በቢልዮን የሚገመት ብር የወጣባቸው የውሃ ተቋማት ደረቁ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት 1 ቢሊዮን 900 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረጋባቸው 102 ጥልቅ የመጠጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮዎች ግንባታቸው ተከናውኖ ውሃ መሰጠት በጀመሩ በወራት እና በሳምንታት ውስጥ መድረቃቸውን ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ በክልሉ የነበረው የመጠጥ ውሃ ሽፋን በገጠር ከ72 በመቶ በታች ሆኗል ብለዋል።

Read More »

የታገቱትን ሕጻናት ለማስለቀቅ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ተመድ አሳሰበ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሁለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኤክስፐርቶች ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ በሙርሌ ጎሳ አባላት ታግተው የተወሰዱት ሕጻናት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጊዜ ሳይወስዱ የልጆቹን መመለስ ማፋጠን እንዳለባቸው አሳሰቡ። በጋምቤላዋ ጂካውና ላሬ ወረዳዎች13 የኑዌር መንደሮች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ከ208 በላይ የሚሆኑ ሴቶችና ሕጻናት ...

Read More »

በምዕራብ ሸዋ ጊንጪ ተቃውሞ ተቀሰቀሶ የትራንስፖርትና የትምህርት አገልግሎት ተቋረጠ

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ በምትገኘው የጊንጪ ከተማ ዳግም ተቃውሞ መቀስቀሱንና የትራንስፖርትና የትምህርት አገልግሎት ከማክሰኞ ጀምሮ መቋረጡን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። ተቃውሞ ጨርሶ አልተቋረጠም ሲሉ የገለፁት ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች አሁንም ድረስ በከተማዋ ዙሪያ በመሰማራት በህብረተሰቡ ላይ ፍርሃትን አሳድረው እንደሚገኙ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው መናገር ያልፈለጉ እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በነዋሪዎች ሲነሱ የነበሩ የተለያዩ የአስተዳደርና የመብት ...

Read More »

በቂሊንጥ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪዎችና ሌሎች ተከሳሾች ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታ አቀረቡ

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2008) በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንቶ ወህኒ ቤት የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪዎችና ሌሎች ተከሳሾች ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታ አቀረቡ። “ለሃገራችንንና ለህዝባችን የሚበጀውን በማሳሰባችን በአሸባሪነት መከሰሳችን ሳያንስ የፍርድ ሂደቱ ተቋርጦ በወህኔ ቤት ውስጥ ያለ አንዳች ምክንያት መቀጠላችን አግባብ አይደለም” ሲሉም ለፍትህ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ አመልክተዋል።  የበረራ ባለሙያዎች እነ የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና አበባ ተመስገን በሚሉ የክስ ፋይሉች በአሸባሪነት ...

Read More »

በቦሌ ወረገኑ የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ እርምጃ ቀጥሏል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተጀመረው ህገወጥ የተባሉ መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ እርምጃ መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸው እንዳይፈርስባቸው ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ ወደ 200 አካባቢ ለእስር ተዳርገው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል። ህገወጥ ናቸው ተብለው በመፍረስ ላይ ባሉት ስፍራዎች ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር በ450 ሄክታር መሬት ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የራሱን ማስተር ፕላን ሊያጸድቅ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሶስት አመት ያለማስተር ፕላን የቆየበትን ችግር እልባት ለመስጠት የኦሮሚያ ክልል ያልተካተተበትን የራሱን ማስተር ፕላን ሊያፀድቅ መሆኑ ተገለጸ። ለ10 አመት ሲያገለግል የነበረው የከተማዋ ማስተር ፕላን ከሶስት አመት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ቢያበቃም ከኦሮሚያ ክልል የመሬት መስፋፋት ጋር በተገናኘ ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን አስተዳደሩ አስታውቋል። በቅርቡ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መስፋፋት ጋር የተፈጠረውን ...

Read More »

ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ በህወሃት ነባር ታጋዮችና በሰራዊት አዛዦች መካከል ፍጥጫ መቀጠሉ ተሰማ

ኢሳት (ግንቦት 17 ፥ 2008) በመሰረታዊ ብረታብረት ኮርፖሬሽንና በስኳር ኮርፖሬሽን መካከል ከተፈጠረው ውዝግብ ጋር በተያያዘ በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነባር ታጋዮች በሰራዊት አዛዦች መካከል ፍጥጫ መቀጠሉ ተሰማ። የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች ሪፖርቱን በፓርላማ እንዲያቀርቡ ድጋፍ ያደረጉትና ማበረታቻ የሰጡት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ መሆናቸውም ተመልክቷል። ከ6 ዓመታት በፊት ከመንግስት በተመደበለት በ10 ቢሊዮን ብር ካፒታል ስራውን የጀመረው የመሰረታዊ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 77 ቢሊዮን ብር ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት ወታደራዊ ሃይሉን ለማጠናከር የጦር መሳሪያዎችን በብዛት እየሸመተ ነው

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰነዶች እንደሚያመለክቱት ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ የኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ የሆነ ወጪ በማውጣት የጦር መሳሪያዎችን እየገዛ ሲሆን፣ የጦር መሳሪያ ባለሙያዎችንም ወደ ቻይናና ሌሎች የምስራቅ አውሮፓ አገራት በመላክ እያሰለጠ ነው። ሰነዶቹ እንደሚያስረዱት በሁለት አመታት ውስጥ መንግስት ለታንክ መግዢያ ብቻ ከ684ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣ ለመድፎች 896 ሚሊዮን ብር፣ ለተሽከርካሪዎች ፣ ...

Read More »

በምስራቅ ሃረርጌ “ ዘረኝነት በቃ!” ያሉ ቄሶች ተቀጡ

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ሀረርጌ ሃገረ ስብከት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የሚያገለግሉ ቄሶች ፣ “ዘረኝነት ይቁም፣ አድልዎ ይወገድ፣ የሁሉም ህዝብ መብት ይከበር!” የሚሉ መፈክሮችን በማንገብ የዲሞክራሲ የለውጥ እንቅስቃሴ ጀምራችሁዋል ተብሎው ደሞዛቸው እንዲቀነስ፣ ከደረጃም ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል። እስካሁን በ16 ቀሳውስት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ እርምጃው በሌሎችም ላይ ሊቀጥል ይችላል ተብሎአል። ...

Read More »

ዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የእንግሊዝ መንግስት ለድርቅ ተጎጂዎች እርዳታ አበረከቱ

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በድርቁ የተጎዱትን ሰዎች ሕይወት ለመታደግ ዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር 35 ሽህ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የምግብ፣ የውሃ፣ የጤና አገልግሎት፣ የቤት እንስሳት እንክብካቤ፣ ለሕጻናት ምገባ መርሃ ግብር የሚውል 2.2 ሚሊዮን የስዊዘርላንድ ፍራክ መድቧል። ለቀጣይ አምስት ዓመታት በሚዘልቀው የቤተሰብ ምገባ ፕሮግራም ማእቀፍ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ 12.5 ኪሎ ግራም በቆሎ፣ ...

Read More »