ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2008) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች በመሰራጨት ላይ ባለው የአጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ በሽታ ከ2ሺ በላይ ሰዎች ለህመም መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ገለጠ። የአለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩዩ አካላት የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ የበሽታው ስርጭት መጨመር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አመልክቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በ15 ሰዎች ላይ ተከስቶ የነበረው የበሽታው ምልክት ...
Read More »የአዲስ አበባ ተራ አስከባሪዎች ያለፍላጎታቸው የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ እየተገደዱ ነው
ኢሳት (ሰኔ 13 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አስሩም ክፍለ ከተሞች በታክሲ ተራ ማስከበርና በተሽከርካሪ ማፅዳት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወጣቶች ያለፍላጎታቸው የገዥው የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ መገደዳቸውን ለኢሳት አስታወቁ። በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙ የኢህአዴግ ተወካዮች ወጣቶቹ በአባልነት ካልታቀፉና ፎርምን ካልሞሉ በተሰማሩበት ስራ ላይ መቀጠል እንደማይችሉ ሰሞኑ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸላቸው ወጣቶቹ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን ...
Read More »ኤርትራ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ለተሰነዘረባት ጥቃት የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ገለጸች
ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ኢትዮጵያ በቅርቡ በኤርትራ ላይ ለሰነዘረችው ጥቃትም ሆነ በአካባቢው ላሰማራችው ሳራዊት የአሜሪካ እጅ አለበት። የአሜሪካ መንግስት ሁለቱም ሃይሎች ጦርነት ውስጥ እንዳይገቡ ያስጠነቀቀ ቢሆንም፣ የኤርትራ መንግስት የአሜሪካ መግለጫ ጎጂውንና ተጎጂውን እኩል የሚፈርጅ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብሎአል። የኤርትራ መንግስት በሰሞኑ ግጭት የአሜሪካ እጅ አለበት ቢልም ዝርዝር መግለጫ ወደ ፊት ...
Read More »ሱዳን መከላከያዋን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ማስጠጋቷ ተሰማ
ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ታጣቂ አርሶደአሮች የሱዳንን አርሶደአሮች በማባረር መሬታቸውን እየቀሙ ነው በሚል የአገሪቱ መከላከያ ሃይል የተወሰነ ጦሩን ወደ ድንበር አካባቢ አንቀሳቅሷል። ምንም እንኳ ሱዳን ወታደሮቿን ብታንቀሳቅስም፣ እስካሁን ደረስ ወታደሮቿ በኢትዮጵያ አርሶአደሮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ አልደፈሩም። የሱዳን መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ታጣቂ አርሶአደሮች ከ800 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ወስደውብናል በማለት ውንጀላ ያቀርባሉ። ፣ የሁለቱ አገራት ...
Read More »በረሃብ አድማ ላይ የሚገኘው አቶ አግባው ሰጠኝ በብሄሩ የተነሳ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ተናገረ
ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ጌታቸው መኮንን መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከ1 አመት ከ8 ወራት ላላነሰ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት 16 ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነሱ መካከል አቶ አግባው ሰጠኝ በማንነቱ የተነሳ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል። አቶ አግባው ከግንቦት 17 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በቂሊንጦ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን፣ በጀመረው የረሃብ ...
Read More »በአማራ ክልል የተሰራጨው የቡና ዘር ምንነት አለመታዎቅ ስጋት አስከትሏል፡፡
ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ደጋማ ክፍል በእርዳታ ስም የተሰራጨው የቡና ዘር ምንነት ሳይመረመር በመሰራጨቱ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። ማንነቱ ያልታወቀ የውጭ ዜጋ መስመሩን ባልተከተለ ሁኔታ ባለሙዎችን ሳያሳትፍ እና በቂ ገለጻ ሳያደርግ የዞኑን አመራሮች በመያዝ ወደ አርሶ አደሮች በመድረስ ዘሩን ማሰራጨቱ አግባብ እንዳልሆነ የአትክልትና ፍራፍሬ ባለሙያው ...
Read More »ኢትዮጵያ በጅቡቲ ድንበር ወታደሮቿን ማስፈሯ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 9 ፥ 2008) ኢትዮጵያ በጎረቤት ጅቡቲ በምትዋሰንበት የደንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሯ ተገለጠ። ይኸው በኮሎኔል አመራር ስር የተሰማራው ወታደራዊ ሃይል ታዱራህ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በምትገኘው የባልሆ ከተማ የሰፈረ ሲሆን፣ የወታደሮቹ ቁጥር በትንሹ 150 እንደሚደርስ በደህንነት ዙሪያ ሪፖርቶችን የሚያቀርበው አፍሪካ ኢንተሊጀንስ አርብ ዘግቧል። በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ አለመረጋጋትን እያሳየ እንደመጣ ያወሳው የደህንነት ተቋሙ ወታደሮቹ መሰማራት በተጠርጣሪ ታጣቂዎች ...
Read More »በድሬዳዋ ሶስት የጦር ሄሊኮፕተሮች መውደማቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 9 ፥ 2008) በቅርቡ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ በዝግጅት ላይ በነበሩ ሄሊኮፕተሮች ላይ በደረሰ አደጋ፣ ሶስቱ ከጥቅም ውጭም መሆናቸውን የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች ገለጹ። አደጋው የተከሰተው በድሬዳዋ አየር ምድብ ሲሆን፣ ለአደጋው መንስዔ ሆነ የተገኙት ሌ/ኮሎኔል ፀጋዘዓብ ካሳ የተባሉ አብራሪ መሆናቸውም ታውቋል። ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓም በኢትዮጵያ አየር ሃይል የድሬዳዋ ምድብ ውስጥ ሄሊኮፕተርን በመሬት ላይ ...
Read More »በዛምቢያ የ19 ኢትዮጵያውያን ህይወት አለፈ
ኢሳት (ሰኔ 9 ፥ 2008) የዛምቢያ መንግስት በዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪ (ኮንቴይነት) ከሃገሪቱ ወደ ጎረቤት ኮንጎ በማቅናት ከነበሩ 73 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን መካከል 19 ህይወታቸው ማለፉን አርብ አስታወቀ። የዛምቢያ ሰሌዳ ቁጥርን በለጠፉ ተሽከርካሪ ይጓዙ የነበሩት ኢትዮጵያውያን በድንበር አካባቢ ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ በማሰማታቸው የኮንጎ የድንበር ተቆጣጣሪዎች ተሽከርካሪውን አስቁመው አደጋው ሊረጋገጥ መቻሉን የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። የዕቃ መጫኛ ተሽከርካሪው አሳና ጥራጥሬዎችን ጭኖ በመጓዝ ...
Read More »ህወሃት ቁልፍ ዲፕሎማሲ ስልጣኖችን በራሱ አባላት እየሞላ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 9 ፥ 2008) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃት አባላትን ወደ ቁልፍ ዲፕሎማሲያዊ ስፍራዎች የማሸጋገሩ እርምጃ መቀጠሉ ታወቀ። የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አባል የሆኑት ዶ/ር ኃ/ሚካዔል አበራ በብሪታኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ ሌላው የህወሃት አባል አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማሪያም በአቶ ግርማ ብሩ ምርት በዋሺንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እንደሚላኩ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ፕሬዚደንት ለረጅም አመታት ያገለገሉትና ...
Read More »