በአዲስ አበባ ዙሪያ ከቀያቸው ተፈናቅለው ኮረብታ ላይ የሰፈሩት ዜጎች እንደገና ተነሱ

ሰኔ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደገለጸው ከአዲስ አበባ የዘፈቀደ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የእርሻ ቦታቸውን የተነጡቁት  አርሶአደሮች ፣ በለቡ አደባባይ አብርሃሙ ስላሴ ቤተክርስቲያን ያለበት ኮረብታማ ቦታ ላይ መኖሪያ ቤታቸውን ሰርተው ቢኖሩም፣ አሁንም እንደገና ቤታቸው እንዲፈርስ በመደረጉ ያለምንም ካሳ መውደቂያ አጥተው ይገኛሉ። ነዋሪዎቹ ቤቶቻቸው ሲፈርሱባቸው እቃዎቻቸውን እንኳን እንዲያወጡ ጊዜ አልተሰጣቸውም። ነዋሪዎቹ ከዚህ በፊት በከተማው መስፋፋት ምክንያት ሲገፉ ቆይተው ኮረብታው ...

Read More »

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮችን ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢያወጣም የሚመዘገብ ወጣት ሊያገኝ አለመቻሉ ተገለጸ።

ሰኔ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወታደርነት መቀጠር የሚፈልጉ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ  ወጣቶች   ከግንቦት 30 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ድረስ እንዲመዘገቡ የሚጠይቁ ማስታወቂያዎች በየቦታው ቢለጠፉም ፣ የሚመዘገቡ ወጣቶች ቁጥር አነስተኛ መሆን ገዢው ፓርቲን አሳስቦታል። በማስታወቂያው ከወጡት መስፈርቶች መካከል ኪሎ- ከ50 እስከ 70 የሆነ፣ ቁመት ከ1 ሜትር 60 በላይ ፣ በብሔረሰብ እኩልነት የሚያምንና ከዚህ ቀደም ፖሊስ ...

Read More »

በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ግጭት ሁለቱም አገራት እርስ በእርስ ተወነጃጀሉ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን ሁለቱም መንግስታት አስታወቁ። እሁድ ሰኔ 5 ቀን 20008 ዓም በፆረና ግንባር ተከሰተ በተባለ ግጭት ሁለቱም መንግስታት ዕርስ በዕርስ የተወነጃጀሉ ሲሆን፣ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን በሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን  የዘገቡት ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ድረገጾች ሲሆን፣ ኤርትራ መጠነ ሰፊ ጥቃት ተሰንዝሮባታል ብለዋል፣ ውጊያው ...

Read More »

በጎንደር ዳባት 40 የሚሆኑ ሰዎች መታሰራቸው ተነገረ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ ከኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ማሽን መነሳት ጋር ተያይዞ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ወደ 40 የሚደርሱ ነዋሪዎች ለእስር ተዳረጉ። የዞኑ አስተዳደሮች ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ድርድር እንዲካሄድ ጥረትን ቢያደርጉም የከተማዋ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውን እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። የተቀሰቀሰው ግጭት ለሁለተኛ ሳምንት ዕልባት አለማግኘቱን የተናገሩት ...

Read More »

ሶስት የክልል ፕሬዚደንቶች በአውስትራሊያ የጠሯቸው ስብሰባዎች በተቃውሞ ተበተኑ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ ሶስት የክልል ፕሬዚደንቶች በአውስትራሊያ ካንበራና ሜልበርን የጠሩዋቸው ስብሰባዎች በተቃውሞ ተበተኑ። ቅዳሜ ሰኔ 4 በካንበራ እንዲሁም ሰኔ 5 ፥ 2008 በሜልበርን የተጠራውን ስብሰባ ኢትዮጵያውያን ተደራጅተው ባስተባበሩት ተቃውሞ የተበተነ ሲሆን፣ ፖሊስ ተቃውሞውን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ለመጠቀም መገደዱን የቋጠሮ ድረገጽ አዘጋጅ ሳምሶን አስፋው ከስፍራው ዘግቧል። የትግራይ ክልል ፕሬዜደንት አቶ አባይ ወልዱ፣ ...

Read More »

የደሞዝ ገቢ ታክስ ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ የመንግስት የታክስ ገቢ እንዲቀንስ የሚያደርግ መሆኑ ተገለጠ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ገቢ ታክስ ለማሻሻል ሰሞኑን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ የመንግስት የታክስ ገቢ በሶስት ቢሊዮን ብር እንዲቀንስ የሚያደርግ መሆኑ ተገለጠ። ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰራተኞች በየአመቱ ወደ አምስት ቢሊዮን ብር አካባቢ በገቢ ታክስ ሲከፍሉ መቆየታቸውን ያወሳው የገንዘብና የኢኮኖሚ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጁ የሚጸድቅ ከሆነ የሶስት ቢሊዮን ብር አካባቢ ገቢ መቀነስ እንደሚኖር አስታውቀዋል። ይሁንና የሚኒስቴሮች ምክር ቤት በቅርቡ ...

Read More »

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተራዘመ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) የትምህር ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ። ሚኒስቴሩ የፈተናው መሰረቅን ተከትሎ ብሄራዊ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓም እንደሚካሄደ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁንና የኢትዮጵያ ኣስልምና ጉዳዮች ጠቅላላ ምክር ቤት የፈተናው ጊዜ ከረመዳን ጾም ጋር የተገናኘ ነው ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ፈተናው ለሁለተኛ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን ገልጿል። ለሁለተኛ ጊዜ ...

Read More »

አቶ ጌታቸው ረዳ በጀርመንት አገር ተቃውሞ ገጠማቸው

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008) የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በጀርመን ሃገር ተቃውሞ ገጠማቸው። በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት ከተማ ሰኞ ሰኔ 6 ፥ 2008 ከኢትዮያውያን ተቃውሞ የገጠማቸው አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቀመጫቸውን ለቀው ሲሄዱ ታይተዋል። በተንቀሳቃሽ ምስል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ጌታቸው ረዳ ለደቂቃዎች ተቃውሞዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ እርሳቸውም ተቃውሞ ያሰሙትን ሰዎች ለማግባባት ሲሞክሩ ታይተዋል። አቶ ጌታቸው ረዳን ያረፉበት ...

Read More »

ኤርትራ በጾረና ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረባት አስታወቀች

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በጾረና ግንባር የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ትናንት እሁድ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ስለ ጥቃቱ ዝርዝር መግለጫ እንደሚያወጣ ገልጿል። በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መግለጫ የለም። በሁለቱም ድንበሮች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታዬ ሲሆን፣ ጥቃቱ ወደ ሙሉ ጦርነት ይሸጋገር አይሸጋገር ገና  የታወቀ ነገር የለም። አርበኞች ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ ጦርነቱ ህወሃት ከገባበት የውስጥ ...

Read More »

በአልሸባብ የተገደሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥር አሻቀበ

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት አልሸባብ የተባለው ታጣቂ ቡድን በማእከላዊ ሱማሊያ በኢትዮጵያ የጦር ካምፕ ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት 89 ወታደሮች ሲሞቱ 103 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ወታደሮች በተከታታይ ቀናት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ በጽኑ ከቆሰሉት መካከል ደግሞ 60 ወታደሮች ቅዳሜ ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተልከዋል። ቁስለኞቹ በህክምና ላይ መሆናቸውን ኢሳት ከሆስፒታሉ ምንጮች ለማረጋገጥ ...

Read More »