ሰኔ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም በሚከበረው በአል ላይ መምህራን በግዳጅ በቦታው ተገኝተው እንዲያከብሩ ታዘዋል። የመምራን ነጻነት ባልተከበረበት ሁኔታ፣ የመምህራንን ቀን ማክበሩ ትርጉም የለውም በሚል ተቃውሞ ያነሱ መምህራን “ ትታሰራላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል። መንግስት ከመምህራን ሊደርስበት የሚችለውን ተቃውሞ በመፍራት ሰሞኑን የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ጭማሪው መታወጁን ተከትሎ በቤት ኪራይና በእቃዎች ላይ ዋጋ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የስደተኞችን መጠለያ ጠባቂ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ካምፓቸውን ጥለው በመሸሻቸው 40 ሰዎች ተገደሉ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) በደቡብ ሱዳን የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን በመጠበቅ ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስደተኞቹ በታጣቂዎች ሲጠቁ ካምፑን ጥለው መሄዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪ ቡድን አጋለጠ። የሩዋንዳ ወታደሮችም ስደተኞቹን ለመታደግ ያልተገባ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተመልክቷል። ይሕም ለ40 ሰዎች መገደልና ለ20ሺ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። አልጀዚራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ድርጊቱ የተፈጽመው በዚህ በፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ በየካቲት 2016 ...
Read More »በአማራ ክልል በርካታ ዞኖች ነዋሪዎች ከምግብ እጥረትና የተነሳ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለመመገብ መገደዳቸውን ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) ድርቅ ጉዳት እያደረሰ ባለባቸው የአማራ ክልል በርካታ ዞኖች ነዋሪዎች ከምግብ እጥረትና አቅርቦት የተነሳ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለመመገብ መገደዳቸውንና ህጻናት ክፉኛ እየተጎዱ መሆኑ ተገለጠ። በሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና የአራት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ እህተ አሻግሬ ከምግብ እጥረት የተነሳ የነበራቸው ክብደት ወደ 40 ኪሎግራም መቀነሱንና ልጆቻቸም የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ለጀርመን የዜና አገልግሎት አስረድተዋል። የሚቀርብላቸው የምግብ ...
Read More »የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ እየተባባሰ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተቀሰቀሰውን የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ መባባስን ተከትሎ ለጊዜያዊ የህክምና መስጫ የተቋቋሙ ጣቢያዎች ወደ 24 ከፍ እንዲሉ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል የከተማዋ ነዋሪዎች ለማንኛውም አገልግሎት የሚጠቀሙትን ውሃ አፍልተው እንዲጠቀሙ ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታን ለማከም የህክምና ሰርቲፊኬት በሌላቸው የህክምና ተቋማት በበሽታው የተያዙ ...
Read More »ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የነዳጅ ክምችት ማግኘቷን ተከትሎ ከፍተኛ ወታደራዊ ቁጥጥር ልትዘረጋ ነው
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ የነዳጅ ክምችት ማግኘቷን ተከትሎ በድንበሩ አካባቢ ከፍተኛ ወታደራዊ ቁጥጥር ልትዘረጋ መሆናን ሃሙስ ይፋ አደረገች። በድንበሩ አቅራቢያ የሚገኘው የሃገሪቱ የቱርካና ግዛት በኢትዮጵያ ወታደሮች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎችን ለማደን በሚል ተደጋጋሚ ጥቃት ሲካሄድበት መቆየቱ ይታወሳል። በዚሁ በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያ ወታደሮች ሲፈጸሙ የነበሩ ድንበርን የመጣስ ድርጊት በኬንያና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድ ድርድር ...
Read More »ከሃላፊነታቸው በለቀቁት ዳኞች ምትክ አዲስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንቶች ተሾሙ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) በቅርቡ ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው በለቀቁት በአቶ ተገኔ ጌታነህ ምትክ አዲስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ተሾመ። የህወሃት ታጋይ በነበሩ ምክትል ፕሬዚደንት በአቶ መድህን ኪሮስ ምትክ ደግሞ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ የነበሩ ሃሙስ ሰኔ 16 ፥ 2008 በፓርላማ ተሾመዋል። አቶ ተገኔ ጌታነህ ተክተው የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙት በጠቅላይ ፍ/ቤት በዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ዳኜ መላኩ ሲሆኑ፣ አቶ ...
Read More »ከቡና ሊገኝ የታሰበው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ140 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ አስመዘገበ
ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008) በተያዘው የኢትዮጵያ 2008 በጀት አመት ከአለም አቀፍ የቡና ንግድ ሊገኝ የታሰበው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ140 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ አስመዘገበ። በተያዘው የፈረንጆች አመት በአለም አቀፍ ደረጃ የታየው የቡና ዋጋ መቀነስ የኢትዮጵያ የቡና ንግድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳሰሩን የንግድ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። በአለም አቀፍ ደረጃ የታየውን የዋጋ መቀነስ ተከትሎ በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅትች ቡናን ...
Read More »በሊቦከምከም ወረዳ አንድ ታጣቂ 6 ፖሊሶችን ገደለ
ሰኔ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሊቦ ከምከም ወረዳ በደንጎሎ ቀበሌ አቶ አረጋ የተባለ ግለሰብ፣ እጁን ለመያዝ የሄዱትን 6 የፖሊስ አባላትን ገድሎ አንድ ስናይፐት ጠመንጃ መማረኩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። የፖሊስ አባላት በደረሳቸው መረጃ መሰረት እጁን ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ፣ ታጣቂውም አስቀድሞ በደረሰው መረጃ መሰረት ራሱን አዘጋጅቶ በመጠበቅ በፖሊሶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። አቶ አረጋ ጥቃቱን ካደረሰ በሁዋላ ለተወሰኑ ሰአታት ...
Read More »የወታደሮች ምልመላ እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች አዲስ የምልመላ ትእዛዝ ሰጡ
ሰኔ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለወራት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ለመመልመል የተደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ተከትሎ ድንጋጤ ውስጥ የገቡት የኢህአዴግ ከፍተኛ የደህንነት ሹሞች፣ ክልሎች ኮታቸውን እንዲያሙዋሉ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጥተዋል። ሰራዊቱን እየጣሉ የሚጠፉ ወታደሮች መበራከት እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ሙሉ ጦርነት ሊካሄድ ይችላል በሚል የወታደር ምልመላውን አጠናክሮ ለመቀጠል የተጀመረው እቅድ በአማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮምያና ሃረሪ ክልሎች ከሽፏል። በሃረር ከተማ የሁሉም ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር የነጻነት ትግሉን አቀጣጥሎታል ሲል አርበኞች ግንቦት7 ገለጸ
ሰኔ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር አባል የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለማስታወስ ባወጣው መግለጫ “ ህወሃት አንዳርጋቸው ጽጌን በእጁ ለማስገባት በአፈናው ተግባር ተባባሪ ለሆነው ለየመኑ የቀድሞ መሪ መንሱር ሃዲ መንግሥት ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቢከፍልም፣ አፈናው በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀስ እና እኔም አንዳርጋቸው ነኝ የሚሉ ታጋዮች ትግሉን እንዲቀላቀሉ እንዲሁም ወደ ...
Read More »