ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ግጭትን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ሁለቱም አገራት ከጦር ትንኮሳዎች ታቅበው በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና መረጋት በሚሰፍንበት ጉዳይ ላይ አበክረው እንዲሰሩ ሲል ጥሪውን አቅርቧል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጽሑፍ ለሁለቱም አገራት በላከው መግለጫው ሀገራቱ ከግጭት ቀስቃሽ እርምጃዎች ታቅበው ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጡ ጠይቋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከወታደራዊ እርምጃዎች ታቅበው ጉዳዩን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሣስበዋል።
Read More »በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ኩንቢ ወረዳ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ ፖሊስን ጨምሮ 10 ሰዎች ተገደሉ
ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሎቹ ድንበር አዋሳኝ ላይ በምትገኘው ኩንቢ ወረዳ በሁለቱ ብሔረሰቦች መሃከል በተቀሰቀሰው የድንበር ግጭት ሳቢያ ከሞቱት መካከል ዘጠኙ ሰላማዊ ዜጎች ሲሆኑ አንድኛው የልዩ ጦር አባል ናቸው። በትናንትናው እለት ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የተፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት በዋነኛነት ትእዛዝ በመስጠት ሲመሩ የነበሩት የሶማሊያ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመር መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ የሚመራው ልዩ ጦር በወሰደው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ምክንያት ዘጠኝ የኦሮሞ ብሔርተወላጆች መገደላቸውና በአጸፋውም አንድ የልዩ ጦር ታጣቂ መገደሉ ታውቋል። የፌደራል ፓሊስ አባላት ወደ ቦታው ሄደው ሕዝቡን ካረጋጉ በኋላ ለልዩ ኃይሉ አስረክበውመውጣታቸው ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱ ሲታይ ሆንተብሎ በፌደራል ፖሊስ የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ያመላክታል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።በተጨማሪም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ከነገሌ ቦረና 30 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ በሶማሌ መርሃን ጎሳ አባላትና በቦረናዎች መሃከል ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሮ የግጭት ስጋት አንዣቧል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች መሳሪያቸውን አንግበው ምሽግ ይዘው በደፈጣ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው የአካባቢውም ነዋሪዎች ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያየዘ በስጋትና ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸውን ምንጮቻችን አክለው ዘግበዋል።
Read More »በመፈንቅለ መንግስት በተከሰሱት በጄነራል ተፈራ ማሞና በጀነራል አሳምነው ጽጌ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ገቡ
ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከግንቦት 7 ጋር በማበር መፈንቅለ መንግስት ልታደርጉ ነው በሚል ምክንያት ከሚያዚያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ላለፉት ስምንት ዓመታት በጨለማ እስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የቆዩት ጄነራል ተፈራ ማሞና ጄነራል አሳምነው ጽጌ እስርቤት ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክ አስገብታችኋል በሚል ምክንያት በደረሰባቸው አሰቃቂ ድብደባ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው እራሳቸውን በመሳታቸው ሆስፒታል ገብተዋል። በተጨማሪም የጄኔራል አሳምነው ጽጌ አክስት ከ14 ዓመት ልጃቸው ጋር ለአንድ ቀን ታስረው ከሕግ ውጪ ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ከጄኔራሎቹ ጋር አብሮ የታሰረ አንድ የኦሮሞኛ ቋንቋ ጋዜጠኛም በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስሮ አሰቃቂ የሆነ ድብደባ እየተፈጸመበት መሆኑንምንጮችአስታውቀዋል። ጄኔራሎቹና አብረዋቸው የተከሰሱት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ላይ እጃቸው ከተያዘበት እለት ጀምሮ ዓይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ አካላዊ ጥቃቶች ሲፈጸምባቸው እንደቆየ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወቃል። ከተከሳሹቹ አብዛሃኞቹ ካለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በህወሃት ልዩ የደኅንነት ኃይሎች በምርመራ ሰበብ በየጊዜው ልብሳቸውን እያወለቁ ከመገረፋቸውም በላይ እስካሁን ድረስ ሕጋዊ መብታቸው ሳይከበር በጨለማ ቤት ተጥለው ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸውና ከሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል።
Read More »የኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች በእዳ መዘፈቃቸውንና በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ስጋት መደቀናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ
ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዥው ፓርቲ ተነድፈው ኢትዮጵያን በዓለም አስረኛ ስኳር ላኪ ያደርጓታል ተብለው የተጀመሩት የስኳር ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በእዳ መዘፈቃቸውን ጥናቶች አጋልጠዋል። ለፕሮጀክቶቹ መስተጓጎል የባለሙያዎች እጥረትና የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ፈንድ ማጣት በዋነኛነት የተጠቀሱ ችግሮች መሆናቸው በጥናቱ ተመልክቷል። በደቡብ ክልል በኦሞ ሸለቆ ውስጥ ለሚገኘው የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ መስተጓጎል ዓይነተኛ ችግሮቹ ፦አካባቢው ለልማት ምቹ የሆነ ስፍራ ላይ አለመገኘቱና የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ሲሆኑ፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሜቴክ የፈጠረው ችግርም የፕሮጀክቱን ቀጣይ ትርፋማነትስጋት ውስጥ ጥሎታል ተብሏል። በኬኒያ ቱርካና ሃይቅ ብዝኅሕይወት ላይም አደጋ ከመደቀኑ በተጨማሪ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ ድንበር አቅራቢያ በሚኖሩ ከ200 ሽህ በላይ አርብቶ አደሮች ህልውና ላይ ስጋት መጋረጡን የኦሞ ቱርካና የጥናት ማእከል ተመራማሪ የሆኑት ቤኔዴክት ባምስኪ በጥታናታዊ ሪፓርታቸውአስታውቀዋል። 4.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እ.ኤ.አ. በ2011 የተጀመሩትና በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩት በመላው አገሪቷ ውስጥ የሚገኙ 10 የስኳር ፋብሪካዎች በአምስት ዓመታት ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስኳር ያመርታሉ ተብሎ ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካሁንድረስ ግን የትኞቹም በአግባቡ ስራቸውን አልጀመሩመ። ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት በምሕጻረቃሉ አይኤምኤፍ ባወጣው ሪፖርት በዘንድሮው ዓመት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት ከነበረበት 8.7 % ወደ 4.5% እንደሚያሽቆለቁል አስታውቋል።በጋምቤላ ክልል ውስጥ የ100 ሽህ ሄክታር ባለይዞታ እንደነበረውና በህንዳዊው ባለሃብት ሲንቀሳቀስ እንደቆየው እንደ ካራቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ያሉ በመንግስት የቀረቡት የግብርና ኢንቨስትመንቶችም ሙሉ ለሙሉ አዋጪ እንዳልሆኑና በኪሳራ መደምደማቸውን ጥናቱ አረጋግጧል። ከቻይናው ኢምፓርትና ኤክስፓርት ዴቨለፕመንት ባንክና ከቻይና ንግድና ኢንዱስትሪ ባንኮች 1.63 ቢሊዮን ዶላር ብድር መገኘቱን የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚንስቴር አስታውቋል። የመጀመሪያው ዙር የእዳ ክፍያ የሚጀመረው በመጪው ጥቅምት ወር መሆኑን የብድር ስምምነቱ ሰነድ ውል ላይ ሰፍሯል። በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 49 ቢሊዮን ብር ማለትም 2.25 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር በፕሮጀክቱ ስም ተወስዷል። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃል አቀባይ አቶ ጋሻው አይችሉህም ተጠይቀው የፕሮጀክት ጥናቱ ሂደቱ ሳይጠናቀቅ ምላሽ ለመስጠትፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸውን በለንደን ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ አቶ አብዱልመናን መሃመድ ሃምዛ 40% የሚሆነውን እዳ የተሸከመችን አገር ይዞ እንደዚህ ዓይነት የፕሮጀክት ኪሳራ ሲያጋጥም ትልቅ አገራዊ ክስረት ያስከትላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ከኩራዝ አንድ ስኳር ፋብሪካግንባታ እስካሁን ድረስ 75% ብቻ ስራውን ያጠናቀቀው ሜቴክ ፤ፕሮጀክቱ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ 97% የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ መውሰዱን የብሉንበርግ ዘገባ ያመለክታል።
Read More »በኢትዮጵያ ሆስፒታል ለመገንባት የተሰባሰቡ ባለሙያዎች ማህበራቸው ለዶ/ር ቴዎድሮስ ድጋፍ በማድረጉ ተቃውሞ አሰሙ
ኢሳት ( ሰኔ 7 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሆስፒታል በመገንባት የህክምና አገልግሎት እንሰጣለን በሚል በሰሜን አሜሪካ የተሰባሰቡ የህክምና ዶክተሮች ማህበራቸው ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ድጋፍ በማድረጉ፣ ከአባላት ተቃውሞ ገጠመው። ሆስፒታሉ በተያዘው 2016 ስራ ይጀምራል ተብሎ ቃል የተገባ ቢሆን፣ ግንባታ አለመጀመሩም ጥያቄ አስነስቶ ምንም ስራ ሳይሰራ 600 ሺህ ዶላር ወጪ መሆኑንም አባላቱ አወያይቷል። በቁጥር 250 የሚሆኑ በትውልድ ኢትዮጵያውያን የሆኑትና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ...
Read More »ያለአግባብ በጀት የተጠቀሙ ድርጅቶች ተጨማሪ በጀት ተያዘላቸው
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2008) ባልፈው በጀት አመት ከስድስት ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብ አላግባብ ተጠቅመዋል የተባሉ መንግስታዊ ድርጅቶች ጉዳያቸው እልባት ሳያገኝ ተጨማሪ በጀት እንዲያዝላቸው መደረጉ ተቃውሞን አስነሳ። ከሶስት ሳምንት በፊት የጠቅላይ ኦዲት ተቋም የመከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ ወደ አምስት የሚጠጉ መንግስታዊ ድርጅቶች ከስድስት ቢሊዮን የሚበልጥ ገንዘብን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል ሲል ሪፖርት ማቅረቡ ይታወሳል። በመንግስት በጀት አጠቃቀም ዙሪያ ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀረበው የኦዲት ...
Read More »የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚያካሄደው የንግድ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ በመሰረቁ ተስተጓጎለ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2008) ለሶስት መንግታዊ ተቋማት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ የመዳብ የኤሌክትሪክ ገመድ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መዘረፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያካሄደው የንግድ አገልግሎት ተስተጓጎለ። ከሁለት ሳምንት በፊት ተፈጽሟል በተባለው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያው መስመር መዘረፍ ምክንያት የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ጨምሮ የኢትዮጵያን የዱር አራዊት ጥበቃ ባለስልጣን ስራቸው ማካሄድ እንዳልቻለ ታውቋል። ፖሊስ ከ10 ሜትር በላይ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ...
Read More »በከባድ የዝናብና የጎርፍ አደጋ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2008) በተለያዩ ክልልች በተያዘው የክረምት ወቅት በሚኖር ከባድ የዝናብና የጎርፍ አደጋ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የብሄራዊ አደጋ ኮሚሽን ማክሰኞ አሳሰበ። ኮሚሽኑ ባለፈው ወር ወደ 408 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ከቀያቸው ይፈናቀላሉ ሲል ትንበያን ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ቁጥሩ ከ80ሺ በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስታውቋል። በዝናብና በጎርፍ አደጋ ከቀያቸው ይፈናቀላሉ ተብሎ የሚጠበቁ ሰዎችን ለመደገፍ ከ220 ...
Read More »በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አንድ እስረኛ ተገደለ፣ በሌሎች እስረኞች ላይ ጉዳት ደረሰ
ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2008) ፖሊሶች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ማክሰኞ ዕለት ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ አንድ እስረኛ መገደሉን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የእስረኛን ቤተሰቦች በመደበኛ ሰዓት ምግብ እንዲያቀብሉ ዕገዳ ተጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በመጨረሻ ምግብ ቢገባም እንደወትሮው ማነጋገር አልተፈቀደም። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት፣ ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ ለእስረኛች ከሶስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ይገባ የነበረው ስንቅ፣ እስከ ከሰዓት ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ተከልክሎ የቆየ ሲሆን፣ ቤተሰብ ...
Read More »ሜቴክ በህገወጥ መንገድ የሚገነባው ፋብሪካ በዩኒስኮ የተመዘገበውን የያዩ የቡና ጫካ ሊያጠፋው መቃረቡ ታወቀ
ሰኔ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የያዩ የቡና ጫካ በእንግሊዝኛ ስያሜው Yayu Coffee Forest Biosphere Reserve በዩኒስኮ ከተመዘገቡት ሁለት የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጫካዎች አንዱ ቢሆንም፣ የመከላከያ ብረታብረት ኮርፖሬሽን ምህንድስና ( ሜቴክ) በሚገነባው የያዩ ድንጋይ ከሰል ልማትና ማዳበሪያ ፋብሪካ ኮፕሌክስ የተነሳ ጨካው የመጥፋት አደጋ እንደተደቀነበት ከማእድን ሚኒስቴር ለኢሳት የተላኩት ሰነዶች አመልክተዋል። ሜቴክ ግንባታውን የጀመረው ከማእድን ሚኒስቴር ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ...
Read More »