ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ የሚገደሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው

ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ አንድ አካባቢ በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የተጀመረው ዘመቻ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በምሽት እየታደኑ የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ነዋሪዎች እንደሚሉት ትናንት ምሽት ፌደራል ፖሊሶች አንድ ቄስ ገድለዋል። እስካሁን ለማረጋጋጥ ባንችልም ሌላም አንድ ቄስ ክፉኛ ተጎድተው በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ ነዋሪዎች ...

Read More »

በባህርዳር ከተማ ትልቁ የገበያ ስፍራ የተነሳው ቃጠሎን ተከትሎ ህዝቡ ጣቱን በመስተዳድሩ ላይ እየቀሰረ ነው

ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 22  ከሌሊቱ በ6፡00ሰዓት በባህርዳር ከተማ ትልቁ ገበያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ  የጎማ መደብሮች፣የቤት ዕቃ መሸጫዎች የባልትና ውጤት አቅራቢዎችና በርካታ የጌጣጌጥ መሸጫ  ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ የአካበቢው ህብረተሰብ  የአሁኑ ቃጠሎ ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ የገበያ ቦታዎችን አስለቅቆ ለባለሃብቱ ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ሴራ  አንድ አካል ነው ይላሉ ፡፡ ከአመታት በፊት በደሮ ...

Read More »

በናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ አደረጉ

ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሀብታሙ አያሌው እገዳው ተነስቶለት የውጪ ህክምና እንዲያግኝ በናይሮቢ-አምነስቲ ቢሮ ፊትለፊት በረሀብ አድማ ጥያቄ ሲያቀርቡ ዋሉ። ሥርዓቱ በፈጠረባቸው ጫና ለስደት የተዳረጉት እነኚህ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች  በቀድመው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ምስል የተሰራ ቲሸርት በመልበስ ፤በቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ላይ የተጣለበት ...

Read More »

አንድ የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ብድሩን መክፈል ባለመቻሉ ለጨረታ ሊቅርብ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ያስገኛል ተብሎ ከአምስት አመት በፊት ስራ የጀመረ አንድ ግዙፍ የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከመንግስት የተበደረውን ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈል ባለመቻሉ ለጨረታ ሊቅርብ መሆኑ ተገለጠ። ፋብሩካው ያጋጠመው የፋይናንስ ችግር ወደ 1ሺ 200 ለሚጠጉ ሰራተኞች ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ ኩባንያው ለውጭ ገበያ ሊያቅረብ ያሰበው ምርትም በከፍተኛ መጠን ቅናሽ ማስመዝገቡ ታውቋል። ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ...

Read More »

በኦጋዴን የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀ በመላ ኢትዮጵያ እየደረሰ የሚገኝ ወንጀል ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) በኦጋዴን የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል በመላው ኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚያሳይ እንደሆነ ተገለጸ። በኦጋዴን ህዝብ ላይ በኢህአዴግ ታጣቂዎች የተፈጸመው ወንጀል ተደብቆ የተቀመጠ እና ለመገናኛ ብዙሃን የማይነገር በመሆኑ ተመሳሳይ ወንጀሎች በኦሮሚያ፣ ጋምቤላና፣ አማራ ክልሎች ላይ መፈጸሙን የክሬት ትረስት ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ ለኢሳት ተናግረዋል። የውጭ መገናኛ ብዙሃን በእነዚህ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመዘገብ ...

Read More »

የኩዊንስ ኮሌጅ ባለቤት መንግስት ባሳደረባቸው ጫና ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ገለጹ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው ኩዊንስ ኮሌጅ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባሳደረባቸው ጫና ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ገለጹ። ኮሌጁንም ወደ ሌላ ሰው በማስተላለፍ የ25 አመት ልፋታቸው ከንቱ መቅረቱን አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምስረታ ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያ ጀምሮ ተሳታፊ መሆናቸውን የገለጹት የኩዊንስ ኮሌጅ መስራችና የቀድሞ ባለቤት አቶ ታደለ ሺበሺ ሲደረግባቸው ...

Read More »

በሶማሊያ ክልል የጃማ ዱባብ የገጠር መንደር አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) በቅርቡ በሶማሊያ ክልል በሚገኘው የጃማ ዱባብ የገጠር መንደር አካባቢ ተቀስቅሶ ለ21 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግጭት ዳግም ተቀሰቀሰ። አካባቢውን ከሶማሌላንድ ጋር በሚያዋስናት የድንበር አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት የተቀሰቀሰው ይኸው ግጭት ጎርጎር፣ አሊ ቡራሌ እና ቦዴ ድሂር በሚባሉ ሶስት የገጠር መንደሮች መዛመቱን የሶማሊላንድ ፕሬስ ሃሙስ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል። ከሁለት ቀን በፊት በሶማሊ ክልል ልዩ ሃይሎች ...

Read More »

በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ በተካሄደው ዘመቻ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ተገደሉ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በላፍቶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ ናቸው ያላቸውን የመኖሪያ ቤቶች ለማፍረስ እያካሄደ ባለው ዘመቻ ሃሙስ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ። በዚሁ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሃና ፋሪ ተብሎ በሚጠራው በዚሁ አካባቢ እየተካሄደ ባለው የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ቁጥራቸው በአግባቡ ሊታወቅ ያልቻለ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ለኢሳት አስረድተዋል። ...

Read More »

በወረዳ አንድ የቤት ማፍረስ ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ትናንት ቤታቸው የሚፈርስባቸው ዜጎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ በህዝቡ በኩል ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች እንዲሁም 2 ፖሊሶችና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ ቢገደሉም፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ወደ ጎን በማለት ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻውን ቀጥሎበታል። በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገ ሲሆን፣ ቤቶቹ ወደ ሚፈርሱባቸው አካባቢዎች መጠጋትም ሆነ ማለፍ ...

Read More »

ወታደሮችንና ከባድ ማሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ግንባር እየተጓዙ ነው

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደቡብና ከመሃል አገር የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም አዳዲስ የገቡና ነባር የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ግንባር እየተጓዙ ነው። የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪዎች በግዳጅ ወታደሮችን እንዲያመላልሱ እየተደረገ መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች፣ ከባድ መሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ በብዛት ወደ ግንባት እየተጓዙ ነው ብለዋል። ከትናንት በስቲያ ወደ ትግራይ ...

Read More »