ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) መብታቸውን በጠየቁ የወልቃይት ተወላጆች ላይ የተወሰደውን ዕርምጃ እንደሚያወግዝ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ዓለም አቀፍ ቡድን አስታወቀ። የኦፌኮ አለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሃምሌ 10 ፥ 2008 ባወጣው መግለጫ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ለመብቱ የሚያደርገውን ትግል እንዲያቀናጅም ጥሪ አቅርቧል። “በጎንደር የተወሰደው የሃይል ዕርምጃ እና የተከሰተውን ቀውስ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፣ “የማንነት ጥያቄ ይሁን ሌላ የመብት ጥያቄ ...
Read More »በጎንደር በሚደረገው በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ተቃውሞ ይቀሰቀሳል በሚል ተጨማሪ መከላከያ ሃይል መሰማራቱ ተነገረ
ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) ረቡዕ ዕለት በጎንደር ከተማ ይካሄዳል የተባለውን የእግር ኳስ ጨዋታ ተከትሎ ተጨማሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ጎንደር ከተማ መግባታቸው ታወቀ። የአማራ ክልል የአካባቢ ሚሊሺያዎች መሳሪያቸውን ይዘው በቤታቸው እንዲወሰኑም መመሪያ መውረዱን ከጎንደር ለኢሳት የደረሰው ዜና ያስረዳል። ረቡዕ ሃምሌ 13 ፥ 2008 ዓም በጎንደር ስታዲያም በኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና በፋሲል ከነማ መካከል ሊካሄድ መርሃ ግብር የተያዘለት ፕሮግራም ህዝባዊ ቁጣ ...
Read More »በአሰቦት ከ30 በላይ ሰዎች ታሰሩ
ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሃረርጌ ዞን በሚገኘው አሰቦት ከተማ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአንድ ነዋሪ ላይ በፈጸሙት ድብደባ ተቃውሞን ቀስቅሶ በትንሹ 30 ሰዎች መታሰራቸውንና ድርጊቱ በአካባቢው ውጥረት ማንገሱን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማው ከንቲባ ላይ ያላቸውን ተቃውሞና ቅሬታ ማክሰኞ መግለጽ በጀመሩበት ጊዜ የጸጥታ ሃይሎች አንድ ነዋሪን በጠመንጃ ስለት (ሳንጃ) ጭንቅላቱን እንደወጉትና ድርጊቱን ተጨማሪ ተቃውሞ መቀስቀሱን እማኞች ...
Read More »በምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት የተኩስ ዕርምጃ በትንሹ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን እማኞች ለኢሳት መግለጻቸው ይታወሳል። ይኸው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በትክክል ሊታወቅ ያልቻለ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
Read More »የኮሌራ ወረርሽኝ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ነው ተባለ
ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ ስርጭቱ በተለያዩ የመዲናይቱ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታወቀ። የበሽታው ስርጭት መባባስን ተከትሎ በየክፍለ ከተማው ተቋቁመው የነበሩ ጊዜያዊ የህክምና መስጫ ተቋማት በእጥፍ እንዲያድጉ ተደርጎ 26 መድረሳቸው ታውቋል። በመጣል ላይ ያለው ዝናብ እስከ ነሃሴ ወር ድረስ ቀጣይ በመሆኑ የበሽታው ስርጭት እየጨመረ ሊሄድ ...
Read More »ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከህዝቡ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተባለ
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት እንደገለጹት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ በአጠቃላይ የታሰሩትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ጉዳይ የሚከታተሉ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ኮሎኔሉ ወደ ትግራይ ተላልፈው እንደማይሰጡ እንዲሁም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ኮሎኔሉና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት ለሽማግሌዎች ተመልሰው እንደሚሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ኮሎኔሉ ራሳቸው ሽማግሌዎች በተስማሙት መሰረት ስምምነቱ ...
Read More »በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የሚካሄዱ ህዝባዊ አመጾች እንደቀጠሉ ናቸው
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ በጃዊ ቦኒ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ከተለያዩ የገጠር አካባቢዎች የተሰባሰቡ ነዋሪዎች መንገዶችን በመዝጋት እና ገዢውን ፓርቲ የሚያወግዙ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞ እያደረጉ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ 5 ሰዎች ቆስለዋል። በምእራብ ሃረርጌ አሰቦት ወረዳም እንዲሁ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ ተቀጣጥሎአል። ትናንት የጊንጪ ጀልዱ ግንደበረት መንገድ ...
Read More »ዓለም የኢትዮጵያን ርሃብ ችላ ሊለው አይገባም ሲል ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ጥሪውን አቀረበ
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምግብ እጦት ችግር ምክንያት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ግብረሰናይ ድርጅቶች በጋራ በመተባበር አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ሊያቀርብላቸው ይገባል ሲል የኦሎምፒክ ባለድሉ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተማጽኖውን አሰማ። ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቀው የኢትዮጵያ ድርቅ ተጠቂ የሆኑና አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች 10.2 ...
Read More »አቶ ሃብታሙ አያሌው ከሕክምና ቦርድ ማረጋገጫ ቢያገኝም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀረ
ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ሕመም የሚሰቃየው አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመታከም የሚያስችለውን ተጨማሪ የሕክምና መረጃ ቦርድ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከተሰጠ በሁዋላ፣ የሕክምና ቦርድ አባላት የፈረሙበትና ታማሚው በግድ ወደ ውጭ ወጥቶ መታከም እንዳለበት የሚያረጋገጥ ማስረጃውን ይዞ ቢቀርብም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አልተሰየሙም በሚል ምክንያት ቀጠሮዎችን በማጓተት ፍርድ ቤቱ ...
Read More »የጸጥታ አካላት በጎንደር ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግድያና አፈና በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተደረገ
ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማና አካባቢዋ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ጥያቄን ባቀረቡ ነዋሪዎች ላይ የወሰዱትን ግድያና እስራት በመቃወም ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ። የተለያዩ መፈክሮችን ሲያስተጋቡ ያረፈዱት ሰልፈኞች መንግስት የማንነት ጥያቄን እያቀረቡ ባሉ አካላት ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። ...
Read More »