በደባርቅ ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ መጀመሩን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ለሶስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ማክሰኞች መጀመራቸውን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎች የወሰዱትን ዕርምጃ ለማስቆም ያደረጉት ጥረት ግጭትን ቀሰቀሰ። የስራ ማቆም አድማ ያካተተውን ተቃውሞ የተቀላቀሉ የደባርቅ ከተማ ሆስፒታል የህክምና ስራተኞች በቅጥር ግቢው ውስጥ በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በጎንደር ባህር ዳር ከተማ የተፈጸመ ግድያን ለማውገዝና ...

Read More »

በፌዴራልና ክልል ከተሞች መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና ክልሎች መደበኛ መንግስታዊ አገልግሎቶች በመስተጓጎላቸው የህዝቡን ምሬት እያባባሱ እንደሆነ ተገለጸ። አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና የልል መንግስታዊ ተቋማት በመዘዋወር መረጃውን ያደረሱን የኢሳት ምንጮች፣ በመንግስታዊ ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚሄዱ ነዋሪዎች አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ በመፈጠሩ በስርዓቱ ላይ መማረራቸውን ገልጸዋል። በተለይም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች ...

Read More »

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ጠየቁ

ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች ጠየቁ። በአቶ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በጋራ ተጽፎ ለኢሳት የደረሰው ...

Read More »

በክልሎች ሲካሄዱ የቆዩ ተቃውሞዎችን ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ሲያገናኝ የቆየው መንግስት ችግሩ ከአገልግሎት አሰጣት ችግር የመነጨ ነው አለ

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008) በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በጸረ-ሰላም ሽብርተኛ ቡድኖች የተዘጋጀ ነው ሲል የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት የአገልግሎት አሰጣት ችግሮች ለተቃውሞ ምክንያት ሆኗል በማለት ሰኞ አስታወቀ። በሃገሪቱ ስላለው የጸጥታ ጉዳይ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች ማብራሪያን የሰጠው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ለአምባሳደሮቹ መግለጹን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሃገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን ...

Read More »

ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የዕርዳታ ገቢ እየተሰበሰበ ነው

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008) ነዋሪነታቸው በተለያዩ ሃገራት የሆነ ኢትዮጵያውያን አትሌት ፈይሳ ሌልሳን ለመደገፍ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ40ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ቢቢሲ ሰኞ ዘገበ። አትሌቱ በኢትዮጵያ ያለውን ግድያና አፈና በመቃወም ወደ ሃገሪቱ እንደማይመለስ መግለጹን ተከትሎ በርካታ ስራዎች ለአትሌቶቹ ድጋፋቸውን እየገለጹ እንደሚገኝ የዜና አውታሩ በዘገባው አስፍሯል። አትሌቱ በሌላ ሃገር ለሚያደርገው የፖለቲካ ጥገኝነት ይረዳ ዘንድ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን አትሌቱን ለመደገፍ ...

Read More »

በአውስትራሊያ ለኢሳት ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008) ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓል በማስመልከት በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄዱ። በአውስትራሊያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዝግጅት አካል በሆነው የሲድኒው 6ኛ አመት የኢሳት የምስረታ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍ በተለያዩ መልክ መግለጻቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚሁ የሲድኒ ዝግጅት ኢሳትን ለመደገፍ 35 ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008) አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሃገሪቱ የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና እስራትን በመቃወም የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እሁድ በሪዮ ኦሎምፒክ የተቃውሞ መልዕክቱን ያስተላለፈው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ጥሪውን አቀረበ። እሁድ በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ስለሆነ የተቃውሞ ድርጊቱ ከኢሳት ጋር ቆይታን ያደረገው አትሌት ሌሊሳ በተለይ አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶች የገዢው የኢህአዴግ መንግስትን ግድያ እና አፈና በመቃወም ...

Read More »

በባህር ዳር የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008) በቅርቡ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጸሙ ድርጊቶችን በማውገዝ በተለያዩ ተቃውሞ ውስጥ የቆዩ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች እሁድ የጀመሩት ከቤት ያለመውጣት አድማ ሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ለኢሳት አስታወቁ። ህዝበ ውሳኔ ተላልፎበት ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው ይኸው አድማ የከተማዋ ነዋሪ በመንግስት የሚፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን በፅኑ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። ...

Read More »

በባህርዳር የስራ ማቆም አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ

ነሃሴ  ፲፮ ( አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የስራ ማቆም አድማ   የአገልግሎት መስጫ ድርጅቶች ተዘግተው ውለዋል፡፡ ሁሉም የግል ባንኮች አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ሲሆን፣  የፖስታ ቤት ባለሙያዎችም በስራ ማቆሙ አድማ ተሳታፊ በመሆን መስሪያ ቤቱን ዘግተዋል፡፡ የተለያዩ የክልል ቢሮዎች ሰራተኞቻቸው በአድማው እንዳይሳተፉና ቢሮ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም፣  አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ‹‹ እኛም የህብረተሰቡ አንድ ...

Read More »

በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አዋሽ ውስጥ ታስረዋል

ነሃሴ  ፲፮ ( አሥራ  ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነሃሴ 6 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ተካሄዶ በነበረው ተቃውሞ የተያዙ ከ2500 በላይ ዜጎች አዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። ታስረው ከተፈቱት መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት ውሃ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉ ተደብድበዋል። በጠጠር እና በእሾህ ላይ እንዲሮጡ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ከ2 ሺ 400 በላይ እስረኞች አሁንም በእስር ቤቱ ውስጥ ይገኛሉ። ...

Read More »