ጳጉሜ ፩ ( አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ እምቢተኝነቱን ጥሪ ተቀብለው በአስቸኳይ በተግባር ላይ ባዋሉት የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች፣ የንግድ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። ምንም አይነት የመኪና እንቅስቃሴ የለም። ለወትሮው ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ከተሞች ዝምታ ሰፍኗል። በርካታ ነዋሪዎችን በአጋዚ ጦር ያጡት የምስራቅ ሸዋ ከተሞች አርሶ፣ ኮፈሌና ዶዶላ የምስራቅ ሃረርጌዎቹ ሀሮማያ፣ አወዳይ ፣ ኮምቦልቻ፣ እንዲሁም አምቦ፣ ባሌሮቤ፣ ወለጋ ...
Read More »ህዝቡ ተከታታይ ጥሪዎችን በንቃት እንዲጠብቅ ተጠየቀ
ጳጉሜ ፩ ( አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴው ለኢሳት እንደገለጸው በአሁኑ ሰአት የተለያዩ የስራ ማቆም አድማዎች እንዳሉ ተደርጎ የሚበቱ ወረቀቶች ወይም የሚተላለፉ የቃል መልእክቶች አስተባበሪ ኮሚቴው ያልጠራውና ሆን ተብሎ በገዢው ፓርቲ የሚደረግ የማምታቻ ጥሪ ነው። ህዝቡ ከአስተባባሪው ኮሚቴ ከሚሰጠው መግለጫ ውጭ በሌሎች መግለጫዎች እንዳይታለል የጠየቀው የአስተባባሪ ኮሚቴው፣ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና የሁለተኛ ...
Read More »ሜቴክ ገንዘብ የከለከለው ድርጅት የኦሞ ኩራዝ ፋብሪካ ስራውን ትቶ አዲስ አበባ ገባ
ጳጉሜ ፩ ( አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ስር በሚገነባው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ውስጥ ድርሻ ወስዶ የግንባታ ስራ ሲሰራ የነበረው ፒጂኤ የተባለው የንግድ ድርጅት ለስራው ስራ መከፈል የነበረበት 40 ሚሊዮን ብር ሊከፈለው አለመቻሉን ተከትሎ አካባቢውን ለቆ ወጥቷል። ሜቴክ መክፈል የነበረበትን ገንዘብ ለፒጄኤ ለመክፈል ባለመቻሉ፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ድርጅቱ ለአንድ አመት ያክል ...
Read More »በቂሊንጦ እስርቤት የነበሩ ወደሶስት ሺ የሚጠጉ እስረኞች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰን የእሳት አደጋ ተከትሎ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ እስረኞች ለሶስተኛ ቀን የገቡበት አለመታወቁ አሳስቦት እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሰኞ አስታወቀ። የእስረኞቹ ወደ ዝዋይና ሸዋ ሮቢት ተዛውረዋል ተብሎ ቢገለፅም፣ የታሳሪ ቤተሰቦት ወደ ስፍራው ሄደው እስረኞቹ እንደሌሉ ተነግሯቸው መመለሳቸውንና ድርጊቱ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ተሾመ ከዜና ...
Read More »በጎንደር እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም ለተለያዩ ግብዓቶች ማስፈጸሚያ የ3.5 ሚሊዮን ብር በጀት ጥያቄ ቀረበ
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) በጎንደር ከተማና ዙሪያዋ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ እልባት አለማግኘቱን ተከትሎ የከተማው አስተዳደር የክልሉ መንግስት ለጸጥታ ሃይሎች ለሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማስፈጸሚያ የ3.5 ሚሊዮን ብር ልዩ የበጀት ጥያቄን አቀረበ። የከተማዋ አስተዳደር እስከ ነሃሴ አምስት 2008 ዓም ድረስ ለጸጥታ ሃይሎች ምግብና የስልክ አገልግሎቶች እንዲሁም ለእስረኞች የምግብ አቅርቦት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን የክልሉ መንግስት ባቀረበው ባለ ...
Read More »የኢትዮጵያና የግብጽ የአባይ ግድብ ምክክር ከጸጥታ ችግራ ጋር በተያያዘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የኢትዮጵያ ጠየቀች
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) ዛሬ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ የነበረ የኢትዮጵያና የግብጽ የአባይ ግድብ ምክክር ከጸጥታ ችግራ ጋር በተያያዘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የኢትዮጵያ መንግስት መወሰኑን የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ። ሁለቱ ሃገራት የአባይ ግድብ ግንባታ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት (በተለይ በግብፅ ላይ) የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለማስጠናት ከሁለት የፈረሳይ ኩባንያዎች ጋር ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ የፕሮጄክት ስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ይሁንና ...
Read More »መንግስት ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ከመጠን በላይ ያለፈ ሃይል መጠቀሙን አሜሪካ ገለጸች
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር መንግስት ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ እየተጠቀመ መሆኑ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጠች። ይኸው ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የሃይል እርምጃ በገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲካሄድበት ሃገሪቱ አበክራ መጠየቋን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፖወር ለአለም አቀፍ ጋዜጠኞች አስታውቀዋል። በርካታ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት እሳት ከመነሳቱ በፊት እስረኞች በጥይት መገደላቸውን ተገለጸ
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) በቂሊንጦ እስር ቤት እሳት ከመነሳቱ በፊት እስረኞች መገደላቸውንና የእሳት ቃጠሎ የተፈጸመው ግድያውን ለመሸፈን ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ቅዳሜ ዕለት ንጋት ላይ ከ2:30 ጀምሮ ለሁለት ሰዓታት ያህል እስር ቤቱ በእሳት የጋየ ሲሆን፣ ከእሳቱ ሸሽተው ህይወታቸውን ለማዳን የሞከሩ ሰዎች ማማ ላይ በነበሩ ጠባቂዎች በተተኮሰ ጥይት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከእስር ቤት ሊያመልጡ ሲሉ ...
Read More »አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በመንግስት ሃይሎች ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Rights of Ethiopians) ከህወሃት አልሞ ተኳሾችና መስዋዕት ለሆኑ፣ ጉዳት ለደረሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እንዲደረግ አለም አቀፍ ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ በማድረግ ለኢትዮጵያውያን መብት በአገራችን በተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት በአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የኦሮሚያና የአማራ ክልል ለሚገኙ ወገኖች የተቻለንን ድጋፍ የማድረጊያ ጊዜው አሁን መሆንኑን በመግለጽ በመላው ...
Read More »ከ450 በላይ የሚሆኑ መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝባዊ ተቃውሞውን መቀላቀላቸው ተነገረ
ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008) በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሳያቋርጥ ወራትን ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ ከ450 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ ተቀብለው ትግሉን እንደተቀላቀሉ ተገለጸ። ከ450 በላይ የሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት በሰሜን ጎንደር አካባቢ ህዝባዊነታቸውን በማሳየት ወያኔን በማስወገዱ ሂደት ላይ ተጋድሎ ለማድረግ ህዝባዊ እምቢተኝንቱን ትናንት እሁድ መቀላቀላቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል። ህዝቡን የተቀላቀሉት የሰራዊት ተወካይ ከስፍራው ...
Read More »