የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኒስትሮችን ሹምሽር ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን እንደሚያፀድቅ ተነገረ

ኢሳት (ሃምሌ 18 ፥ 2008) ከሁለት ሳምንት በፊት የ2008 አም የስራ ዘመኑን አጠናቆ ለእረፍት የተበተነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የሚኒስትሮችን ሹምሽር ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን ማጽደቅ እንደሚያካትት ሪፖርተር ዘገበ። ከአምስት አመት በኋላ ፓርላማው ጠርቶታል የተባለው ይኸው አስቸኳይ ስብሰባ ሶስት አዋጆችን ያጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በተወሰኑ ሚኒስትሮች ላይ ያደረጉት ሹምሽር እንዲጸድቅላቸው እንደሚያደርጉም በሪፖርተር ...

Read More »

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ የትግራይንና የጎንደርን ህዝብ ለማፋጀት የሚደረገው ሙከራ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሃምሌ 18 ፥ 2008) በፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ የትግራይንና የጎንደርን ህዝብ ለማፋጀት የሚደረገው ሙከራ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። በኦሮሚያ ክልል በ400 ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በድጋሚ ያወገዘው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ለሃገሪቱ ችግር መፍትሄ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል። “ለሃያ አምስት ዓመት አንዱን ከሌላ ጋር በማጋጨትና በማጣላት ጊዜውን የሚያጠፋው ይህ መንግስት አሁንም በጥፋቱ ቀጥሎበት ...

Read More »

በምእራብ አርሲ ህዝባዊ አመጽ እንደገና አገረሸ

የአካባቢው ነዋሪዎች መብታችን ይከበር፣ የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ለአነሳናቸው የፍትህ ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ ይሰጠን፣ በወያኔ መተዳደር አንፈልግም የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በማንሳት ተቃውአቸውን አሰምተዋል። በዳባ፣ ዶዶላ፣ ኢዶ በሚባሉ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚገኙ መንገዶች ሙሉ በሙሉ በድንጋይ ተዘግተው ውለዋል። በተለይ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ የሚወስደው መንገድ መዘጋት መኪኖች ቀኑን ሙሉ ቆመው እንዲውሉ አድርጓቸዋል። የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ...

Read More »

በጎንደር አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው

ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ በጎንደርና አካባቢው የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ቢሆንም፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እስከ ሃምሌ 25 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ታውቋል። ህዝቡ የታሰሩ የኮሚቴው አባላት እንዲፈቱ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙትና የህዝባዊ አመጹ ማእከል የሆኑት ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ እንዲፈቱ በተቃውሞ ሰልፍ ይጠይቃል። ...

Read More »

ለጤናና ስፖርት እየተባለ ከፌደራል ፖሊስ አባላት የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲሁም የውጭ ድርጅቶች ለጥበቃ እያሉ የሚከፍሉት ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አንድ በሚስጢር የተያዘ  የምርመራ ሰነድ አመለከተ

ከሰራዊቱ የሚደርሰው ጥቆማ ለመንግስት ህልውና አደጋ እየፈጠረ መምጣቱን ተከትሎ በተደረገው ማጣራት ከፌደራል ፖሊስ አባላት ለጤና እየተባለ የሚቆረጠው ገንዘብ ከጤና ጋር ግንኙነት ለሌላቸው የህወሃት ፣ የኢህአዴግ በአላት እና ለመሳሰሉት ወጪ እንደሚደረግ በኮማንደር እሸቱ የሮማው፣ በኮማንደር አበበ ኪ.ማርያም፣ በ ኮማንደር ደጄኔ ወንድሜነህ፣ በም/ኮማንደር ደነቀው ክፍሌ እንዲሁም ም/ኢ/ር ተሾመ ጊዳ የተደረገው የምርመራ ሪፖርት ያመለክታል። እንዲሁም ኢሲኤ፣ ቻይና፣ ግለገል ጊቤ፣ ካጅማ እና ከመሳሰሉት የውጭ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉትን ሶማሊያዊያን ዜጎች ግድያን አሜሶን በአፋጣኝ እንዲያጣራ ተጠየቀ

ባለፈው ሳምንት በቤይ ግዛት ውስጥ በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉትን 14 ንጹሃን ያልታጠቁ ሶማሊያዊያን ግድያ ኢፍሃዊ ነው ሲሉ ታዋቂው የአገሪቱ የሕግ ምሁር ዳሂር አሚን ጄሰው ድርጊቱን አወገዙ። ሰላማዊ ዜጎችን በግፍ የገደሉ በሕግ ሊጠየቁ ይገባልም ሲሉ ከሸበሌ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአጽኖት ገልፀዋል። በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ስር ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወሰዱት ኢሰብዓዊ የጅምላ ግድያ ሰለባ የሆኑ ቁርዓን በመማር ላይ የነበሩ ...

Read More »

አባይ ጸሃዬ ከኤርትራ ጋር ወደጦርነት አንገባም አሉ

ኢሳት (ሃምሌ 15 ፥ 2008) ከኤርትራ ጋር ጦርነት ውስጥ እንግባ እያሉ የሚገፋፉን ጦርነቱ ውስጥ የማይገቡ፣ ሌላው እንዲሞት የሚፈልጉ ወገኖች ናቸው ሲሉ አቶ አባይ ጸሃዬ ገልጹ። የህወሃት መስራችና አሁንም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አባይ ጸሃዬ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው አይጋፎረም ጋር ሰሞኑን ባደረጉት በዚህ ቃለምልልስ ሻዕቢያም ሆነ በርሱ የሚደገፉ ሃይሎች ሲተነኩሱን አጸፋ ምላሽ እንሰጣለን፣ ከዚያ በላይ ግን ልማታችንን የሚያደናቅፍ ጦርነት ውስጥ ...

Read More »

በአቶ ሃብታሙ አያሌው ሊሰጥ የነበረውን የህክምና ጥያቄ ብይን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘመ

ኢሳት (ሃምሌ 15 ፥ 2008) የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሃገር እንዳይወጣ እገዳ ተጥሎበት ለሚገኘው አቶ ሃብታሙ አያሌው አርብ ሊሰጥ የነበረውን ብይን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘመ። የአቶ ሃብታሙ ቤተሰቦች በህክምና የቦርድ አባላት የጸደቀን እና አቶ ሃብታሙ ከሃገር ውጭ እንዲታከሙ የተላለፈን የባለሙያዎች ውሳኔ ከፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ የቀረበለትን ጥያቄ በአዲስ መልክ ለመመልከት ከቀጣዩ ሳምንት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) ዓም ተለዋጭ ቀጠሮን እንደሰጠ ከሃገር ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 15 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ እና በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሂደት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አርብ አሳሰበ። መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገውና በሃገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችን ዙሪያ ሪፖርቱን ያወጣው ፍሪደም ሃውስ፣ መንግስት በብቸኝነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቁጥጥርን ተግባራዊ ማድረጉ ተቃውሞዎች እንዲቀሰቀሱና እየተባባሱ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል። ...

Read More »

በአንድ ቀበሌ ብቻ  30 ሰዎች በኮሌራ በሽታ አረፉ

ሐምሌ  ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ወረ መነዬ ቀበሌ ካለፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ በተነሳው የኮሌራ በሽታ 30 ሰዎች ሲሞቱ 94 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘው እየታከሙ ነው። የአካባቢው ባለሙያዎች መረጃውን እንዳያወጡ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት የኢሳት ምንጮች፣ በሽታው ወደ አጎራባች አካባቢዎች እየተዛመተ መሆኑንም ተናግረዋል። በርካታ በሽተኞች ወደ ጸበል ...

Read More »