መከላከያ ሰራዊት በቦረና ሚኦ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ አንድ ሰው ሲገድል ሶስት አቆሰለ

ኢሳት (ሃምሌ 20 ፥ 2008) በቦረና ዞን ሚዖ ወረዳ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በህዝብ ላይ በከፈቱት ተኩስ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአይን ምስክሮች ለኢሳት ገለጹ። ማክሰኞ ዕለት በአካባቢው የመብት ጥያቄ በአደባባይ መነሳቱን ተከትሎ ረቡዕ ከተማዋን የተቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በእርቀት ተኩስ አንዲት የመንገድ ላይ ቸርቻሪም ሰለባ መሆኑ ታውቋል። ማክሰኞ ዕለት በሚዖ ወረዳ ኩሉቡማ ከተማ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን ገልጿል ፥ ጥያቄም አቅርቧል። ...

Read More »

በኢትዮጵያ የብሊሃርዚያ በሽታ ስርጭት አሳሳቢ ነው ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 20 ፥ 2008) ኢትዮጵያ ካላት 90 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑ ህዝቦቿ ወደ 23 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆነው የብልሃርዚያ በሽታ ህክምናን የሚፈልግ እንደሆነና የበሽታው ስርጭትም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቁ። የብልሃርዚያ በሽታ በአለማችን ካልጠፋባቸው ጥቂት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር 14 ሚሊዮን ታብሌት ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዙን የአለም ጤና ድርጅትን ዋቢ በማድረግ አፍሪካ ኒውስ ማክሰኞ ዘግቧል። ...

Read More »

በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል

ኢሳት (ሃምሌ 20 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ረቡዕ መቀጠሉ ታውቋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ማክሰኞ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃን እንደሚወስድ  ማሳሰቢያን ቢሰጥም በተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ተቃውሞ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በዞኑ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና አምስት ሰዎች ዳግም ጉዳት እንደደረሰባቸው የኦሮሚያ ...

Read More »

በሃመር ወረዳ የሚኖሩ አርብቶ እና አርሶ አደር ማህበረሰቦች ለመንግስት ግብር መክፈል ማቆማቸውን ገለጹ

ኢሳት (ሃምሌ 20 ፥ 2008) በደቡብ ክልል ሃመር ወረዳ ስር የሚገኙ በርካታ አርብቶ እና አርሶ አደር ማህበረሰቦች በመንግስት አስተዳደር ላይ ተቃውሞን በማቅረብ ግብር መክፈል ማቆማቸውን የአካባቢው እማኞች ለኢሳት ገለጹ። የማህበረሰቡ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የሚያነሷቸው አስተዳደራዊ ጥያቄዎች በቂ ትኩረትና ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት ነዋሪዎቹ ግብርን ጨምሮ ከመንግስት በብድር የቀረበላቸውን የምርጥ ዘር ክፍያ ላለመክፈል መወሰናቸውን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ...

Read More »

በጎንደር የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄን ከሽብርተኝነት ጋር ያያያዙ የመንግስት አካላት ይቅርታን እንዲጠይቋቸው የጎንደር ነዋሪዎች ጠየቁ

ኢሳት (ሃምሌ 20 ፥ 2008) በቅርቡ በማራ ክልል በጎንደር ከተማ በነዋርዎች ዘንድ የተነሳው “የነጻነትና የማንነት” ጥያቄ ከሽብርተኛ ድርጊት ጋር የያያያዙ የመንግስት አካላት ይቅርታን እንዲጠይቁ የከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። በክልሉ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰሞኑን የክልሉና የብአዴን ሃላቺዎች ከነዋሪዎች ጋር ምክክርን ለማካሄድ በጠሩት ልዩ ስብሰባ ላይ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ቅሬታ እንዳቀረቡ በስብሰባው የተሳተፉ እማኞች ለኢሳት አስታውቀዋል። የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳና፣ የመንግስት ...

Read More »

በሚኦ ወረዳ የተጀመረው  ህዝባዊ ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

ሐምሌ  ፳ ( ሀያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦረና ዞን በሚኦ ወረዳ ሂዲ ሎላ ከተማ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ አንድ ሰው ሲገደል ሁለት ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች  “ሞያሌ ከተማ በሁለት ክልሎች መተዳደሩ ተገቢ ባለመሆኑ ወደ ኦሮምያ ክልል ይጠቃለል፣ ዩኒቨርስቲ ይከፈትልን፣ ፍትህ ይሰጠን፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን ይከበሩልን፣ የወያኔን የመከፋፈል ፖሊሲ እንቃወማለን፣ ይህ መንግስት አይወክለንም፣ አያስተዳድረንም “ የሚሉ እና ...

Read More »

የገዢው ፓርቲ ሹሞች በስብሰባ አዳራሽ ላይ የጠየቁትን ይቅርታ በመገናኛ ብዙሃን ለመድገም አልደፈሩም ተባለ

ሐምሌ  ፳ ( ሀያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር የተጀመረውን ህዝባዊ አመጽ  ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው የ ህወሃት /ኢህአዴግ  አመራርና ክልሉን የሚያስተዳድረው ብአዴን፣ እንቅስቃሴውን ለማብረድ ከትናንት በስቲያ ጎንደር ከተማ ውስጥ ከተወሰኑ የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባላት፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከአገር ሽምጋሌዎች ጋር ያደረገው ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል። ነባሩ የብአዴን ታጋይ እና የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ የክልሉ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የሚታየው የቆሻሻ ክምር እና ኮሌራ በነዋሪው ህዝብ ላይ ስጋት ፈጥሯል

ሐምሌ  ፳ ( ሀያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘጋቢያችን እንደገለጸው በከተማው የሚታዬው ቆሻሻ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ባለበት በዚህ ሰአት የኮሌራ በሽታ መስፋፋትና የንጹህ ውሃ አቅርቦት እጥረት መባባስ በነዋሪዎች ላይ ስጋት ደቅኗል። በኦሮምያ ልዩ ዞን በርኬ ወረዳ የሚገኙ አርሶደሮች ሰንዳፋ አካባቢ በ337 ሚሊዮን ብር የተገነባው የ ቆሻሻ መጣያ  በጤናቸው ላይ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን በመግለጽ፣ ከእንግዲህ በዚህ ...

Read More »

በኦሮምያ የክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የኦሮምያ ክልል መንግስት አስታወቀ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ዳግም ተቀስቅሶ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ማክሰኞ አስታወቀ። ዳግም ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጫን ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን እና በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ እየተካሄዱ ባሉ ተቃዋሚዎች የአንዲት ሴት ህይወት ማለፉንና አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጿል። በምዕራብ አርሲ ዞን ስር በሚገኙ ...

Read More »

ሰሞኑን በካይሮ ራሳቸውን ካቃጠሉት ሁለት ኢትዮጵያውያን መካከል የአንዷ ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008) ካይሮ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በራፍ ራሳቸውን ከአቃጠሉት ሁለት ኢትዮጵያውያን መካከል የአንደኛዋ ህይወት ማለፉ ታወቀ። ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ አስሊ ኑሬ በደረሰባቸው ቃጠሎ ተገቢውን ህክምና ሳያገኙ በመቅረታቸው ማክሰኞ ጠዋት ህይወታቸው ማለፉን ለኢሳት ከደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ ኦሮሚያ ከተካሄደው መጠነ ሰፊ ግድያ፣ ድብደባ፣ አፈናና እስራት ሸሽተው ግብጽ መድረሳቸው የተገለጸው እነዚህ ሁለት የኦሮሞ ...

Read More »