ዩጋንዳ ሰራዊቷን ከሶማሊያ ልታስወጣ ነው

ሰኔ ፲፮ (አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ካቱምባ ዋማላ በሶማሊያ ያለው ሁኔታ መሻሻል አላሳየም በሚል ሰራዊታቸውን በታህሳስ ወር እንደሚያስወጡ ገልጸዋል። የሶማሊያ ወታደሮች የአገሪቱን ጸጥታ ይቆጣጠራሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ አለመሳካቱን ጄኔራሉ ገልጸዋል። ለሶማሊያ ወታደሮች ስልጠና የሚሰጡት አሜሪካ፣ እንግሊዝና ቱርክ ስራቸውን በቅንጅት አይሰሩም በማለት ጄኔራሉ ትችት ያቀረቡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ በሰላም አስከባሪ ስም የተሰማሩት ሃይሎች በቅንጅት ...

Read More »

ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተመለከተ ለእንግሊዝ መንግስት ስትሰጥ የነበረው መረጃ የተሳሳተ እንደነበር ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ለብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ እንደነበር ዛሬ ረቡዕ የወጣ መረጃ አመለከተ። ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አንዳርጋቸው ጽጌን ለመርዳት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የብሪታኒያ ባለስልጣናትን ላይ እንቅፋት ሆኖ እንደቆየና፣ በሰውየው መለቀቅ ጉዳይ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አጋልጧል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ...

Read More »

በኮንሶ አዲስ ውጥረት መንገሱ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) በደቡብ ክልል ኮንሶ ወረዳ በቅርቡ ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር የተነሳው ተቃውሞ ዳግም ቀጥሎ በትንሹ አንድ ነዋሪ መገደሉንና በወረዳዋ አዲስ ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ነዋሪዎች በወረዳዋ ሰፍረው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን እያሰሩ እንደሆነ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የጸጥታ ሃይሎች በወረዳዋ ዳግም መውሰድ የጀመሩትን ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበረችው ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንቦት ሰባት ተቀላቀለች

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ቤት አባል የነበረችው ወጣት ሜሮን አለማየሁ በረሃ ወርዳ አርበኞች ግንቦት ሰባት መቀላቀሏን አስታወቀች። ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓም ለንቅናቄው ልሳን በሰጠችው ቃለ-ምልልስ እንዳስታወቀችው በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን የሚለው ፅኑ እምነቷ በመክሸፉ መሳሪያ ለማንሳት መገደዷን ገልጻለች። የኢትዮጵያን በአሲስ ታጣቂዎች የደረሰባቸውን ግድያ በማውገዝ በተጠራው ሰልፍ ላይ መንግስት መወገዙን ተከትሎ ወደ እስር ቤት ...

Read More »

በአዳማ ወረዳ በፈነዳ ቦምብ 6 ህጻናት ቆሰሉ

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል አዳማ ወረዳ ውስጥ በፈነዳ ቦምብ 6 ህጻናት መቁሰላቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ማክሰኞ ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ዋቄ ሚኡ ቀበሌ ውስጥ በፈነዳት ቦምብ ሰለባ የሆኑት ዕድሚያቸው ከ 5 አመት እስከ 17 አመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናትና ታዳጊዎች መሆናቸውም ተመልክቷል። ያረጁና የተበላሹ ብረታብረትና መሰል ነገሮችን ለሚገዙትና ...

Read More »

ኢትዮጵያና ኬንያ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008) ኢትዮጵያና ኬንያ በሶማሊያ አሰማርተው ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተቀናጅቶ በሚሰራበት ጉዳይ ዙሪያ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በኬንያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ በመምከር ላይ መሆናቸው የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገ አንድ የደህንነት ተቋም የሁለቱ ሃገራት ወታደሮች በሶማሊያ ባላቸው ተልዕኮ ተቀናጅተው ባለመስራታቸው ምክንያት በአልሻባብ ታጣቂ ሃይል ላይ ሲካሄድ የቆየው ዘመቻ ውጤት ሳያመጣ መቅረቱን መግለጹ ይታወሳል። ...

Read More »

የመከላከያ መሃንዲሶችና  መምህሮቻቸው ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምቱ መደረጉን ተቃወሙ

ሰኔ ፲፭ (አሥራ  አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሜ/ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅና በደብረዘይት ወታደራዊ ምህንድስ ክፍል ውስጥ  ሲሰሩ የነበሩ በርካታ ወታደራዊ መሃንዲሶች፣ የጥገና ሰራተኞች እና መምህራን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ከመነሳቱ ከ2 ሳምንት በፊት ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ድንበር መላካቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ሰራተኞቹ “ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማያውቅ ነው” በማለት ወደ ግንባር መላካቸውን ቢቃወሙም፣ የሚሰማቸው አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ከሁለቱ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ብቻ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ ከተማን እንደገና መቆጣጠራቸው ተሰማ

ሰኔ ፲፭ (አሥራ  አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰኔ 13 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በኮንሶ የሚታየው ውጥረት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በሁዋላ 4 ነዋሪዎችን አፍነው መውሰዳቸው ታውቋል። ይህንን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞ ያስነሳ ሲሆን፣ ወታደሮቹ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡበ አሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ...

Read More »

የተቀናሽ ሰራዊት አባላት በረንዳ ላይ እያደሩ መሆኑን ተናገሩ

ሰኔ ፲፭ (አሥራ  አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሌሎች አገር ዜጎች ለተቀናሽ የሰራዊት አባላት ተገቢውን እንክብካቤ ሲያደርጉ፣ በኢትዮጵያ ግን ማረፊያ ጎጆ እንኳን በማጣታቸው በረንዳ ላይ እየተጣሉ መሆኑን የተቀናሽ ሰራዊት አባላት ተናግረዋል። በባህርዳር በርካታ የተቀናሽ ሰራዊት አባላት ያሉ ሲሆን ብዙዎቹ በረንዳ ላይ ያድራሉ። “ሰራዊቱ አካሉን አጥቶና ተጎድቶ እያለ” መኖሪያ ቤት እንኳን ማግኘት አልቻለም የሚሉት የተቀናሽ ሰራዊት አባላት፣ አቤቱታቸውን የሚሰማላቸው ...

Read More »

በአውስትራሊያ የአቶ አባይ ወልዱን ጠባቂ የመታው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

ሰኔ ፲፭ (አሥራ  አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በታስማኒያ ሆባርት ከተማ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ለመስራት በሄዱት በትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ ጠባቂ ላይ ድብደባ አድርሰሃል በሚል አንድ ወጣት መከሰሱን ሄራልድ ሰን የተባለው የአገሪቱ ጋዜጣ መዘገቡን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት ፣ ወጣቱ ላይ ክስ የመሰረተው የሶማሊያ ዜግነት ያለው አብዱ ባራክ አብዲ   የተባለ የአቶ አባይ ወልዱ ጠባቂ ሲሆን፣ ፍርድ ...

Read More »