በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የጅምላ አፈሳ እየተካሄደ ነው ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008) በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ የለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በአካባቢው የጅምላ አፈሳ በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። የክልሉ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ጨለማን ተገን በማድረግ ተቃውሞን አስተባብረዋል ብለው የጠረጠሯቸውን አካላት በማሰር ላይ እንደሆኑ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር በደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው ሰፍረው የሚገኙ ...

Read More »

የጢስ አባይ ነዋሪዎች እና ወታደሮች ሲታኮሱ ዋሉ

ነሃሴ  ፫ ( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ የተገደለውን አንድ  የጢስ አባይ ተወላጅ ደም ለመበቀል የሟች ቤተዘመዶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ሌሊቱን ከአጋዚ ጦር ጋር ጠበንጃ አንስተው ሲዋጉ ማደራቸው ከጢስ አባይ የወጡ መረጃዎች የክልዩ ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡በጢስ አባይ ከተማ ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመሄዱ ዛሬ ረፋዱ ላይ  ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት  ከተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች በአንቶኖቭ ...

Read More »

ባለፉት ሶስት ቀናት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር በእየለቱ እያሻቀበ ነው

ነሃሴ  ፫ ( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አጋዚ የሚባሉት የገዢው ፓርቲ ታማኝ ወታደሮች በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ከተለያዩ አካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በኦሮምያ ክልል ብቻ ከ130 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በአማራ ክልል ደግሞ ከ70 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። ከፍተኛ ግድያ ከተፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል ባህርዳር ቀዳሚ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ ...

Read More »

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለን ግድያ በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያ አማራ ክልሎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለን ግድያ በመቃወም ማክሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። እየተፈጸመ ያለውን ግድያና እስራት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ጥያቄን ሲያቀርቡ ያረፈዱት ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት ከአምባገነን መንግስታት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም አሳስበዋል።  የአሜሪካ መንግስት በየአመቱ በኢትዮጵያ ስለሚፈጸመው የሰብዓዊ ...

Read More »

ህዝባዊ ንቅናቄው በመላ ኢትዮጵያ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተካሄዱ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ከ100 የሚበልጡ ሰዎች መንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ተከትሎ፣ ህዝባዊ ተቃውሞው በመላ ኢትዮጵያ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተነገረ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አባል የሆኑት አቶ ሙላቱ ገመቹ አሜሪካ አገር ለሚተላለፈው ለኤንቢሲ (NBC) ለተባለው የቴሌቪዥን የዜና አውታር፣ “ሰዎች በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጠዋል፣ መንግስት ደግሞ የሰላማዊ ሰልፈኞችን ፍላጎት አላሟላም” በማለት ተናግረዋል። ...

Read More »

የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም የአሜሪካ መንግስትና አለም አቀፍ ተቋማት ጠየቁ

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008) ወደ 100 ለሚጠጉ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆምና ድርጊቱ አሳስቧቸው እንደሚገኝ የአሜሪካ መንግስትና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ገለጡ። ከቀናት በፊት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በመንግስት የተወሰዱ የሃይል እርምጃዎችን ተከትሎ መግለጫን ያወጣው የአሜሪካ መንግስት በህገ-መንግስት የተቀመጡ የሃገሪቱ ዜጎች መብት እንዲከበር ጥሪን አቅርቧል። በሃገሪቱ ሰዎች ሃሳባቸውን በሰላም የመግለጽና እንዲሁም የመሰባሰብ መብታቸው መከበር ...

Read More »

በባህር ዳር ጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ አራት አባላት ተገደሉ

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008) በባህር ዳር ከተማ በሚገኝ አንድ የመከላከያ ካምፕ ውስጥ ሰኞ በጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ የእርስ በዕርስ ግጭት በትንሹ አራት አባላት መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። በከተማዋ አለመረጋጋት መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ አባላቱ ሊገደሉ መቻላቸውንና ድርጊቱ አዲስ ውጥረት ማንገሱን አስረድተዋል። በሳምንቱ መገባደጃ በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ እስከ ...

Read More »

በሳምንቱ መገባደጃ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በትንሹ 97 ሰዎች በላይ መገደላቸው ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተካሄዱ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ከ50 የሚበልጡ ሰዎች የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ ዕርምጃ ተገደሉ። በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የጸጥታ ሃይሎች በትንሹ 33 ሰዎች መግደላቸውና ተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሮይተርስ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል። በተመሳሳይ ሁኔታ በአማራ ክልል ጎንደር እና ባህርዳር ከተማ እና ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች መጠነ ሰፊ ግድያ በመንግስት ሃይሎች መፈጸሙ ታወቀ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) ባልፉት ሶስት ቀናት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ በፈጸሙት የተኩስ ዕርምጃ ከ50 የሚበልጡ ሰዎች በኦሮሞያና አማራ ክልሎች መገደላቸውን በሃገር ውስጥ የሚታተመው አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ያሰባሰባቸውን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘገበ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ስር በሚገኙት አሳሳ፣ አዳባ፣ ሻሰማኔና ኮፈሌ ከተሞች መጠነ ሰፊ ግድያ መፈጸሙን መጽሄቱ እማኞችን በመጥቀስ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃ በትንሹ 97 ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008) አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃ በትንሹ 97 ሰዎች መገደላቸውን ሰኞ ገለጠ። በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተከፍቷል ባለው በዚሁ የተኩስ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎች መጎዳታቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። የብሪታኒያው የማሰራጫ ጣቢያ (ቢቢሲ) በአፍሪካ ፕሮግራሙ ሰኞ ባቀረበው ...

Read More »