እነ አቶ በቀለ ገርባ  ለሕገወጡ ፍርድ ቤት ቃላችንን አንሰጥም አሉ

ነሃሴ  ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሚያ ክልልን አመጽ ተከትሎ ከሕግ አግባብ ውጪ ታስረው የሚንገላቱት  የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጄኔ ጣፋ፣አዲሱ ቡላላን ጨምሮ የመድረክ ፓርቲ አባል የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አያኖ ዛሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተከሳሾቹ በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ ምላሻቸውን እንዲሰጡ ከፍርድ ቤቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የክስ መቃወሚያቸውን አሰምተዋል። አቶ በቀለ ገርባ ...

Read More »

በጎንደር እና በባህርዳር የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

በአዲስ አበባም የስራ ማቆም አድማ ተጠርቷል ነሃሴ  ፬ ( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን  የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለመከታተል በርካታ ህዝብ በፍርድ ቤቱ ዙሪያ ተገኝቶ ሲጠባበቅ  የዋለ ቢሆንም፣ ኮሎኔሉ ፍርድ ቤት ባልቀረቡበት ሁኔታ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። በድርጊቱ የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን ገዢውን ፓርቲ በማውገዝ እና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋት የገለጹ ሲሆን፣ ከተማዋን የወረሩት ልዩ ኮማንዶ የሚባሉት፣ የአጋዚ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተክትሎ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደኅንነት ሁኔት አስጊ መሆኑን ሪፕሪቭ ገለጸ

ነሃሴ  ፬ ( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ100 በላይ ሰላማዊ ዜጎች መብታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸውን ተክትሎ በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ተክትሎ ላለፍት ሁለት ዓመታት ከየመን ታፍነው የተወሰዱት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል የሚል ስጋት እንደፈጠረባቸው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፕሪቭ  አስታውቋል። የሶስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ተላልፈው መሰጠታቸውና እስካሁን ...

Read More »

ኢትዮጵያ ገልለተኛ አጣሪ ቡድን የተቃውሞ ሰልፎች ወደሚደረጉባቸው ቦታዎች እንዲገባና እንዲያጣራ እንዲፈቅድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ

ነሃሴ  ፬ ( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አል ሁሴን እንደገለጹት በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተፈጸሙት ሃይል የተሞላባቸው እርምጃዎች እንዲመረመሩ ጽ/ቤታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋጋር ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። የታሰሩት ዜጎች እንዲፈቱም ባለስልጣኑ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ዜናም ሜሪካና አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግድያ እንዲያጣሩ ዋሽንግተን ፖስት ጠይቋል። ዋሽንግተን ፖስት ባወጣው ርእሰ አንቀጽ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ...

Read More »

የህወሃት/ኢህአዴግ የስልጣን መሰረት ተናግቷል ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት መንበረ-ስልጣኑን ላይ ከተቆናጠጠ ከ25 ዓመት ወዲህ በቅርቡ ያጋጠመውን አይነት ህዝባዊ ተቃውሞ አጋጥሞት እንደማያውቅና፣ ይህ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገለጸ። የወቅቱን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታ አስመልክቶ የምስራቅ አፍሪካ ተማራማሪ የሆኑት ሬኔ ላፎትን ለዣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሲናገሩ “ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወጀብ ውስጥ የምትጓዝ አውሮፕላን ትመስላለች” ሲሉ ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ ደረጃን ...

Read More »

ከተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር ተያይዞ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌና የሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ደህንነት አደጋ ውስጥ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) በኢትዮጵያ በመባባስ ላይ ያለው ህዝባዊ አመጽና የፖለቲካ አለመረጋጋት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ደህንነትን አደጋ ውስጥ እንደከተተው አንድ አለም አቀፍ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ረቡዕ አስታወቀ። የብሪታኒያ መንግስት በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ነውጥ ግምት ውስጥ በማስገባት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥረትን ማድረግ እንዳለበት ሪፕሪቭ የተሰኘው ተቋም ገልጿል። በኢትዮጵያ በመካሄድ ...

Read More »

ምዕራባውያን አገራት ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያጤኑት ተጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) በሳምንቱ መገባደጃ በኢትዮጵያ የተፈጸመው የ100 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ ምዕራባውያን ሃገራት ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ድጋፍ ዳግም እንዲያጤኑት የሚያደርግ መሆኑ አለበት ሲል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አቋሙን በሚያንጸግባርቅበት ርዕሰ-አንቀጽ ገለጸ። በሃገሪቱ እየተካሄዱ ባሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ አቋሙን ይፋ ያደረገው ይኸው አለም አቀፍ ጋዜጣ የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በሃገሪቱ እየተፈጸመ ያለው ግድያ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በይፋ ማወጅ እንዳለባቸው አሳስቧል።  በኢትዮጵያ ...

Read More »

የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በገለልተኛ አለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን ማጣራት እንዲደረግበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየተወያየ እንደሆነ ገለጸ

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሳምንቱ መገባደጃ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በገለልተኛ አለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን ማጣራት እንዲደረግበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ መሆኑን ረቡዕ ይፋ አደረገ። በአለም ዙሪያ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተለው ይኸው አካል የኢትዮጵያ  መንግስት ከአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል በሯን ክፍት እንድታደርግ በይፋ መጠየቁን ሮይተርስ ከጄኔቭ ዘግቧል።  ከቀናት በፊት ከ100 ለሚበልጡ ...

Read More »

በኦሮሚያ ምስራቅ ሃረርጌ ህዝባዊ ተቃውሞ መቀጣጠሉ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ዳግም ተቀስቅሶ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ መቀጣጠሉንና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። ለእስር የተዳረጉ ነዋሪዎች ከእስር እንዲፈቱና በአከባቢው የተሰማሩ የጸጥታ ሃይሎች የሚወስዱትን የሃይል እርምጃ እንዲያቆሙ በመጠየቅ ላይ ያሉ ነዋሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠሉን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በአካባቢው በሳምንቱ መገባደጃ የተከናወኑ ህዝባዊ ...

Read More »

በካሳንቺስ የሚኖሩ በ 10 ሺዎች የምቆጠሩ ነዋሪዎች ለልማት በሚል ሰበብ ከመኖሪያ ቦታቸው ሊነሱ ነው

ኢሳት (ነሃሴ 4, 2008) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከካዛንቺስ ቤተመንግስት ዙሪያ በተለምዶ ግቢ ገብርዔል ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ እስከ ኡራዔል ቤተክርስቲያን ድረስ ያሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ለልማት በሚል ሰበብ ለማስነሳት የተያዘው እቅድ በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞን ቀሰቀሰ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ከከተማው አስተዳደር ከነዋሪዎች የተላለፈን መልዕክት ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ተቃውሞን እያቀረቡ እንደሆነ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።  ...

Read More »