ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የጸጥታና የደህነት ሃይሎች ሙሉ ስም ዝርዝር፣ የመታወቂ ቁጥር፣ የመኖሪያና የስራ አድራሻ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ኢሳት እጅ ገብተዋል። የጸጥታ ሃይሎች ያደረጉዋቸውን ስብሰባዎች የሚያሳዩ ቃለ ጉባኤዎች እንዲሁም በሚስጢር እንዲያዙ የተደረጉ የምርምራ ዘገባዎችም ኢሳት እጅ ገብተዋል። ኢሳት የደህንነት ምንጮቹን አደጋ ውስጥ በማይጥል መልኩ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ዋና ዋና መረጃዎችን እየመረጠ ...
Read More »የመንግስት ወታደሮች 400 የኦሮሞ ተወላጆችን መግደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ
ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ተካሂዶ በነበረው ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ወቅት በገዥው መንግስት ታጣቂዎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰላሚዊ ዜጎች በግፍ መገደላቸውንና ከአስር ሺ በላይ መታሰራቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው ሪፓርት ገልጿል። ሂውማን ራይትስ ወች ለተወሰደው ኢሰብዓዊ ጨፍጨፋ የኢትዮጵያ መንግስት በአፋጣኝ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ብሏል። ገለልተኛ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ በዜጎች ...
Read More »ግብፅ ፖለቲከኞችና ምሁራን በአባይ ግድብ ላይ ጥቃት ማድረስ እንደማራጭ እንዲወሰድ ጠየቁ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ላይ ጥቃትን እንደአማራጭ ሊወስድ እንደሚገባ የሃገሪቱ የፖለቲካ አመራሮችና ምሁራን ጥያቄ ማቅረብ መጀመራቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። በጉዳዩ ዙሪያ ይፋዊ ምላሽ የሰጡት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምህ ሽክሪ በበኩላቸው በመነሳት ላይ ያለውን አማራጭ ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን አስዋት ማሶሪያ የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጥቃትን እንደአማራጭ የሚለው ሃሳብ ተቀባይነት ...
Read More »ባለፉት ሁለት አመታት በእሳት አደጋ አንድ ቢሊዮን ብር የሚደርስ ንብረት መውደሙ ታወቀ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማና ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በሚደርሱ የእሳት አደጋዎች ጥናትን ያካሄዱ አካላት ባለፉት ሁለት አመታት በደረሱ አደጋዎች ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የሚደርስ ንብረት መውደሙን ይፋ አድርጓል። ከአሜሪካ የልማት ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን በተካሄደው ጥናት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ወደ 70 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ወጪ መደረጉ ...
Read More »በኢትዮ-ሶማሊላንድ ድንበር በኮንትሮባንድ ነጋዴዎችና በልዩ ፖሊስ መካከል በተደረገ ግጭት 21 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) ከሶማሊያ በተገነጠለችው ሶማሌላንድና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በኮንትሮባንድ ነጋዴዎችና በልዩ ፖሊስ መካከል በተደረገ ግጭት 21 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ጋሻሞ ተብላ በምትጠራው በዚህ መንደር ለ21 ሰዎች ሞት መንስዔ የሆነው ግጭት፣ አሳዛኝ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ሞሃመድ ኦማር፣ ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ኮንትሮባንድ ጭኖ ይጓዝ የነበረን መኪና በሃይል ለማስቆም በመሞከራቸው የደረሰ አሳዛኝ ክስተት ማለታቸውን ጋራዌ ኦንላይን ...
Read More »ግብፅ ሰሞኑን በሶማሊያ ለሞቱ የኢትዮጵያ ወታደር ቤተሰቦች ሃዘኗን ገለጸች
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ላይ በተፈጸመው ጥቃት የሞቱ ወታደሮች እንደሌሉ ቢገልፅም፣ የግብጽ መንግስት ደርሷል ባለው ጥቃት ለተጎጂ ቤተሰቦች ሃዘኑን ገለጸ። የደረሰው ጥቃት በተመለከተ ማክሰኞ ምሽት መግለጫን ያወጣው የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱ ክፉኛ እንደሚያወግዝ አስታውቆ፣ የተሰማውን ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስትና ለተጎጂ ቤተሰቦች አስተላልፏል። የኢትዮጵያ መንግስት ከቀናት በፊት በወታደሮቹ ላይ በተደረገው ጥቃት ...
Read More »በሆለታ ስፖንጅ ፋብሪካ በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ንብረት አወደመ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው የሆለታ ከተማ ሃሙስ በአንድ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ንብረት በቃጠሎ ወደመ። ምክንያቱ ባልታወቀውና ማለዳ ላይ እንደደረሰ በተነገረው በዚሁ አደጋ በፋብሪካው ማሽን ላይ ከባድ ውድመት ያደረሰ ሲሆን፣ ፖሊስ የቃጠሎውን ምክንያት ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል። ለሽያጭ የተዘጋጁ ምርቶች እንዲሁም ጥሬ እቃዎች በእሳት ...
Read More »ለኢሳት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንንና ሬዲዮ /ኢሳት/ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። ለኢሳት በስጦታ የተበረከቱ መኪናዎች ቁጥር 120 መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን፣ አድቦኬሲ ኢትዮጵያ የተባለ የኢትዮጵያውያን ስብስብ ደግሞ በዚህ ሳምንት ወደ 15ሺህ ዶላር የሚጠጋ ስጦታ አበርክቷል። ኢሳትን በገንዘብ ከማጠናከር በተጨማሪ፣ በአይነት ድጋፍ እንዲደረግ በቀረበው ጥሪ መሰረት ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ለኢሳት የተበረከቱ መኪናዎች ቁጥር 120 ...
Read More »ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደትግል ቦታ መመለሳቸው ታወቀ
ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008) በዩኤስ አሜሪካና አውሮፓ ለሳምንታት ቆይታ ያደረጉት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ስፍራ መመለሳቸው ታወቀ። ማክሰኞ አስመራ የገቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአመሪካና አውሮፓ ከተሞች ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አቀባባል እንደተደረገላቸው ይታወቃል። በዩ ኤስ አመሪካ ዋሽንግተን ዲሲና ሲያትል ከተሞች እንዲሁም በአውሮፓ ኦስሎ ጄኔብና ፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር የተወያዩትና ከፍተኛ አቀባበል የተደረገላቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ...
Read More »በሶማሊያ ለአመታት ቁልፍ የሆኑ የደህንት ስራዎችን ሲሰሩ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሰራተኞች ( ሰላዮች) ማንነታቸው ባልታወቁ አልሞ ተኳሾች እየታደኑ መገደላቸው ተጠቆመ።
ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ይህ ክስተትም በአገሪቱ ውስጥ የሚገኘውን ሰራዊት አደጋ ላይ መጣል ብቻ ሳይሆን በመከላከያ ሰራዊትና በደህንነቱ ክፍል መካከል ከፍተኛ የሆነ ፍርሃትና አለመተማመን መፍጠሩን፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው የደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው ምስጢራዊ መረጃ ያመለክታል። የዚህን ዜና ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን።
Read More »