ነሃሴ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ቀጥለዋል። ትናንት በሰሜን ጎንደር የመተማ ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ ፣ ድንበር ጠባቂዎችና አካባቢ ሚሊሺዎች በህዝብ ላይ ለመተኮስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ፣ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ስፍራው ደርሰው ከ20 ያላነሱ ሰዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል። ወታደሮቹ በህዝብ ላይ በቀጥታ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሚፈሰው የንጹሀን ደም በአስቸኳይ እጃቸውን ያነጹ ዘንድ ተጠየቁ
ነሃሴ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ይህን የጠየቁት ታዋቂው ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ነው “ከጌታ ምሕረትን ተቀብዬ ላለፉት 27 ዓመታት ዘር፣ ጎሣ፣ ቀለም፣ ጾታ፣ እምነትና የፖለቲካ አመለካከት ሳልለይ ለትንሽ ለትልቁ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስሰብክ የኖርኩ ነኝ” ያሉት ወንጌላዊ ያሬድ፣ ዛሬ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍሎት በልብ ጭንቀትና በብዙ ዕንባ ነው።› በማለት ...
Read More »በቦዲ አርብቶአደሮች መንገድ በመዝጋታቸው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች መንቀሳቀስ አልቻሉም
ነሃሴ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል የቦዲና ሙርሲ ጎሳዎች መሬታቸውን ለሸንኮራ አገዳ ተክል መወሰዱን ተከትሎ የጀመሩትን ተቃውሞ በመቀጠል መንገዶችን በድንጋይና በእንጨት በመዝጋት ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። አንድ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ሹፌር የቦዲ ማህበርሰብ አባል ገጭቶ መግደሉን ተከትሎ የማህበረሰቡ አባላት ለሟች ቤተሰብ ካሳ ለመሬታችንም ተገቢው ክፍያ ይከፈለን በማለት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ አላገኙም። አርብቶአደሮቹ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በዜጎች ላይ የሚደረገው የኃይል እርምጃዎች እንዲቆሙ ሲል ጠየቀ
ነሃሴ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ በመንግስት ታጣቂዎች የሚፈጸሙ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃዎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲቆሙ ሲል ሰመጉ ሪፖርት አድርጓል። ሰመጉ ዜጎችን ከመኖሪያቸው ማፈናቀል፣ግድያ፣ እስራትና በሕገመንግስቱ እና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የተፈቀዱ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች እንዲከበሩ ጠይቋል። አላግባብ ከሕግ ውጪ ንጹሃንን የገደሉ በሕግ እንዲጠየቁና ጉዳተኞች ካሳ እንዲሰጣቸው ሲል ሰመጉ አሳስቧል።የጸጥታ ...
Read More »ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የአባይ ግድብን ተጽዕኖ የሚያጠኑ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008) በመገንባት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ላለፉት አራት አመታት ሲወዛገቡ የቆዩት ግብፅ፣ ኢትዮጵያና፣ ሱዳን፣ የአባይን ግድብ ተፅዕኖ እንዲያጠኑ ከተመረጡ ሁለት የፈረንሳይ አማካሪ ኩባንያዎች ጋር በሚቀጥለው ሳምንት የስምምነት ሰነድ እንደሚፈራረሙ ተገለጸ። የስራ ውል ስምምነት የሚፈራረሙት የሶስቱም አገራት የውሃ ልማት ሚኒትሮች ሲሆኑ፣ አርቴሊያና (Artelia) ቢአር ኤል (BRL) የተባሉ ኩባንያዎች የግድቡን ይዘትና፣ ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ሊያመጣ የሚችለውን ...
Read More »በአምባ ጊዮርጊስ 26 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008) በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ተቃውሞውን ለማዳፈን የተንቀሳቀሰው የአጋዚ ሰራዊት በአምባ ጊዮርጊስ 26 ሰዎችን መግደሉ ተነገረ። በአጋዚ ሰራዊት በተኮሰው ጥይት የቆሰሉ በርካታ የአምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ለህክምና ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል። በህወሃት ባለስልጣናት ልዩ የግድያ ትዕዛት የተሰጠው ጸጉረ-ልውጥ የሆነ ገዳይ የአጋዚ ቡድን በሰላማዊ ህዝብ ላይ በሰነዘረው ጥቃት ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 26 ...
Read More »መድረክ ኢህአዴግ ያወጣውን መግለጫ “የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ የማይመልስ” በማለት መገለጫ አወጣ
ኢሳት ( ነሃሴ 25 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ(መድረክ) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ የ15 ዓመት ግምገማ በማለት ያወጡትን መግለጫ “ህዝቡ ለሚያነሳቸውን መሰረታዊ ጥያቂዎች ምላሽ የማይሰጡ” በማለት መግለጫ አወጣ። በአገሪቱ ለተከሰተው ችግር ኢህአዴግ ሃላፊነቱን እንዲወስድም ጠይቋል። መድረክ ነሃሴ 23 ቀን 2008 ዓም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ የህዝቡን ፍላጎትና ጥያቄ ወደጎን ...
Read More »ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የብሄር ፌዴራሊዝም ከፍተኛ ፈተና ተጋርጦበታል ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ግንባር ቀደምትነት በኢትዮጵያ በስራ ላይ እየተተገበረ ያለው ያለው ፌዴራሊዝም፣ አዋጪነቱ በምዕራብያውያን ዲፕሎማቶችና የፖለቲካ ተንታኞችን አጠያያቂ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ። ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው ፌዴራሊም በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ እንዲውል ያደረገው፣ አገራዊ አጀንዳ ያላቸው ድርጅቶች እንዳያንሰራሩ ለመደፍጠጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በቀጣይ ሊቀሰቀሱ የሚችሉ ብሄር ተኮር ተቃውሞዎችን ከፋፍሎ ለመምታት ታስቦ እንደሆነ ፎሪይን አፌይስ ትናንት ባወጣው ዘገባ አስረድቷል። ...
Read More »በጅቡቲ ተሰደው የሚገኙ የኦሮሞና አማራ ብሄር ተወላጆች ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ተላልፈው እንዳይሰጡ ተጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) የጅቡቲ መንግስት በአገሩ የሚገኙ በመቶዎችን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንዳይሰጥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተማጽኖ አቀረበ። ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ በግዳጅ የሚመለሱ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሰቆቃ፣ እስራት ወይም ግድያ ሊደርስባቸው ይችላል ሲል ገልጿል። የጅቡቲ መንግስት ብዛት ያላቸው የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስሮ እንደሚገኝ የገለጸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ፣ ስደተኞችን ወደኢትዮጵያ በግዳጅና በጅምላ ...
Read More »በአማራ ክልል የሚካሄደው ህዝባዊ ንቅናቄ ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
ነሃሴ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ወታደሮችም በህዝብ ላይ እየተኮሱ ነው። የሰሜን ጎንደር ከተሞች ደባርቅና አምባጊዮርጊስ ዛሬ ከወትሮው በተለየ ከአጋዚ ወታደሮች፣ ከታጣቁ የአካባቢ ሚሊሺዎች ጋር ሲፋለሙ ውለዋል። በደባርቅ ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ በዋለው ህዝባዊ አመፅ 4 ሰዎች ሲገደሉ ከ17 በላይ ቆስለዋል። ባለፈው ሰኞ ነሃሴ 23፣ 2008 ዓም አንድ ዘይት እና እህል የጫነ ተሽከርካሪ በከተማው ...
Read More »