ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ ናቸው

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገር አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላዊ መግቢያና መውጫ ድንበሮች አካባቢ የተያዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ተዘገበ። ማላዊ በሚገኘው ዲዛካ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UNHCR) ስር ባሉት የመጠለያ ጣቢያዎች ካሉ 24 ሽህ ስደተኞች ሲኖሩ፣ ከእነዚህ መካከል በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ወረገኑ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ቀጥሎ በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ጠፋ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ወረገኑ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ህገወጥ ናቸው የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረሱ እርምጃ ሃሙስም ለሁለተኛ ሳምንት ጊዜ ቀጥሎ ተጨማሪ አንድ ሰው መሞቱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መናገር ያልፈለጉት ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች አሁንም ድረስ በአካባቢው በመስፈር በነዋሪዎች ላይ እርምጃን እየወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረገኑ ተብሎ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ስላለው የዴሞክራሲ ችግር ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እየተወያየሁ ነው አለ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲ ችግሮች ላይ ዝምታን መርጧል የሚል ትችል እየቀረበበት ያለው የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ ያለውን ችግር በተለያዩ መድረኮችና ከባለስልጣናት ጭምር በመግለጽ ላይ መሆኑን አስታወቀ። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉና ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩት የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት “ትክክለኛ የሆነ አመራር በአፈና ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም” ሲሉ ለጠቅላይ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል አምባሳደር ከገንዘብ ምዝበራ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) አዲስ አበባ በሚገኘው የማላዊ ኢምባሲ ውስጥ ተፈጽሟል ከተባለ ከፍተኛ ገንዘብ ምዝበራ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ የሃገሪቱ ምክትል አምባሳደር በማላዊ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። የማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሯ ዶረን ካፓንጋ በኢትዮጵያ ተፈጽሟል ስለተባለው የገንዘብ ምዝበራ ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ረቡዕ ይፋ ማድረጉ ታውቋል። በኢምባሲው የገባበት አልታወቀም ከተባለ ከሶስት ሚሊዮን ዶላር ጉዳይ ጋር በተገናኘ ምክትል አምባሳደሯና የኤምባሲው ዋና ...

Read More »

በሙርሌ ታጣቂዎች ታግተው በድርድር የተለቀቁ ህጻናት ለስነልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) ከጋምቤላ ክልል በታጠቁ የሙርሌ ጎሳ አባላት ተጠልፈው ወደደቡብ ሱዳን ከተወሰዱት በኋላ በድርድር የተለቀቁት ህጻናት፣ ወላጆቻቸውን በማጣታቸውና በጠለፋ ወቅት በማያውቋቸው ሰዎች እጅ በመውደቃቸው በስነልቦናዊ ቀውስ እንደተዳረጉ ተገለጸ። ከጥቃቱ ያመለጡና ልጆቻቸው ተጠልፈው ያልተመለሱላቸው ወላጆችም እንዲሁ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል። ጃኒ የተባለ አንድ ህጻን ከተጠለፉበት ቀን ጀምሮ በአንድ ጎጆ ውስጥ ተቆፎበት ወተት ብቻ እየተሰጠው በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ ...

Read More »

መንግስት ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአትላስ ኩባንያ ከተወሰደ በኋላ በኩባንያው ስር የነበሩ የባለሃብቶች ድርሻ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከቁጠባ ሂሳቡ እንደተወሰደበት ያስታወቀው የብሪታኒያው ኩባንያ ድርጊቱን ተከትሎ በኩባንያው ስር ለኢንቨስትመንት ፍላጎት የነበራቸው ባለሃብቶች ድርሻ ማሽቆልቆሉ ገለጸ። ይኸው በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በሽርክና በብርጭቆ ማምረት ላይ ተሰማርቶ የነበረው ኩባንያ በስሩ ኢንቨስት በማድረግ ፍላጎት የነበራቸው አካላት ድርሻ ከ30 በመቶ መቀነሱን ይፋ አድርጓል። አትላስ አፍሪካ የተሰኘው ...

Read More »

ኢህአዴግ “ህዝቡን በመልካም አስተዳደር ማወያየታችን አመጽ እንዳይፈጠር አድርጓል” አለ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የስልጣን ዘመኑን በማክበር ላይ ያለው ኢህአዴግ፣ ከፍተኛ አመራሮቹን ይዞ ግምገማ በማድረግ ላይ ነው። በግምገማው ኢህአዴግ ባለፉት 25 አመታት የተጓዘባቸው መንገዶች እና ያጋጠሙት ችግሮች በነባር አመራሮቹ ውይይት ተደርጎባቸዋል። ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ የኢህአዴግን የርእዮት አለም አቅጣጫ በማብራራት ግንባር ቀደም ሆነው የወጡት በሁዋላም ከጤና ጋር በተያያዘ የመድረክ እንቅስቃሴያቸውን የቀነሱት ...

Read More »

ኢኮኖሚው ሰራዊቱን ሊሸከመው አልቻለም ተባለ

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊሸከመው አለመቻሉ የኢህአዴግ የ25 አመታት የመከላከያ አስተዳደር በሚገመገምበት ወቅት መነሳቱ ታውቛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሰራዊቱን ፍላጎት ማሙዋላት አለመቻሉ በሰራዊቱ ውስጥ እየተባባሰ ለመጣው ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በስብስቡ እና አመራሩ በነባር ታጋዮች የተያዘ እና በጦር ካምፕ ብቻ ተነጥሎ የሚኖር ሰራዊት በመሆኑ ህዝባዊነት አልተላበሰም ...

Read More »

የኢህአዴግ አባላት ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እየጎረፉ ነው

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣበት የኢህአዴግ በአል አከባበርን በተመለከተ ውስጥ ሆኖ ዝግጀቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ዘጋቢያችን ትዝብቱን ልኳል። “ ትላንት ብዙ በአ.አ ከተማ የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩና የፌደራል ሚኒስቴር መ/ቤቶች በተሰጣቸው ትዕዛዝና በወጣላቸው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት የኮንትራት ትራንስፖርት እየተጠቀሙ የመንግስት ሥራ ዘግተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክ/ከተማና ወረዳ መ/ቤቶች እንዲሁም በህዝብ ...

Read More »

የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደገና የተጀመረውን የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ተከትሎ አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ትምህርት እንዲጀምሩ የቀረበላቸውን ማግባቢያ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ተማሪዎቹ “ጥያቄዎቻችን ይመለሱ፣ የታሰሩ ጓደኞቻችን ይፈቱ” የሚሉ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆኑ፣ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ተማሪዎችን ለማግባባት ጥረት ቢያድርጉም ተማሪዎች በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡

Read More »