እነ አቶ በቀለ ገርባ በጨልማ ቤት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የኦፌኮ አመራሮች አሁንም በጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ጠበቃቸው አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለኢሳት ገለጹ። በተመሳሳይም ጥቁር ልብስ እንዳይለብሱ የተከለከሉ ከአምቦ የመጡ 16 እስረኞች ጸጉራቸውን ተላጭተው ፍ/ቤት መቅረባቸውም ተመልክቷል። ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓም ልብሳቸውን በመነጠቃቸው በሌሊት ልብስ ቁምጣና ከናቴራ እንዲሁም በባዶ እግር ፍ/ቤት የቀረቡት እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ በጨለማ ቤት ውስጥ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ስደተኞች ለማስቆም 70 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ መደበ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት የስደተኞችን ፍሰት ለመቅረፍ የሚያስችል የ70 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ እቅድ መንደፉንና በቅርቡ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ሃላፊዎች፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከዘጠኝ የመካከለኛና የምስራቅና አፍሪካ አገራት ጋር ትብብር በመፍጠር የስደተኞችን ፍሰት ለመቀነስ እንደሚሰሩ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ይህንን እቅድ ለማስፈጸም እስከ 70 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ የሚችል የፕሮጄክት በጀት እንደተመደበ የአውሮፓ የስደተኞች ኮሚሽነር ዲሚጥሪስ ...

Read More »

ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ፍልሰት ጨምሯል

ግንቦት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወሃት/ ኢህአዴግ የ25ኛ አመት በአሉን በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በማውጣት ድል ባለ ድግስ ባከበረ ማግስት ዜጎች ቀያቸውን እየጣሉ ወደ አዲስ አበባ በመሰደድ ላይ ናቸው። አዲስ አበባ መድረስ ያልቻሉት ደግሞ በዋና ዋና የክልል ከተሞች በብዛት እየተሰደዱና በልመና ህልውናቸውን ለማቆየት እየጣሩ ነው። ዝርዝር አለን። ህወሃት መራሹ አስተዳደር በኢትዮጵያ ታምራዊ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማስገንዘቡን ይናገራል። አለማቀፍ ...

Read More »

በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ተከሳሾች መከላከል አትችሉም ተባሉ

ግንቦት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ከአዲስ አበባ ተነስተው ሲጓዙ ማይካድራ የሚባል የድንበር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሶ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የመሰረተባቸው  ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ  ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል  የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አንጋፋ ሯጮች በሪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶችን ምርጫ አወገዙ

ግንቦት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በላቲን አሜሪካዋ በብራዚል በሚካሄደው 31ኛው የሪዮ ኦሎምፒክ ላይ አገራቸውን ወክለው የሚቀርቡትን አትሌቶች ምርጫ ላይ አግባብ ያልሆነ ስህተት መፈፀሙን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር አንጋፋ ሯጮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም ባደረጉት ስብሰባ አቋማቸውን አሳወቁ። አንጋፋዎቹ ሯጮች ሻለቃ ኃ/ገብረስላሴና አሰፋ መዝገቡ ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት በአትሌቲክስ ማኅበሩ ምርጫና በሪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልፀዋል።  በኦሎምፒክ ...

Read More »

የኢሳት 6ኛ አመት በዋሽግተን ዲሲና በዳላስ ቴክሳስ በድምቀት ተከበረ

ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥኝና ሬዲዮ (ኢሳት) 6ኛ ዓመት በዋሽንግተን ዲሲና በዳላስ ቴክሳስ በድምቀት ተከበረ። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ በተከበረው የኢሳት 6ኛ አመት ዝግጅት የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለነበሩት አቶ ነዓምን ዘለቀና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ለኢሳት ላበረከቱት ልዩ አስተዋጽዖ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዋሽንግተን ዲሲና አጎራባች ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በታደሙበትና ግንቦት 28, 2008 በተከበረው የኢሳት 6ኛ አመት ክብረ በዓል የኢሳት ...

Read More »

ደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ በመንግስት ታጣቂዎችና በአካባቢው ህዝብ መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2008) እሁድ በደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ ጉና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመንግስት ታጣቂዎችና በአካባቢው ህዝብ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ሰኞ ድረስ እልባት አለማግኘቱንና ድርጊቱ በአካባቢው ውጥረት አንግሶ መገኘቱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ከግጦሽ መሬት ጋር በተገናኘ ተቀስቅሷል የተባለው ይኸው ግጭት መልኩን በመቀየር በነዋሪው ዘንድ ተቃውሞ ማስከተሉን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። ልዩ ...

Read More »

በአባይ ግድብ ግንባታ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ካሳ ስላልተከፈላቸው ተመልሰው እየሰፈሩ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 29 ፥ 2008) በአባይ ግድብ ግንባታ ተብሎ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ነዋሪዎች የካሳ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ተመልሰው እየሰፈሩ መሆኑ ተገለጸ። የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከቀያቸው ለተነሱት ነዋሪዎች ሊከፈላቸው ቃል የተገባላቸው ገንዘብ አለመከፈሉን አረጋግጦ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ካሳውን እንዲከፍል ስምምነት መደረሱን ለፓርላማ በሰጠው ማብራሪያ አስታውቋል። የፓርላማው አባላት በበኩላቸው በመገንባት ላይ ለሚገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ ያርፍበታል ተብለው ...

Read More »

የማህበራዊ ሚዲያዎች ለፖለቲካ ተቃውሞ ዋነኛ ምህዳር ሆነዋል ተባለ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ   “ሶሻል ሚዲያ ለፀጥታ እና ለብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ያለው ፋይዳ እና የምንከተለው ስትራቴጂ “ በሚል   ለጸጥታ ሃይሎች ባዘጋጀው ሰነድ ላይ “ ማህበራዊ ድረገጾችን በመጠቀም የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ተፈላጊነት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ፣ የልማታዊ መንግስት ግንባታ እንቅፋቶች የሆኑትን ጠባብነት ፣ ትምክት፣ አክራሪነት ወይም ጽንፈኝነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት እና ...

Read More »

የኢህአዴግ ባለስልጣናት እርስ በርስ ተወራረፉ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በፌዴሬሽን ም/ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ም/ል ጠ/ሚኒስትርና የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል  የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን “ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተሰርቆ መውጣቱን ቀድሞ ካወቃችሁ ለምን በደህንነት መስመር ፈተናውን አስወጥተህ ወዲያውኑ እንዲረጋገጥ አላስደረክም፣ አሳፋሪ መግለጫ እያወጣችሁ ለምን የህዝብ መሳቂያ መሳለቂያ ታደርጉናላችሁ” ያሉዋቸው ሲሆን፣ አቶ ...

Read More »