ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ በተከሰተው አሰቃቂ የረሃብ አደጋ የተጠቂዎችን ሕይወት ለመታደግ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለጋሽ ግብረሰናይ ድርጅቶች በጋራ በሆን እርዳታ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀምረዋል። ከ1977 ዓ.ም. ድርቅ በእጥፍ ሁኔታ የላቀ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከትላል ተብሎ የተፈራው አሰቃቂው የዘንድሮ ርሃብ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ይፋ ሳይደረግ ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው የኢትዮጵያ ርሃብ ...
Read More »ስዊድን የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙትን ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ማቀዷ ተሰማ
ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደገለጹት፣ ስዊድን እንደ ኖርዌይ ሁሉ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያለገኙትን ከሰኔ ወር መግቢያ ጀምሮ ለማስወጣት ማቀዷን የኢትዮጵያን የስደተኞች ሊቀመንበር አቶ ኤፍሬም አክሊሉ ተናግረዋል። ከአገር ተገፍቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ወረቀት ሳያገኝ፣ መንግስት ሁሉንም ሰነዶች አዘግጅቶ የሚልክላቸው እኛን ለመሰለል ሲመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በቀላሉ እንደሚያገኙ ተናግረዋል። ይህንን ለመቃወም በነገው እለት ሰላማዊ ሰልፍ ...
Read More »የኢትዮጵያ ታንኮችና ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን መግባታቸው ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) ከ20 የሚበልጡ ታንኮችን የያዙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለማፈላለግ በሚል ወደ ደቡብ ሱዳን መግባታቸውን የደቡብ ሱዳን መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። ማክሰኞ ፖቦር በሚሰኝ ስፍራ የታዩት እነዚሁ የኢትዮፕያ ወታደሮች ከባድ መሳሪያዎችን እንደታጠቁና ከጋምቤላ ክልል በኩልም የጦር ጀቶችን ወደ ስፍራው ሲበሩ መታየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል። የቦማ ግዛት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው በግዛቲቱ በሚገኙ ሶስት ቦታዎች የኢትዮጵያ ...
Read More »በጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ላይ በሼህ አላሙዲን በሚደገፈው ኤሳ ዋን የተከፈተው ክስ ውድቅ ሆነ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በሼህ መሃመር አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው AESA One (ኤሳ ዋን) የተባለው ተቋም በኢሳት ጋዜጠኛ ላይ የከፈተው ክስ ውድቅ ሆነ። በኢሳት የመዝናኛ ክፍል ጋዜጠኛ በሆነው beተወልደ በየነ ላይ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የተመሰረተው ክስ ውድቅ የተደረገው፣ ራሱ ከሳሽ አካል ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉና ክሱን በማቋረጡ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። አመታዊ የስፖርት ውድድሮችን ለማካሄድ ባለፉት 4 አመታት በአንዳንድ ...
Read More »ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ ታውቋል ሲል የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በተፈጸመው ጥቃት ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ መታወቁን የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ። እነዚሁ ህጻናት ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በታጠቁ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸው እንደተረጋገጠ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ የሆኑት አቴኒ ወክ-አቴኒ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ከ100 የሚበልጡት ኢትዮጵያውያን ህጻናቱ ከደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ 300 ኪሎሜትር ...
Read More »ዱባይ አየር ማረፊያ የደረሱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ አገሪቷ እንዳይገቡ የመግቢያ ፈቃድ ተከለከሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በዱባይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በኩል ወደ ዱባይና የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ለመግባት የተጓዙ 30 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ ኢትዮጵያ ሊባረሩ እንደሆነ ተነገረ። ገልፍ ኒውስ የተባለ ጋዜጣ ትናንት ማክሰኞ እንደዘገበው ፍላይ ዱባይ በተባለ በዱባይ አየር መንገድ በአንድ የጉዞ መስመር ቲኬት ቆርጠው የተጓዙት ሴቶች ወደ አዲስ አበባ ተገደው እንደሚመለሱ ተነግሯል። የፍላይ ዱባይ ቃል አቀባይም የኢትዮጵያውያኑ ሴቶች መባረር ...
Read More »አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኛ ክስ ተመሰረተበት
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ የጻፋቸው ጹሁፎችና አስተያየቶች በማስረጃነት ቀርበውበት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። ተከሳሹ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም አመጽና ብጥብጥን የሚያነሳሱ ጽሁፎች አሰራጭቷል እንዲሁም መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎች ጽፏል ተብሎ በከሳሽ አቃቢ ህግ ራሱ እንደተመሰረተበት ታውቋል።
Read More »እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ 10 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትንና 141 ሌሎች ሰዎችን ለምስክርነት እንዲቀርቡላቸው ጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) ከወራት በፊት የግንቦት ሰባት ሃይልን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ አራት ተከሳሾች 10 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ 141 ሰዎችን በምስክርነት እንደቀረቧቸው ጠየቁ። አቶ አባይ ፀሃኤ፣ አቶ በረከት ስምዖን፣ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ተፈራ ዋልዋ ተከሳሾቹ ለምስክርነት እንዲያቀርቧቸው የጠየቋቸው ምስክሮች መሆናቸው ታውቋል። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወ/ት ...
Read More »በርካታ ኢትዮጵያውያንን በህገወጥ መንገድ በማዘዋወር የተጠረጠረው ሃዱሽ ኪዳኑ በቁጥጥር ስር ዋለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በርካታ ኢትዮጵያውያን እና የሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዜጎችን በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ወንጀል የተጠረጠረና ለዘጠኝ አመታት ያህል ሲፈለግ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ በስዊዘርላንድ በቁጥጥር ስር ዋለ። ሃዱሽ ኪዳኑ የተባለው ይኸው የ58 አመት ኢትዮጵያዊ በማልታ መንግስት የሚፈለግ በመሆኑ የስዊዘርላንድ መንግስት ተጠርጣሪውን ለማልታ መንግስት አሳልፎ መስጠቱም ታውቋል። ሃዱሽ በማልታ በነበረበት ወቅት በህገ-ወጥ የሰዎች ማዘዋወር ክስ ተመስርቶበት እንደነበርና የዋስትና መብት ...
Read More »የኢትዮጵያ ጦር ለመወረር ተዘጋጅቷል በሚል እሳቤ፣ ባላንጣ የነበሩ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት ለመተባበር መስማማታቸው ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) ከሁለት ሳምንት በፊት በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎች የተገደሉትን 208 ዜጎችን ለመበቀልና፣ የተጠለፉ ህጻናቱን ለማስለቀቅ የኢትዮጵያ መንግስት አጸፋዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚለውን መላ ምት ተከትሎ፣ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት በጥቃቱ እርስ በዕርስ መወነጃጀላቸውን ትተው አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ሬዲዮ ታማዙጂ የተባለ የሱዳን ጣቢያ ገለጸ። የደቡብ ሱዳን ምክትል መከላከያ ሚንስትር የሆኑት ዲቪድ ያው ያዉ ...
Read More »