ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) ባለፈው እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበባቸው የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንትን በተመለከተ የትግራይ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ ማህበር መግለጫ አወጣ። ማህበሩ ባወጣው በዚህ መግለጫ ሻዕቢያና ትምክህተኞችን በመተባበሩ የፈጸሙት ተግባር ነው ሲሉ በትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ላይ የደረሰውን ተቃውሞ አውግዟል። ረቡዕ ሃምሌ 27, 2008 በሚጀምረው የትግራይ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ በዓል ላይ ለመገኘት እሁድ ሃምሌ 24, 2008 ...
Read More »በሱዳንና ግብፅ ድንበር 600 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) የሱዳን መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሃገሪቱ ከሊቢያ እና ከግብፅ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ 600 ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ሰኞ አስታወቁ። ሃገሪቱ በሰኔ ወር ህገወጥ የተባሉ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ልዩ የጸጥታ ሃይሏን በድንበር አካባቢ ያሰፈረች ሲሆን፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚሁ ዘመቻ እየተያዙ መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ወታደራዊ ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የሱዳን የድንበር ልዩ የጸጥታ ሃይሎች ተወካይ ...
Read More »አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ ሁለት ሃላፊዎች በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ተባሉ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) ከሶስት አመት በፊት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ለእስር የተዳረጉት የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ ሁለት ሃላፊዎች በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ተባሉ። ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚኒስትር ደረጃ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሃላፊ የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ እንዲሁም አቶ ገብረዋህድ ወደጊዮርጊስና አቶ በላቸው በየነ የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ሲል ማክሰኞ ብይን ሰጥቷል። ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ኩምቢ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ወደ 49 ሺህ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ተመድ ይፋ አድረገ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ስር በምትገኘው የኩምቢ ወረዳ በቅርቡ በተከሰተ ግጭት ወደ 49 ሺህ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አድርጓል። በአካባቢው በኦሮሚያ ክልል ለወራት የዘለቀው ተቃውሞ ዳግም ያገረሸ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ የቻሉበትን ምክንያት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁንና፣ በርካታ ህዝብ በሚኖርበት የኩምቢ ወረዳ ለቀናት ሲካሄዱ በቆዩ ግጭቶች 49ሺ አካባቢ ...
Read More »ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ተባለ
ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ በአሜሪካ አገር ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ገለጹ። ከቪኦኤ እንግሊዝኛው አገልግሎት ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉን ያማከለ ግልፅና እውነተኛ ምርጫ ካላደረገ፣ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ህልውና ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ይወድቃል ብለዋል። እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ገለጻ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያና ጎንደር የተደረጉት ተቃውሞዎች ...
Read More »“የገዢዎች እብሪት እና ግፍ ካልቆመ ከፍተኛ አደጋ ይደርሳል” ሲሉ የጎንደር ነዋሪዎች አስጠነቀቁ
ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተጻፈውና በቅጅ ለኢሳት የተላከው ደብዳቤ ፣ “ በእብሪተኛ ገዢዎች እየተፈጸመ ያለው ግፍ በሃገርና በህዝብ ላይ የደገሰውን የሞት ድግስ ከማድረሱ በፊት የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሎአል። ደብዳቤው በጎንደር ባለፈው እሁድ ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች በአፋጣኝ መልስ እንዲያገኙ ይጠይቃል። በግፍ ...
Read More »የፊታችን ቅዳሜ በመላው ኦሮምያ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል
ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄ የፈታችን ቅዳሜ በመላው ኦሮምያ አካባቢ እንደሚካሄድ ታውቋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኦሮሞ ህዝብ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ትግሉን ቢያካሂድም እያገኘ ያለው ምላሽ ግን በተቃራኒው ጥይት መሆኑ በርካታ ዜጎችን አስቆጥቷል። በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ገዢው ፓርቲ የሚያካሂደውን ግድያ እንዲያቆም፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ...
Read More »ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበት ግድብ ተደርምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት እና ፋርጣ ወረዳዎች ከ2 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የሚገነባው ርብ የመስኖ ግድብ ተደርምሶ በ60 ሰዎች እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ግድቡ በ2 ሺ ዓም የተጀመረ ሲሆን፣ በአራት አመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ከ8 አመታት በሁዋላም ግንባታው አላላቀም። ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ...
Read More »የኮሌራ በሽታ በኦሮምያ፣ አማራ እና አዲስ አበባ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው
ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በስፋት ሲታይ የነበረው የኮሌራ በሽታ በኦሮምያ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ከተሰራጨ በሁዋላ፣ ከሃምሌ 13 /2008 ዓም. ጀምሮ ደግሞ በሰሜን ሸዋ መከሰቱን ከክልሉ ጤና ቢሮ የወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡ ወደ ሰሜን ሸዋ የገባው በሽታ በመንዝ ላሉ፣መንዝ ቀያ፣መንዝ ማማ፣አሳግርት፣በረኸት፣ምንጃር ሸንኮራና ሞጃ ወረዳዎች በስፋት ተሰራጭቷል። የክልሉ መንግስት መረጃውን ይፋ ባያደርገውም በመንዝ ...
Read More »አቶ ሃብታሙ አያሌው በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው
ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ህመም የሚሰቃየው አቶ ሃብታሙ አያሌው በአገር ውስጥ ሕክምና ሊድን እንደማይችል በሐኪሞች ቦርድ የተፈረመ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ቢያቀርብም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጤናውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አፋጣኝ የሆነ የፍርድ ብያኔ ከመስጠት ይልቅ በተንዛዛ የጊዜ ቀጠሮ ውሳኔ መስጠት አልቻለም። የሃብታሙን ጉዳይ ሲያዩ የነበሩ ሁለት ዳኞች በሌሎች ዳኞች መቀየራቸውን ጠቅላይ ...
Read More »