በድርቁ ምክንያት ስድስት ሚሊዮን ህጻናት ትምህርታቸው ሊስተጓጎል እንደሚችል ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በትምህርት ላይ የሚገኙ የሚገኙ ወደ ስድስት ሚሊዮን ህጻናት ትምህርታቸውን ሊስተጓጎል እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በወቅታዊ የሃገሪቱ የድርቅ አደጋ ዙሪያ ሪፖርትን ያወጣው ድርጅቱ በድርቁ መባባስ የተነሳ ተማሪዎች ለምግብና ለውሃ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ገልጿል። እነዚሁ ለከፋ የድርቅ አደጋ ተጋልጠው የሚገኙትና ቁጥራቸው ወደ ስድስት ሚሊዮን አካባቢ የሚደርሱ ህጻናት ...

Read More »

ሊሰበሰብ ከታቀደው የውጭ ንግድ ገቢ ግማሽ ያህሉ ብቻ መገኘቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) በመገባደድ ላይ ባለው የ2008 በጀት አመት ከውጭ ንግድ ገቢ ሊገኝ ከታቀደው አራት ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች 51 በመቶ የሚሆነው ብቻ መገኘቱን የንግድ ሚኒስቴር ገለጸ። የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል የሃገሪቱ የንግድ ሚዛን ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ ልዩነት እንዲያሳይ ምክንያት መሆኑም ታውቋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች የተገኘው የውጭ ንግድ ገቢ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጻር በ 6.5 ...

Read More »

ተመድ በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ሪፖርት አቀረበ

ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ ኮሚቴ በስደት የሚገኙ 500 ያህል ኤርትራውያን በማነጋገር ያጠናቀረው ይህ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ሪፖርት፣ የግዳጅ ውትድርና፣ እስራት ግድያና ማሰቃየት በሃገሪቱ እንድሚፈጸም የሚዘረዝር ሲሆን፣ ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘችበት እኤአ ከ1991 ጀምሮ የተከሰተው በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲታይ የፀጥታው ም/ቤት እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል። በስዊዘርላንድ መዲና ጄኔቫ ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት 51 ኢትዮጵያዊ ሶማሊዎችን መግደሉን ኦብነግ አስታወቀ

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ድርጅት ፣ ኦብነግ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የመከላከያ ሰራዊት ግንቦት28፣ 2008 ዓምበጋሻሞ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ጃማ ዱባብ መንደር ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት 51 ሲቪሎች ተገድለዋል። ጦሩ ፊት ለፊት ባገኛቸው ዜጎች ላይ በጭፍን መተኮሱን የገለጸው ኦብነግ በጥቃቱ ህጻናት፣ ሴቶችና ሽማግሌዎች ተገድለዋል። ጦሩ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነዋሪዎቹ መስጊድ በመግባት ራሳቸውን ለማትረፍ ጥረት ...

Read More »

የሰኔ 1 ሰማዕታት ታስበው ዋሉ።

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተካሄደውን የግንቦት ወር ምርጫ 1997 ዓመተ ምህረት ተከትሎ “ድምጻችን ይከበር!” በማለት ሰልፍ በመውጣታቸው ሳቢያ  በመንግስት ታጣቂዎች የተገደሉት የሰኔ 1 ሰ ማዕታት 11ኛ ዓመት ዛሬ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ታስቦ ውሏል። በመንግስት ደረጃ በወጣው ሪፖርት ሰኔ 1 ቀን የተገደሉት ሰማዕታት 42 እንደሆኑ ቢነገርም፤  በወቅቱ የሀዘነኞችን ቁጥር ዋቢ በቅርበት የተከታተሉ ገለልተኛ ...

Read More »

በአማራ ክልል ከፍተኛ የዘይት እጥረት ተፈጠረ

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ያለው የዘይት አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ በ ነዋሪዎች ህይወት ላይ ችግር ሲፈጥር ቢቆይም፣ በአማራ ክልል ግን የከፋ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገዢው ፓርቲ  በፋሲካ  ሰሞን  በነፍስ ወከፍ  አንድ ሊትር ዘይት ካከፋፋለ በሁዋላ እስካሁን ዘይት የሚባል ነገር አልቀረበም። ክፍፍሉን ፍትሃዊ እናደርጋለን በማለት ለነዋሪዎች የዘይት የሬሽን ካርድ ያደለው አስተዳደሩ፣ ቃል በገባው ጊዜ ማቅረብ ባለመቻሉ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በባለሙያ የሚመራ ባለመሆኑ ሃላፊነቱን ለአትሌቶች እንዲያስረክብ ተጠየቀ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ቅሬታን ማቅረብ የጀመሩ አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶች ፌዴሬሽኑ ባለሙያ የሚመራ አይደለም በማለት ፌዴሬሽኑ ሃላፊነቱን ለአትሌቶች እንዲያስረክብ ማክሰኞ ጠየቁ። በወቅታዊ የሃገሪቱ የስፖርት ጉዳዮች ላይ በመምከር አስቸኳይ ምክክርን ያደረጉ አትሌቶች፣ ፌዴሬሽኑ ከአትሌቲክስ ዘርፍ ግንኙነት በሌላቸው አካላት በመመራቱ ቅሬታዎች እንዲበራከቱና በአትሌቲክስ ውድድርም ውጤት እየተመናመነ እንዲሄድ ማድረጉን ገልጸዋል። ሰሞኑን ሃገሪቱን በብራዚሉ ኦሎምፒክ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ...

Read More »

በ5 ሚሊዮን ዶላር የተገዛው የኤችአይቪ ኤይድስ ቁሳቁስ ህጋዊ እውቅና በሌለው በቻይና ኩባንያ የቀረበ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ኤይድስ (HIV/AIDS) ምርመራዎችን ለማካሄድ ይረዳሉ ተብለው ከአምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ወጪ የተፈጸመባቸው ቁሳቁሶች ህጋዊ እውቅና በሌለው አንድ የቻይና ኩባንያ ወደ ሃገር ውስጥ መግባቱ ጥያቄ አስነሳ። ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የህክምና ቋቁሶች አጠቃቀሙን የሚያስረዳ መመሪያ የሌላቸው ሆነው ወደ ሃገር ውስጥ መግባታቸውም ታውቋል። ቤጂንግ ዋንቲ ባዮሎጂካል ፋርማሲ በተባለ ኩባንያ ግዢ የተፈጸመባቸው የህክምና ...

Read More »

የኢንተርኔት አጠቃቀም አዋጅ ጸደቀ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) በኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ጥብቅ ቁጥጥርን ያደርጋል ተብሎ ከተለያዩ አለም አቀፍ አካላት ትችት ሲቀርብበት የቆየውና የኮምፒውተር ወንጀል ለመደንገግ የቀረበው አዋጅ ማክሰኞ ጸደቀ። የኢትዮጵያ መንግስት የረቂቁ የኢንተርኔት የስለላ ቁሳቁሶችን እንደሚጠቀም መረጃዎች ቢቀርቡበትም ሃገሪቱ የኮምፒውተር ወንጀል ጥቃት እየሆነ መጥታለች ሲሉ በቅርቡ መግለጹ ይታወሳል። ማክሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው አዲሱ አዋጅ፣ ግለሰቦች ለአመፅ ያነሳሳሉ የተባሉ የፎቶና የቪዲዮ ምስሎችን ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ከ40 ያላነሱ ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የሶማሊ ክልል ጋሻሞ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከ40 የሚበልጡ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘገቡ። ግድያው የተፈጸመባቸው 42ቱ ሰዎች አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የዩኒስ ኢሳቅ ንዑስ ጎሳ አባላት መሆናቸውንም ሳላን ሚዲያ የተሰኘ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም አስነብቧል። ግድያ ተፈጽሞባቸዋል የተባሉ ሁለት ንዑስ ጎሳዎች በጎረቤት ሶማሊላንድ ...

Read More »