ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በህግ-ወጥ መንገድ የዉሃ ግዛት በመጠቀም ወደ አዉሮፓ ለመጓዝ ሙከራን አድርገዋል የተባሉ ኢትዮጵያንን ጨምሮ 143 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አስታወቀ። በ24 ሰዓታት ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፀጥታ ሀይሎች በተወሰደዉ በዚሁ ዘመቻ 322 ስድተኞች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸዉን አል-አህራም የተሰኘ ጋዜጣ የግብፅ የባህር ሀይል ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። የሀገሪቱ የባህር ሀይል ሀላፊ የሆኑት ብርጋዴል ጄኔራል ...
Read More »አልሻባብ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ 10 ወታደሮች ተገደሉ
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) የሱማሌ ታጣቂ ሀይል አል-ሸባብ በደቡባዊ ምዕራብ የሞቃዲሾ አካባቢ በአንድ የሶማሊያ የጦር ማዘዣ ጣቢያ ላይ በፈፅመዉ ጥቃት በትንሹ 10 ወታደሮች ተገደሉ። ታጣቂ ቡድኑ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደዉ ቦንብ አድርሶታል በተባለዉ በዚሁ ጥቃት ቁጥራቸዉ ያልታወቁ ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን ለሰዓታት የቆየ የተክስ ልውውጥ መካሄዱን ሮተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ሰኞ ጠዋት በታችኛዉ የሸበሌ ግዛት በሚገኘዉ የላንታ ቡሮ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ200 ሰዎች በላይ ተገደሉ
ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በድቡብ ሱዳን መዲና ጁባ በመንግስትና በአማፂያን ቡድን ወታደሮች መካክል የተቀሰቀሰዉ ግጭት መባባስን ተከትሎ ከ200 በላይ ሰዎች ተገደሉ። ይኸው በመዲናይቱ ጁባ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ የሚገኘዉ ግጭት አዲሲቷን ሀገርን ወደ እርስ በርስ ጦርነት ይወስዳታል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት የኤምባሲ ሰራተኞቻቸዉን ማስወጣት ጀምረዋል። ከወራት በፊት በደቡብ ሱዳን መንግስትና በሪክ-ማቻር የሚመራዉ አማፂ ቡድን የጋራ ብሔራዊ መንግስት ...
Read More »በፈተና ስም ማህበራዊ ሚዲያው አፈና ተካሄደበት
ሐምሌ ፬( አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ የፌስ ቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም እና ቫይበር የመልክት መለዋወጫ ዘዴዎች የተዘጉ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ እርምጃውን የወሰድኩት የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተና እንዲፈተኑ ለማስቻል ነው ብሎአል። ይሁን እንጅ እርምጃው በአገሪቱ ውስጥ እየተባባሰ ከመጣው የፖለቲካ ቀውስ ጋር እየተያያዘ ነው። ገዢው ፓርቲ ለፈተና በሚል አለማቀፍ ገጽታውን አያበላሽም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ ምክንያቱ ...
Read More »በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ 44 የመድረክ አባላት አርሶአደሮች ታሰሩ
ሐምሌ ፬( አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ አርሶአደሮቹ የታሰሩት ማዳበሪያ አንወስድም ብለዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው ነው ። ከታሰሩ 10ኛ ቀናቸውን የያዙት አርሶአደሮች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ከታሰሩትም መካከል የ80 ዓመት አዛውንትም ይገኙበታል። የአካባቢው የመድረክ ተወካይ እንደገለጹት አርሶአደሮቹ ማዳበሪያውን ለመውሰድ ያልፈለጉበት ምክንያት “ ተመጣጣኝ ዝናብ የለም፣ አንድ ጊዜ ከከፈልን በኋላ በተደጋጋሚ ክፍያ እንጠየቃለን ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው የማይቀርቡ ከሆነ እስረኞችን በነጻ እፈታለሁ ሲል ፍርድ ቤቱ ማስጠንቀቂያ ላከ
ሐምሌ ፬( አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘመነ ካሴ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከአመት በላይ በእስር ቤት በስቃይ ላይ የሚገኙት አቶ አሸናፊ አካሉ ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ጥላሁንና አንሙት የኔዋስ፣ በመከላከያ ምስክርነት የጠሩዋቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደቀርቡላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም፣ ቃሊቲ እስር ቤት ለማቅረብ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ለእስር ቤቱ ሃላፊዎች “ ለምን ...
Read More »የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰረቅን በተመለከተ መንግስት ማብራሪያ ባለመስጠቱ በተፈታኞቹ ላይ ችግር መፍጠሩ ተገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 1 ፥ 2008) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስገባ የመግቢያ ፈተና ተሰርቋል ተብሎ በማህበራዊ ድረገጾች መሰራጨቱ የስርዓቱን ዝርክርክነትና የአመራር ጉድለት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ። መንግስት በፈተና መሰረቅ ጉዳይ ላይ ምንም አለማለቱ በተማሪዎቹ ላይ ችግር መፍጠሩም ታውቋል። ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ፈተና በማህበራዊ ድረገጾች መሰራጨቱን ተከትሎ፣ የትምህር ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ለሁለተኛ ጊዜ አራዝሞ ሌላ ፈተና እንደሚያዘጋጅ ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ ዴቪድ ካሜሩን ለእንግሊዝ ፓርላማ ገለጹ
ኢሳት (ሃምሌ 1 ፥ 2008) የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ መንግስታቸው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለ እንደሚገኝ ለሃገራቸው ፓርላማ ገልጹ። የሃገሪቱ ፓርላማ ሰሞኑን በተለያዩ የብሪታኒያ አበይት ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ጉባዔን ባካሄደ ጊዜ ክሪስ ሎው የተባሉ የፓርላማ አባል ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከእስር ከማስፈታት ስለሚወስዷቸው እርምጃዎችን ጥያቄን አቅርበዋል። በብሪታኒያው አለም አቀፍ ማሰራጫ ...
Read More »በአዲስ አበባ ህገ-ወጥ የተባሉ የመኖሪያ አካባቢዎችን የማፍረሱ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 1 ፥ 2008) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ለሚበልጡ ነዋሪዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ህገ-ወጥ የተባሉ የመኖሪያ አካባቢዎችን የማፍረሱ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር አርብ አስታወቀ። የከተማዉ አስተዳደር ህገ-ወጥ ናቸው ያላቸዉን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ለማፈርስ ባካሄደዉ ዘመቻ 95 በመቶ የሚሆኑት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከሁለት በላይ በህገ-ውጥ መንገድ መሬት የወረሩ መሆኑን ገልጿል። በኣዲሰ አበባ ከተማ በተለያዩ ስፍራዎች ሊካሄድ ...
Read More »ደቡብና ደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ በድርቅ በድጋሚ ሊመታ ይችላል ተባለ
ኢሳት (ሃምሌ 1 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ደቡብና ደቡባዊ የምስራቅ ግዛቶች ዳግም በከፋ የድርቅ አደጋ ሊጠቁ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። በወቅታዊ የሃገሪቱ ድርቅ ዙሪያ ሪፖርቱን ያወጣው ድርጅቱ ዳግም ሊከሰት በሚችለው የድርቅ አደጋ በርካታ የአርብቶ አደር አካባቢዎች እስከቀጣዩ የፈረንጆች አመት ድረስ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል አስታውቋል። በደቡባዊ የኢትዮጵያ ግዛቶች በተያዘው የክረምት ወቅት መጣል የነበረበት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ባለመገኘቱና ሊከሰት ይችላል የተባለ የአየር ...
Read More »