ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት የፖለትካ ነጻነት ችግር ውስጥ እንደወደቀ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2008) አምነስቲ ኢንተርናሽናል የፖለቲካ ነጻነት ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ። መንገስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በዚሁ የአፍሪካ ክፍል ከፍተኛ ጫና እንደሚደረግባቸው የገለጸው የአምነስቲ ኢንተናሽናል ዘገባ፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያንና ሌሎች መንግስታትን የሚነቅፉ ድምጾች በፍርሃት ዝም እንዲሉ ወይም አገር ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል ብሏል። እንደ ኡጋንዳይ፣ ቡሩንዲና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመሳሰሉት አገራት መሪዎች የስልጣን ዘመናቸውን የሚገድባቸውን ህገመንግስት ...

Read More »

በኮንሶ ወረዳ ከሚገኝ አንድ እስር ቤት ወደ 60 የሚጠጉ እስረኞች ማምለጣቸው ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2008) በደቡብ ክልል ኮኖሶ ወረዳ ከሚገኝ አንድ እስር ቤት ወደ 60 የሚጠጉ እስረኞች ከእስር ቤት ሰብረው ማምለጣቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚሁ እማኞች እስረኞቹ ሰገን ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ በሳምንቱ መገባደጃ አርብ በሃይል ማምለጣቸውን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በኮንሶ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው የሚታወስ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የመንግስት ባለስልጣናትን መኖሪያዎች የሚያሳዩ ተጨማሪ ቪዲዮች ቀረቡ ( ሪፖርታዥ )

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ እና በመላው አገሪቱ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የኢህአዴግ ሹመኞች በራሳቸውና በዘመዶቻቸው ስም ያስገነቡዋቸው ህንጻዎች የህዝብ መነጋገሪያ አጀንዳ ከሆኑ ውለው አድረዋል። በተቃራኒው ጥረው ግረው የሰሩዋቸው ቤቶች ህገወጥ ተብለው ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ወይም ተገቢው መኖሪያ ቤት ሳይሰጣቸው በጎዳና ላይ ላስቲክ ዘርግተው የሚኖሩ ዜጎች እየተበራከቱ ነው። ሰሞኑን በቦሌ ክፍለከተማ ከታየው ...

Read More »

ለባለሃብቶች በተሰጡ ሱቆች ዙሪያ በተደጋጋሚ የተነሱት ቅሬታወች ምላሽ አላገኙም፡፡

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለወጣቶችና ስራ አጥ ወገኖች የሚዘጋጁ የመስሪያ ሱቅ ኮንቴይነሮች በባለ ሃብት እጅ በመገኘታቸው ዙሪያ የተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ አለማገኘታቸውን በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለኢሳት አስታወቁ፡፡ ንግድ ፍቃድ የሌላቸው ፣በጥቃቅንና ኢንተርፕራይዝ ያልታቀፉ ነዋሪዎች የመስሪያ ሱቅ እየተሰጣቸው የሚሰሩበት ሁኔታ በግልጽ እየታየ የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ርምጃ ከመውሰድ መቆጠባቸው አሳዛኝ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ያለው የፓለቲካ ምኅዳር መጥበቡንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ መባባሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ባደረገው ጥናታዊ ሪፓርት፣ በኢትዮጵ ውስጥ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ እየከፋ መምጣቱን ጠቁሟል። ድርጅቱ በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ የበላይነት መንገሱንና የፓለቲካ ምኅዳሩ መፈናፈኛ በሌለው ሁኔታ በአንባገነኑ ኢሕአዴግ ብቸኛ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። ባለፈው ዓመት ተካሂዶ በነበረው ነጻና ...

Read More »

በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸው ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋል ሰዎች ተቃውሞ አሰሙ

ኢሳት (ግንቦት 12 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚኖሩ ወደ 3ሺ አካባቢ ነዋሪዎች አካባቢው በአረንጓዴ ልማት የሚሆን ነው ተብሎ ሊነሱ መሆናቸውን ተቃወሙ። ከከተማው አስተዳደር ተወካዮች ጋር በቅርቡ ምክክርን ያደረጉት እነዚሁ ነዋሪዎች፣ መንግስት የቤት ቁልፍን ካስረከባቸው የመኖሪያ ቀያቸውን እንደማይለቁም ለባለስልጣናቱ አስረድተዋል። በዚሁ ውይይት ላይ የተሳተፉና የተቀረጸ መረጃ ለኢሳት ያደረሱ ነዋሪዎች  በገዢው መንግስት ኢህአዴግና በከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ...

Read More »

ህገወጥ በተባሉ የመኖሪያ ቤቶች መፍረስ ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ግንቦት 12 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አየር ማረፊያ ዙሪያ ህገወጥ በተባሉ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ የሚወስደው እርምጃ አርብ መቀጠሉንና በርካታ ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እማኞች አስታወቁ። ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው መንደር ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች የቤት ለቤት ፍተሻን በማካሄድ ሁከትን ፈጥረዋል የተባሉ ሰዎችን አሳልፈው እንዲሰጡ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆናቸውም ...

Read More »

ሰሞኑን በተከሰተው ጎርፍ ከ20ሺ በላይ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸው ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 12 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው ከፍተኛ ጎርፍ ከ20 ሺ በላይ ሰዎች ቤት አልባ ማድረጉ ተገለጸ። በእነዚሁ አካባቢዎች ከተከሰተው ከባድ ጎርፍ በኋላም ብዛት ያላቸው ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊዎች አክለው ገልጸዋል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እንደሚናገሩት ወደፊት በተከታታይ የሚጥለው ዝናብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅላቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ከረጅም ድርቅ በኋላ ...

Read More »

የግብፅ መንገደኞች አውሮፕላን ስብርባሪ በሜዲትራኒያን ባህር ተገኘ

ኢሳት ( ግንቦት 12 ፥ 2008) ሃሙስ ከፈረንሳይ ወደግብፅ በመብረር ላይ እንዳለ በሜዲተራኒያን ባህር ላይ የተከሰከሰው አውሮፕላን ስባሪ ክፍልና የመንገደኞች ንብረት በውሃ ላይ መገኘቱን የግብፅ ባለስልጣናት ገለጹ። ከተለያዩ ሃገራት በተውጣቱ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየተካሄደ ባለው ፍለጋ አንድ የመንገደኞች ሻንጣ፣ ሁለት ወንበሮችና የአውሮፕላኑ ስብርባሪ አካላት መገኘታቸው የግብፅ መከላከላይ ሰራዊት ይፋ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል። የአሮፕላኑ እና የመንገደኞች ንብረቱ ከግብጻዊ የአሌክሳንድሪያ ከተማ በ290 ...

Read More »

በቦሌ ቤታቸው የፈረሰባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ሪቼ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ

ግንቦት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳ 12 የተጀመረውን የቤት ማፍረስ ተከትሎ የታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ቦሌ ክፍለከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወላጆቻቸውን ለመጠየቅ ወደ እስር ቤቱ የሄዱት ህጻናት፣ መጠየቅ አትችሉም በመባላቸው ሲያለቅሱ መመልከታቸውን የአይን እማኞች አክለው ገልጸዋል። የመንግስት ታጣቂዎች በህዝቡ ላይ ባደረሱት ጥቃት ከ8 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል። ቤት የማፍረሱ ...

Read More »