ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) ከአንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶች ቅሬታ ሲቀርብለት የቆየው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ሀገሪቱን ከአንድ ወር በኋላ በብራዚል የሪዮ ኦሎምፒክ የሚወክሉ 43 አትሌቶችን መረጠ። ተቃውሞን አስነስቶ በነበረው የማራቶን ዉድድር ዘርፍ በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ ፣ ተስፋዬ ብርሃኑ፣ እና ተስፋዬ አበራ የተመረጡ ሲሆን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ዴሲሳ በተጠባባቂነት ተይዘዋል። በማራቶን ውድድር በመጀመሪያዉ ዙር በተጠባባቂነት ተይዞ የነበረዉና ተቃዉሞን ሲያቀርብ የቆየዉ አትሌት ...
Read More »የአባይ ግድብ ጉዳይ በወታደራዊ እርምጃ ብቻ የሚፈታ ነው ሲሉ የግብፅ የመከላከያና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚቴና የፓርላማ አባል ተናገሩ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) በግብፅ ፓርላማ የመከላከያና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚቴና የፓርላማ አባል ሃገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ግድብ ዙሪያ ያላትን ልዩነት በወታደራዊ እርምጃ ብቻ የሚፈታ ነው ሲሉ ማሳሰባቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። የፓርላማ አባሉ አህመድ ኢስማዔል የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትኒያሁ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የአባይ ወንዝ በተዘዋዋሪነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል። በግብፅ ፓርላማ የሃገሪቱን የመከላከያና የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ...
Read More »ኢትዮጵያውያንን በግጭት ከምትታመሰው ደቡብ ሱዳን የማውጣት ስራ ባለመጀመሩ ለአደጋ መጋለጣቸው ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) በደቡብ ሱዳን ባለፈዉ ሳምንት ያገረሸዉን ግጭት ተከትሎ ሐገራት ዜጎቻቸውን ማዉጣት ጀመሩ። ሆኖም ኢትዮጵያዉንን የማዉጣት እንቅስቃሴ ባለመጀመሩ ለአደጋ መጋለጣቸዉን ጁባ የሚገኙ ኢትዮጵያውን ለኢሳት ገልፀዋል ። የደቡብ ሱዳን የነፃነት በዓል በሚከበርበት ወቅት ያገረሸው ግጭት እየተስፋፋ መሄድን ተከትሎ አሜሪካና የአዉሮፓ ሀገራት ዜጎቻቸዉን ማዉጣት የጀመሩ ሲሆን ፣ ኬንያና ኡጋንዳ በተመሳሳይ ዜጎቻቸዉን በማጓጓዝ ላይ መሆናቸዉን መረዳት ትችሏል። በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በሳንጃ፣ በዳባት ፣ በደባርቅ እና በሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአምባጊዮርጊስ ከተማ ዛሬ ጠዋት ህዝባዊ አመጽ የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ ወታደሮች ሃይል ተጠቅመው ለማፈን ሞክረዋል። ይሁን እንጅ ውጥረቱ አሁንም ቀጥሎአል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በጎንደር ከተማ እና በአካባቢው የተሰማራ ...
Read More »በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለው የርሃብ አደጋ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ኦክስፋም አስታወቀ
ሐምሌ ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ኦክስፋምን ገልጾ፣ ባለፈው ዓመት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ሰብልቻቸው የወደሙባቸው አርሶአደሮችና የቤት እንስሶቻቸው ያለቁባቸው አርብቶ አደሮች ምጽዋት ጠባቂ ሆነዋል ብሎአል። ከድሬደዋ 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፊዲቶ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት 10ሽህ በላይ ተረጅዎች ሲኖሩ የርሃቡ ተጠቂዎች ውስጥ ሕጻናት መኖራቸውንና በተመጣጠነ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ድጋሚ ባገረሸው የእርስበርስ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል
ሐምሌ ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ የውጭ አገር ዜጎች በየአገሮቻቸው ኢምባሲ አማካኝነት አገሪቱን ለቀው በመውጣት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ግን ተመሳሳይ እርዳታ ባለማግኘታቸው ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ ወድቋል። የአውሮፓ ሕብረት አገራት ዜጎችን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት በተለይም ጎረቤት ኡጋንዳና ኬንያ ወታደሮቻቸውን ወደ ደቡብ ሱዳን በመላክ ዜጎቻቸውን ከጥቃት በመከላከል ወደ አገራቸው እየመለሱ ነው። ድጋሜ ...
Read More »በርካታ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በእስር ላይ እንደሚገኙ ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 7 ፥ 2008) በተለያዩ የምዕራብና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ቁጥራችዉ በትክክል ሊታወቅ ያልቻለ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ መሆናቸውንና በርካታ ወጣቶች ከሀገሪቱ በመሰደድ ላይ እንደሚገኙ የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) ሐሙስ አስታወቀ ። ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ በተለያዩ 10 የአፍሪካ ሀገራት ለዚሁ ችግር ተጋለጠዉ የነበሩ 1ሺ 657 ኢትዮጵያዉያንን ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደቻለም ድርጅቱ ገልጿል። የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ስደተኞቹን ...
Read More »የተለያዩ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደጎንደር ከተማና አካባቢው በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰቡ
ኢሳት (ሃምሌ 7 ፥ 2008) የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎቻቸዉ ወደ ጎንደር ከተማ እና አካባቢዉ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳሰቡ። አዲስ አበባ የሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲዉ ባልደረቦች ወደ ጎንደር ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜዉ እንዲያቋርጡ ያሳሰበ ሲሆን ዜጎቹም ወደ ጎንደር ከተማ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃን እንዲያደርጉ ባሰራጭው መልእክት አመልክቷል። አሜሪካዊያን ወደ ስፍራዉ ለሚያደርጉት የጉዞ ጥንቃቄ በተጨማሪ ላማንኛዉም ህዝባዊ ...
Read More »ለቤተ-እስራዔላውያን የበጎ አገልግሎትን ሲሰጡ የነበሩ ድርጅቶች በጎንደር አየር ማረፊያ እንዲጠለሉ ተደረገ
ኢሳት (ሃምሌ 7 ፥ 2008) ሰሞኑን በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የእስራዔል መንግስት በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ የበጎ አገልግሎት አባላትን ወደ አየር ማረፊያ ማስጠለሉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። የእስራዔል የበጎ አገልግሎት አባላት በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ የቤተ-እስራዔላውያን የተለያዩ አገልግሎትን ሲሰጡ የነበሩ እንደሆነ ታውቋል። ይሁንና ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት ለበጎ አገልግሎት አባላቱ ስጋት እየሆነ በመምጣቱ የእስራዔል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ...
Read More »በጎንደር የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 7 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ሐሙስ ወደ ደባርቅ ከተማና ዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ ። ሰሞኑን በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች የተገደሉ ሰዎችን ሐሙስ የቀብር ስነ-ስርአት ቢካሄድም ስነ-ስርአቱ ወደ ተቃዉሞ መቀየሩንና ነዋሪዎች ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሐት)ን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ መዋላቸዉ ታዉቋል። በከተማዋ የተሰማራ የፀጥታ ሀይሎች ተቃዉሞዉን ለመበተን አስለቃሽ ጢስን መጠቀም ...
Read More »