ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ወር ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለማስለቀቅ በድጋሚ ወደ ደቡብ ሱዳን መግባታቸው ተገለጸ። ወታደሮች በሃገሪቱ የቦማ ግዛት ቢደርሱም የግዛቲቱ ባለስልጣናት ወታደሮቹ የቦማ ግዛትን አልፈው ለመሄድ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ፈቃድ ሳይሰጣቸው መቀረቱን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ የግዛቲቱን ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። የደቡብ ሱዳን መንግስት ተወካዮች ከሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጋር ሲያካሄዱት በነበረው ድርድር ታፈነው ...
Read More »ኢህአዴግ የመኖሪያ ሰፈሮችን ማፍረሱን ቀጥሏል
ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2008) ኢህአዲግ ባለፈው አመት የምርጫ ወቅት ገብቶት የነበረን ቃል በማፍረስ ህጋዊ ይደረጋሉ ያላቸውን የመኖሪያ ሰፈሮችን በማፍረስ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጡ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ እየፈረሱ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ህገወጥ ሆነው የተገኙ ናቸው በማለት እርምጃው ቀጣይ እንደሚሆን አስታውቋል። ባልፈው ሳምንት የመኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸውና በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረገኑ በሚባል አካባቢ የመኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ግንባታቸው ...
Read More »ግንቦት 20ን ለማክበር 2 ቢሊዮን ብር ተመደበ
ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2008) በሳምንቱ መጨረሻ የሚከበረውን የኢህአዴግ 25ኛ ዓመት በዓል ለማክበር 2 ቢሊዮን ብር መመደቡ ታወቀ። ለበዓሉ አከባበር በቀበሌ መዋቅር ለወጣቶችና ለሴቶች ማህበራት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቧል። በሃገር ቤት ለሚታተሙ ጋዜጦች እንዲሁም ለኤፍ ኤሞችም ገንዘብ የተደለደለ ሲሆን፣ እነዚህ መገናኛ ብዙሃን ግንቦት 20ን በተመለከተ ፕሮግራሞችን እንዲሰሩ እንዲሁም የማስታወቂያ አገልግሎት እንዲሰጡ ክፍያ እንደተፈጸመላቸው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የኢህአዴግ 25ኛ ዓመት በማስመልከት በትዕይንቱ ...
Read More »የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ
ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2008) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ ፥ በምትካቸው አዲስ ሰው ተሹሟል። ባለቤታቸው በተመሳሳይ ከስራቸው ተነስተዋል። የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት 2ኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ መስሪያ ቤት ከሚሰሩት ባለቤታቸው ጋር ከስራና ከስልጣን ከመነሳታቸው በተጨማሪ፣ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል ውስጥ መሆናቸውንም መረዳት ...
Read More »በተለምዶ አሜሪካ ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለዘመናት የኖሩ ዜጎች “መጠለያ አልባ” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገሩ
ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቤት የማፍረስ እርምጃው መቀጠሉትን ተከትሎ፣ ከትናንት ጀምሮ መርካቶ የሚገኘውና በተለምዶ አሜሪካ ግቢ በሚባለው አካባቢ እና አጎራባች ቀበሌዎች የሚገኙ ቤቶች እየፈረሱ ነው። ይህን ተከትሎ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የኖሩ ዜጎች ተለዋጭ መጠለያ ባለማግኘታቸው ማደሪያቸውን በቤተክርስቲያን ፣ በመስጊድ ወይም በጎዳናዎች ላይ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወኪላችን በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው ...
Read More »ኢህአዴግ የአገሪቱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ግንቦት20ን እንዲያከብሩ እያስገደደ ነው
ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ አመት የመንግስት ስልጣን የተቆጣጠረበትን በአሉን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለማክበር ያቀደው ኢህአዴግ፣ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ስራቸውን እየተው በአሉን እንዲያደምቁ አዟል። ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን፣ ትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ሲቪል አቪየሽን፣ ስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት፣ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር፣ ቤተ መንግስትን አስተዳዳር፣ ካርታ ስራዎች ድርጅትና ሌሎችም ...
Read More »በአዲስ አበባ 44 የግል ኮሌጆች የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአ/አ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በዘርፉ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ፈቃድ የወሰዱና በራሳቸው ምክንያት ያቋረጡ 44 የግል ኮሌጆች የመጨረሻ የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው በዛሬው እለት በመንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ባወጣው ማስታወቂያ የተዘጉትን 44 ያህል ኮሌጆች ዘርዝሮአል። እነዚህ ኮሌጆች ስልጠናቸውን አቋርጠው ተቋሞቻቸውን ሲዘጉ በገቡት ውልና ግዴታ መሰረት አስፈላጊ መረጃዎችንና ...
Read More »1.5 ሚሊዮን ዜጎች በጎርፍ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የብሄራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2008) በተያዘው የክረምት ወቅት 1.5 ሚሊዮን ሰዎች በጎርፍ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችል የብሄራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን አሳሰበ። የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው በጎርፍ አደጋ የሚፈናቀሉ ሰዎች በሃገሪቱ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ላይ ተጨማሪ ጫናን እየፈጠሩ እንደሆነ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከአንድ ወር በኋላ የሚገባው የዘንድሮው የክረምት ወቅት ከመጠን በላይ ለሆነ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የአደጋ ...
Read More »በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እጅግ እየጠበበ መምጣቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2015) በኢትዮጵያ መሰረታዊ የንግግርና የመሰብሰብ ነጻነት ጨምሮ የፖለቲካ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጠበበ መሄዱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።መቀመጫውን በብሪታኒያ ለንደን ያደረገው ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከዋሽንግተን ቢሮ እሁድ ግንቦት 14 /2008 ዓ.ም ሜይ 22 /2016 ኢትዮጵያን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ የኢህአዴግ መንግስት የንግግርና የመሰብሰብ ነጻነትን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የከለከለበት ደረጃ ላይ መድረሱን አትቷል። “ወደተሳሳተ መንገድ ...
Read More »በወልቃይት ቃብትያ አካባቢ አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ
ኢሳት (ግንቦት 15 ፥ 2008) ሰሞኑን በትግራይ ክልል ስር በሚገኘው የቃብትያ አካባቢ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች በክልሉ ላለመተዳደር የወሰዱትን የቃለ መሃላ ውሳኔ ተከትሎ በአካባቢው አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ። ትላንት እሁድ የወልቃይት ተወላጆች በውሳኔያቸው ዙሪያ ለመምከር በተሰባሰቡ ጊዘ የአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች የማስፈራሪያ የተኩስ እርምጃ መውሰዳቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የጸጥታ ሃይሎች በነዋሪዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎም በአካባቢው ትምህርትና የሌሎች የመሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጡን ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ...
Read More »