አቶ ደመቀ መኮንን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሱ ህዝባዊ ተቃውሞ ህገ-መንግስቱን በሃይል ለመናድ የተደረጉ የአመጽ ድርጊቶች ናቸው አሉ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሱ ህዝባዊ ተቃውሞ ህገ-መንግስቱን በሃይል ለመናድ የተደረጉ የአመጽ ድርጊቶች ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ሰኞ ለመንግስት መገኛና ብዙሃን አስታወቁ። የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ደመቀ በሁለቱ ክልሎች ለሶስት ቀናት ሲካሄዱ የነበሩ የተቃውሞ ሰልፎች “ህገወጥ” ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ሲካሄዱ የቆዩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ...

Read More »

በጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጥሎ የግልና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ አለመጀመራቸው ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) ላለፉት ሶስት ቀናቶች በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ሰኞ ድረስ እልባት አለማግኘቱንና በከተማዋ የግልና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ አለመጀመራቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የፈጸሙትን ግድያ በመቃወም ነዋሪዎች በሶሮቃ አካባቢ አሁንም ድረስ ከመከላከያ አባላት ጋር ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸው ታውቋል። ተጨማሪ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወደ አካባቢው በመስፈር ላይ መሆኑን የተናገሩት እማኞች በጎንደር ከተማ ...

Read More »

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቶ ሃብታሙ አያሌው በሃኪሞች ቦርድ ከሃገር ውጭ እንዲታከም የታዘዘን ውሳኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲያጣራ አዘዘ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጽኑ በህመም ላይ የሚገኘው አቶ ሃብታሙ አያሌው በሃኪሞች ቦርድ ከሃገር ውጭ እንዲታከም የታዘዘን ውሳኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መርምሮ እንዲያጣረ አዘዘ። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ከሃገር እንዳይወጣ እገዳ ተጥሎበት የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አቶ ሃብታሙ አያሌው ያቀረበውን የሃኪም ማስረጃ የተሟላ አይደለም ሲል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የአቶ ሃብታሙ አያሌው ...

Read More »

ህወሃት መራሹ መንግስት ህዝባዊ አመጹን በሃይል ለመቆጣጠር ባደረገው ሙከራ በአንድ ሳምንት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  በግፍ ተገደሉ

ነሃሴ  ፪ ( ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት አገዛዝ በቃን የሚሉ ተቃውሞዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ህዝባዊ አመጹን በመሳሪያ ለመጨፍለቅ እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው። በዚህ የሃይል እርምጃ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ከ150 በላይ ሰዎች መገደላቸው በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ ዜጎች መቁሰላቸው ታውቋል። በኦሮምያ በበርካታ ከተሞች ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ...

Read More »

በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ንቅናቄ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እየተከሰተ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄና መንግስት እየወሰደ ያለውን የግድያ እርምጃ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሽፋን ሰጡ። ቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል፣ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ፣ ዶቼ ቬለ እና፣ ኤንዲ24 በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ከዘገቡት አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ይጠቀሳሉ። ቢቢሲ ባሳለፈነው ቅዳሜና እሁድ በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች ብዛት ያላቸው ዜጎች በመንግስት ...

Read More »

ህወሃት በጎንደር የሃይማኖት አባቶችን በማሰማራትና ታቦት በማስወጣት ህዝባዊ ንቅናቄውን ለማጨናገፍ እየሰራ ነው ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠየቁ። ሰሞኑን ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት መንግስት ባሰማራቸው የመከላከያ፣ የፖሊስና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ማዋል ስለተሳነው የሃይማኖት ተቋማትንና የሃይማኖት አባቶችን ተጠቅሞ ህዝባዊ ንቅናቄውን ለማጨናገፍ እየሰራ መሆኑን ድርጊቱን በቅርበት የሚከታተሉ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። እነዚህ በዳንሻ እና ሰሮቃ አካባቢ የሚኖሩ ...

Read More »

የጎንደር ህዝብ ከእንግዲህ በህወሃት /ኢህአዴግ አንገዛም አለ

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጎንደር ከተማ ህዝብ ገንፍሎ በመውጣት በህዋሀት ኢህአዴግ ላይ ያለውን ተቃውሞ ሲያሰማ ውሎአል። ከእየቦታው የተሰባሰበው የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በአዘዞ በአርሶአደር ታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። የህዝቡን ትግል ለመርዳት ከወልቃይትና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር መግባታቸውን ተከትሎ ወታደሮቹ ጥቃታቸውን ቀንሰዋል። በልዩ ሃይል ...

Read More »

የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ሰራተኞች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አስተዳደር ያለሰራተኞቹ ፈቃድ ለአባይ ግድብ በሚል የአንድ ወር ደሞዛቸውን  ከነሐሴ ጀምሮ እንደሚቆርጥ ማስታወቁን ተከትሎ ሰራተኞቹ ተቃውሞውአቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የሰራተኛው ተቃውሞ ያስፈራው አስተዳደሩ ውሳኔውን ለሚቀጥለው ወር መተላለፉን አስታውቋል። ሰራተኞች ውሳኔውን አንቀበለም በማለታቸው ደሞዛቸው የታገደ ሲሆን በዚህም ምክንያት  ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ ሰራተኞቹ  እኛ የምናዋጣው ከምናገኘው ጋር ተመጣጣኝ ...

Read More »

በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በጎርፍ አደጋ ተጠቁ፡፡

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር በ2 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በመገንባት ላይ ያለው ርብ ግድብ ከመፍረሱ ጋር ተያይዞ ከ17 በላይ ሰዎች መሞታቸው እንዲሁም ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ከደረሰባቸው በሁዋላ፣ የግድቡ ውሃ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎችን ማጥለቅለቁ ታውቋል፡፡በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ መንገድ ዳርና ወደተራራ ቦታዎች በመሄድ ለመስፈር ሙከራ እያደረጉ ነው። ግድቡ በ4 ...

Read More »

ሶስት የኢሲኤ (ECA) ሰራተኞች ታሰሩ

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008) አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት  መንግስታት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ቦምብ እና መሳሪያ ተገኝቷል በሚል ሶስት የድርጅቱ ሰራተኞች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ። ዋና ሃላፊው ሚስተር ካርሎስ ሎፔዝ  የድርጅቱን ሰራተኞች ባልተጣራ ጉዳይ አሳልፈው መስጠታቸው በሰራተኞች ዘንድ እያነጋገረ መምጣቱንም መረዳት ተችሏል። አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታተ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ግቢ ወስጥ ተገኘ ከተባለው መሳሪያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ...

Read More »