ኢህአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የቤተክርስቲያንን አንድነት መጠበቅና ዕርቅ ማውረድ አይቻልም ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) ሃገር ቤት ባሉ አባቶችና በውጭ ባሉት አባቶች መካከል ዕርቅን በማውረድ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት መጠበቅ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በቀጠለበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ መልከ-ፀዴቅ ገለጹ። በውጭ ሃገር ባለው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ዕርቅ በማውረድ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን፣ ሆኖም በመንግስት ጣልቃ-ገብነት መክሸፉን ዘርዝረዋል። በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ...

Read More »

በፈረንሳይ ስደተኞች ተጋጭተው አንድ ኢትዮጵያዊ ተገደለ፣ ሌሎች 6 ስደተኞች ቆሰሉ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) በሰሜን ፈረንሳይ አገር በካላይስ የወደብ ከተማ በስደተኞች መካከል ግጭት ተከስቶ አንድ ኢትዮጵያዊ መገደሉ ተነገረ። ሌሎች ስድስት ስደተኞች መቁሰላቸውም ለማወቅ ተችሏል። ዛሬ ማክሰኞ በተቀሰቀሰው በዚህ ግጭት ከሱዳን፣ ኤርትራና፣ ኢትዮጵያ ወደ ፈረንሳይ የገቡ ስደተኞች ከአፍጋኒስታን ከመጡ ሌሎች ስደተኞች ጋር ተጋጭተው በጩቤ እንደተወጋጉና እንዲሁም በዱላ እንደተደባደቡ አር ኤፍ አይ (RFI) የተባለ የፈረንሳይ የዜና አውታር የአካባቢው ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ...

Read More »

በማላዊ የእስር ቅጣት ያጠናቀቁ 165 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በእንግልት ላይ መሆናቸውን ተነገረ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) በህገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የእስር ቅጣት ያጠናቀቁ 165 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሃገሪቱ በእንግልት ላይ መሆናቸውን የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ማክሰኞ ገለጠ። በሃገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን ሁኔታ ለመመልከት በቅርቡ የባለሙያ ቡድንን ወደ ማላዊ ልኮ እንደነበር ያስታወቀው ድርጅቱ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ 165 ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን አስታውቋል። ...

Read More »

በአውስትራልያ ብሪዝቤን ከተማ የወልቃይትን ህዝብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ ገዢው መንግስት በህዝቡ ላይ የወሰደውንና እየወሰደ ያለውን እርምጃ የተመለከተ ውይይት ተካሄደ።

ሐምሌ  ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቅዳሜ ሃምሌ 16 2008 ዓ ም በ ኢትዮጵያውያን በተጠራው በዚህ ስብሰባ ላይ በተለይ የወልቃይት አካባቢ ተወላጆችና የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑ ነዋሪዎች የችግሩን አነሳስና ሂደት ምን እንደሚመስል በጥልቀትና በስፋት ለተሰብሳቢው ያስረዱ ሲሆን ከታሪክ እያጣቀሱና የአይን እማኝነታቸውን እያከሉ ስፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል። የአካባቢው ተወላጅ የሆኑትና ስብሰባውን ከጠሩት ኢትዮጵያውያኑ መሃከል አንዱ የሆኑት ...

Read More »

አቶ ሃብታሙ አያሌው ተጨማሪ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠው

ሐምሌ  ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ሕመም በስቃይ ላይ የሚገኘውና በ አገር ውስጥ ታክሞ መዳን እንደማይችል በሕክምና ቦርድ የተፈረመ ማረጋገጫ የተሰጠው አቶ ሃብታሙ አያሌው የተንዛዛ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ  እየተሰጠው ሕይወቱ አደጋ ላይ ይገኛል። በዛሬው እለት የሀብታሙ አያሌው የሕክምና ጉዳይ ላይ የአቃቤ ሕግን አስተያየት ለመቀበል የተሰየመው ችሎት አቃቤ ሕግ አስተያየቱን በቃል ሊያቀርብ ፈቃደኛ ቢሆንም ...

Read More »

የምእራብ አርሲ ወጣቶችን ለመያዝ የተሰማራው የአጋዚ ጦር ቤት ለቤት በመግባት አሰሳ እያደረገ ነው

ሐምሌ  ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከኮሳ፣ አሰሳና ዶዶላ አካባቢዎች ሃምሌ 18 እንደገና የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የመንግስት መስሪያ ቤት የወደመ ሲሆን፣ መንገዶችም ተዘግተው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴም ተቋርጦ ውሎአል። የፌደራል ፖሊስ አባላት መኪኖች ወደ ከተሞች መግባት ባለመቻላቸው በእግራቸው ተጉዘው ለመግባት የቻሉ ሲሆን፣ ምሽት ላይ ጥይቶችን በመተኮስ ህዝቡን ሲያሸብሩት አምሽተዋል። ዛሬ ደግሞ ቤት ለቤት እየገቡ ወጣቶችን ...

Read More »

በባህርዳር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በጎንደር በህዝቡ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተቃወሙ

ሐምሌ  ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የትግራይ ክልል የደህንነትና የፖሊስ አባላት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባላትን ለመያዝ ወደ ጎንደር በተንቀሳቀሱበት ወቅት የኮሚቴው አባል የሆኑት ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን “ ህገወጥ በሆነ መንገድ አልያዝም” በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ፣ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ 19 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ 18ት ደግሞ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከግብፅ የሚገነቡ የመድሃኒት ምርቶችን አገደች

ኢሳት (ሃምሌ 18 ፥ 2008) በመንገባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ፕሮጄክት ከግብፅ ጋር አለመግባባት ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያው ከግብፅ የሚገነቡ የመድሃኒት ምርቶችን አገደች። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በ11 ኩባንያዎች ላይ የተጣለው እገዳ የሃገሪቱን መስፈርት የማያሟሉ ሆነው ስላልተገኙ ነው ሲል ምላሽን መስጠቱን አል-ማስሪ የተሰኘ የግብፅ ጋዜጣ ዘግቧል። በቅርቡ ወደ ግብጽ በመጓዝ በ13 የሃገሪቱ የመድሃኒት አምራት ፋብሪካዎች ላይ ጉብኝትን ያደረጉ የጤና ጥበቃ ተወካዮች 11ዱ ...

Read More »

በድሬዳዋ ከተማ በወባና ዳንጊ በሽታ በርካታ ሰዎችን እንደተጠቁ ተነገረ

ኢሳት (ሃምሌ 18 ፥ 2008) በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተን የወባና የዳንጊ ትኩሳት በሽታ ተከትሎ በየዕለቱ በትንሹ ስድስት ሰዎች ወደ ህክምና መስጫ ተቋማት በመግባት ላይ መሆናቸው ተገለጠ። የክረምት ወቅቱን ተከትሎ በከተማዋና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች በመስፋፋት ላይ ያለውን የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የመከላከሉ ስራ በዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሰኞ አስታውቋል። የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር ሲባል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ 94ሺ ...

Read More »

በምዕራብ አርሲ በሚገኙ ከተሞች የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ግጭት ተለወጠ

ኢሳት (ሃምሌ 18 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ለወራት በክልሉ ከቆየው ተቃውሞ ጋር ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ግጭት መለወጡን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። በዶዶላ፣ አዳባ፣ አሳሳ፣ እና አካባቢው ከሰኞ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለውን ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ለማዋል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተኩስ ዕርምጃን እየወሰዱ እንደሚገኝ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ እማኞች ...

Read More »