ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች የኮሚቴ አባላት መታሰራቸውን ተከትሎ በጎንደር ከተማ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ፣ በደባርቅ የተደገመ ሲሆን፣ የዳባት ወረዳ ወጣቶችም ወደ ደባርቅ በመሄድ ህዝባዊ አመጽ ጀምረዋል። የወልቃይት ጠገዴን ህዝባዊ ጥያቄ ሲመሩ በመጨረሻም መሳሪያቸውን አንግበው ሲፋለሙ የተገደሉት ባለሃብቱ አቶ ሲሳይ ታከለ በጎንደር ከተማ ደማቅ የሆነ የጀግና የቀብር ስነስርዓት ከተደረገላቸው ...
Read More »በርካታ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ጎንደር እያመሩ ነው
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ህዝባዊ አመጽ ለመቆጣጠር በኦሮምያ፣ በደቡብና መሃል አዲስ አበባ ያሰፈራቸውን የአጋዚ ጦር አባላትንና ወታደሮችን ወደ ሰሜን በማጓጓዝ ላይ ይገኛል። ሰላማዊ ትግሉን በሃይል ለመጨፍለቅ የወሰነ የሚመስለው ስርዓቱ፣ በተመሳሳይ መልኩ ከታጠቁት የክልሉ ታጣቂዎች ተቃውሞ ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉ ነዋሪዎች በጎንደር የተወሰደውን እርምጃ ...
Read More »አሜሪካና እንግሊዝ ዜጎቻቸው ወደ ጎንደር እንዳይሄዱ አሳሰቡ
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተቀማጨነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሆነው የአሜሪካን ኤንባሲ አሜሪካዊያን ዜጎች ወደ ጎንደር ከተማና አካባቢው እንዳይጓዙ ጊዜያዊ የጉዞ እገዳ ጣለ። በተጨማሪም ኤንባሲው በጎንደር አካባቢ ያለው ሕዝባዊ አመጽ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ ወደ ቀጠናዎቹ እንዳይዘዋወርና በአሁኑ ወቅትም በስፍራው ያሉ ዜጎች እራሳቸውን እንዲጠብቁም ሲል ጥሪውን አቅርቧል። የእንግሊዝ ኤንባሲም በበኩሉ በጎንደር ያለው ...
Read More »የማላዊ ፕሬዚደንት የክብር ዶክትሬታቸውን ለመቀበል ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ የመንግስትን ገንዘብ አባክነዋል ተባለ
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) ባሳለፍነው እሁድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የተቀበሉት የማላዊ ፕሬዚደንት ፒተር ሙታሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ የመንግስትን ገንዘብ አባክነዋል ተብለው ከፍተኛ ተቃውሞ ቀረበባቸው። ባለፈው ዕሁድ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት ፕሬዚደንቱ ለጉዞአቸው አንድ የደቡብ አፍሪካ የግል አውሮፕላንን እንደተከራዩና ከፍተኛ የመንግስት ገንዘብ አባክነዋል ተብለው ተቃውሞ እየቀረበባቸው መሆኑን የሃገሪቱ ኒያሳ ታይምስ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ፕሬዚደንቱ የክብር ዶክትሬት ...
Read More »የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ያሰማራው የሰላም አስከባሪ ሃይሉ ከአራት አመት በኋላ እንደሚያስወጣ አስታወቀ
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከ20 ሺ በላይ የሰላም አስከባሪ ሀይል በሶማሊያ አሰማርቶ የሚገኘዉ የአፍሪካ ህብረት በቀጣዮቹ አራት አመታት ከሶማሊያ ጠቅልሎ እንደሚወጣ ይፋ አደረገ። በጉዳዩ ዙሪያ ሰሞኑን ልዩ ጉባዔን ያካሄደዉ የህብረቱ የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት ከቀጣዩ ሁለት አመታት ጀምሮ የፀጥታና የደህንነት ሀላፊነቶች ለሱማሊያ እንዲተላለፍ ውሳኔ መድረሱን እንደገለፀ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አስከባሪዉ ሀይሉ ...
Read More »ህወሃት በአማራ ክልል የሚኖሩ አባላት የጥንቃቄ ዕርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አስተላለፈ
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በአማራ ክልል ለሚኖሩ የህወሃት አባላት በተለይም በንግድ ስራ ለተሰማሩት ግለሰቦች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ማስተላለፉ ታወቀ። የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት የሆኑት በንግድ ስራ የተሰማሩ በአማራ ክልል የሚኖሩ ግለሰቦች በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ እንዲሁም በእጃቸው የሚገኙ ጥሬ ገንዘቦችን ወደ ባንክ እንዲያስገቡና ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል። ከጎንደር ባሻገር ...
Read More »አርበኞች ግንቦት 7 ለጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) አርበኞች ግንቦት 7 መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በምስልና ድምፅ ከኤርትራ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት የአማራም ህዝብ ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን በተመለከተ በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ በህወሃት በኩል የሃይል ምላሽ መሰጠቱ ...
Read More »ኢትዮጵያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በተመለከተ ከኬንያ ጋር የተፈራረምኩት ስምምነት የለም አለች
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) የኬንያ መንግስት ባለፈዉ ሳምንት ከኢትዮጵያ ጋር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ስምምነት መፈረሙን ቢገልፅም ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር የተደረሰ ስምምነት የለም ስትል ማስተባበሏን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። ከኢትዮጵያ በኩል የተሰጠዉ ይኸዉ ማስተባበያ የኬንያ መንግስት ይፋ ካደረገዉ መግለጫ ጋር የሚጋጭ መሆኑን ዴይሊ ኔሽን የተሰኘ የኬንያ ጋዜጣ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት በኬንያ ጉብኝት ባደረጉበት ...
Read More »የማህበራዊ ሚዲያ መዘጋት አለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ስራ ማስተጓጎሉ ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 6 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት የማህበራዊ ድረ-ገጾች መዝጋቱን ተከትሎ የንግድ ድርጅቶች፣ የጋዜጠኞች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት፣ የኢምባሲዎችና የኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ስራ መስተጓጎሉ ተነገረ። ይህ በኢትዮጵያ መንግስት የተደረገው የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መዘጋት፣ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እስኪጨርሱ ድረስ ብቻ የሚቆይ ነው ቢባልም፣ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መዘጋት በእያንዳንዱ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ለማወቅ ተችሏል። የግል ንግድ ድርጅቶች፣ የግል ...
Read More »በጎንደር የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ሲካሄድ ዋለ
ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ የኮሚቴ አባላትን ለመያዝ የህወሃት የደህንነት አባላት ጎንደር ከገቡ በሁዋላ፣ ከኮሚቴ አባላቱ መካከል አንዱ የሆኑት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እጄን አልሰጥም ማለታቸውን ተከትሎ፣ ኮሎኔሉን ለመያዝ በመጡት የህወሃት የደህንነት አባላትና በህዝቡ መካከል ተቃውሞ ተነስቷል። ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ከነዋሪዎችም ከመንግስት ታጣቂዎችም በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። የገዢው ፓርቲ ...
Read More »