገኝ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል። ባለፉት አራት ወራቶች ብቻ በኬንያ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ 25 ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ተላልፈው ...
Read More »በኢትዮ-ሱማሌ ድንበር በተከሰተ ግጭት ከ10 ሰዎች በላይ ተገደሉ
(ሚያዚያ 24 ፥ 2008) በቅርቡ በኢትዮጵያና የሶማሊያ የድንበር አካባቢ ከአስር ለሚበልጡ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ሃገራት ተወካዮች በጅጅጋ ከተማ በመምከር ላይ መሆናቸው ተገለጠ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ልዩ ሃይሎች በየጊዜው ከሶማሊያ አርብቶ አደሮች ጋር የሚያደርጉት ግጭት በድንበር ዙሪያ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ስጋት ውስጥ እንዳካተተው የሶማሊያ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። የሶማሌ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት በቅርቡ ለተፈጸመው ከ10 በላይ የሶማሊያውያን ግድያ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስትና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት በደቡብ ሱዳን ስለተገኙት 32 ህጻናት መግለጫም ሆነ ዘገባ አለማውጣታቸው ታወቀ
(ሚያዚያ 24 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስትና የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ከተጠለፉት ህጻናት መካከል 32ቱ ህጻናት ስለመገኘታቸው ጉዳይ አለመዘገባቸው ትዝብት ፈጠረ። ከሁለት ሳምንት በፊት በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን በመጡ በሙርሌና ዲንቃ ጎሳ ታጣቂዎች በግፍ ታፍነው ከተወሰዱት 125 ኢትዮጵያውያን ህጻናት፣ 32ቱ መገኘታቸውን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት መግለጻቸውን “ዘስታር” ቅዳሜ ዕለት መዘገቡ ይታወሳል። ከጋምቤላ ክልል ጋር በሚዋሰነው የደቡብ ሱዳን የቦማ ግዛት ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጀርመን ለእረፍት እና ለህክምና መግባታቸው ታወቀ
ሚያዚያ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት የግል አውሮፕላን ( ቻርተርድ አውሮፕላን ) ተከራይተው ባደን ባደን በተባለ የጀርመን ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው በስፍራው ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል። አቶ ሃይለማርያም በጀርመን የእረፍት ጊዚያቸውን የሚያሳልፉበት ለእረፍት በሚል በገዙት ቤት ሳይሆን እንደማይቀር የገለጹት ምንጮች፣ በቆይታቸውም ለአይናቸው የውበት ቀዶ ጥገና ወይም ኮስሞቲክስ ሰርጀሪ ሳያደርጉ እንደማይቀር ምንጮች ገልጸዋል። 20 ሚሊዮን ህዝብ በተራበበት ...
Read More »ታፍነው ከተወሰዱት ህጻናት መካከል 32ቱ መገኘታቸው ተዘገበ
ሚያዚያ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሙረሌ ጎሳ ሚሊሺያዎች ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓም ከጋምቤላ ተጠልፈው ወደ ደቡብ ሱዳን ከተወሰዱት ከ125 ህጻናት እና ሴቶች መካከል 32 ቱ መገኘታቸውን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ገልጸዋል። አሶሼትድ ፕሬስ የቦማ ግዛት አስተዳዳሪ ኦጋቶ ቻንን በመጥቀስ እንደዘገበው ፣ የአካባቢው የጎሳ አባላት ህጻናቱን የሰበሰቡት በሊኩአንጎሌ ወረዳ በሚገኙ ሶስት መንደሮች ነው። የተገኙት ህጻናት ወደ ዋና ...
Read More »የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኦሮምያ ተቃውሞ ሪፖርትን ለፓርላማ ማቅረብ አልቻለም
ሚያዚያ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሀት አባል እንደሆኑ በሚነገርላቸው ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ግጭት የደረሰውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ቢያጣራም ለፓርላማው ለማቅረብ አለመቻሉ ታውቋል። ኮምሽነር ዶ/ር አዲሱ ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሪፖርቱን ለፖርላማው ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆኑን ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ቢናገሩም፣ ባለፉት ስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥም ማቅረብ አልቻሉም። ምንጮቻችን ...
Read More »