በዛምቢያ ሲጓጓዙ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ጠፋ

ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በዛምቢያ ድንበር በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ ነበሩ የተባሉ 14 ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ሁለት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አርብ ገለጡ። የዛምቢያ ፖሊስ በበኩሉ በተለያዩ ጊዜያው ወደ ዛምቢያ የሚሰደዱና ሃገሪቱ አቋርጠው የሚጓዙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው መገልጹን የዛምቢያ መገኛኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሃገሪቱ የድንበር አካባቢ ደርሶ ነበር ከተባለው የትራፊክ አደጋ የተረፉ 12 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ከቀናት በፊት የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት የስራ ማቆም አድማ አርብ ድረስ መቀጠሉን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስታወቁ። የአዲስ አበባ ኮሚሽን በበኩሉ የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የአዲስ አመት በአል ዝግጅት በሰላም ለማክበር ሲባል በከተማዋና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የጸጥታ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን አርብ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ ...

Read More »

በቡሬ ከተማ መንግስትን ይቃወማሉ የተባሉ ባለሃብቶችና ወጣቶች እየታሰሩ ነው ተባለ

ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በአማራ ክልል በቡሬ ከተማ የተቀቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስትን አይደግፉም የተባሉ ባለሃብቶችና ወጣቶች እየታሰሩ እንደሆነ ተገለጸ። ባለሃብቶቹ የታሰሩት ነሃሴ 20 ህወሃት/ኢህአዴግን በመቃወም በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመሳተፋቸው ሳይሆን ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የቡሬ ከተማ የፖሊስ አስተዳደር ጽ/ቤት  በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶች የወደመባቸው ንብረት እንዲያሳውቁ በደብዳቤ ጠይቆ፣ ህዝባዊ ተቃውሞውን ያነሳሱ በሚል የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ምርመራ ...

Read More »

ሽንፋ አካባቢም በህዝቡ እና በወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ዋለ

ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአይን እማኞች እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን ሽንፋ እና ሸይዲ መሃል ላይ ዘውዴ ባድማ በሚባል ቦታ ላይ የአጋዚ ወታደሮች ከልዩ ሃይል አባላት ጋር በጋራ በመሆን፣ የህዝቡን የጦር መሳሪያ ለመቀማት ሲንቀሳቀሱ መሳሪያቸውን ለማስረከብ ፈቀዳኛ ካልሆኑት ነዋሪዎች ጋር ተታክሱዋል። የተኩስ ልውውጡን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሷል። ህዝቡ መሳሪያውን ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ ገዢው ...

Read More »

አዲሱን ዓመት በደስታ ለመቀበል የሚጣደፍ ህብረተሰብ አለመኖሩ ገዥውን መንግስት አሳስቦታል፡፡

ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ የዘመን መለወጫ ቀንን ለመቀበል ከአሁን በፊት ሲታይ የነበረው ጥድፊያና ጉጉት ባለመታየቱ ከተማዋን ለሟሟቅ በተለያዩ ሱቆችበራፍና መንገድ ላይ በርካታ የድምጽ ማጉያዎችንበመከራየት ልዩ ልዩ ዘፈኞችን በመክፈት ለሟሟሟቅ የሚደረገው ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል፡፡ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት  ከአሁን በፊት የነበሩት በዓላት በአዲስ ተስፋ ሲቀበሉ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን ህዝቡ ተገዳይ በሆነበት ጊዜ ላይ ቆመው እንዲህ አይነቱን የበዓል ግርግር ለመቀበል ህሊናቸውአይፈቅድም፡፡ በአዲስ አበባ በመላው ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች  በጥቃቅንና አነስተኛ የሚንቀሳቀሱ ኢንተርፕራይዞች የመንገድ ላይ ባዛር እንዲያካሂዱ ግፊት ተደርጎባቸው ቢያካሂዱም የሸማቹ ቁጥር መቀነሱእንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ ዜና በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር  ለአዲሱ አመት የተዘጋጀውን ሎተሪ ከአሁን በፊት እንደነበረው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ህብረተሰቡ ተሻምቶ አለመግዛቱ እንዳስደመማቸው ሎተሪ አዟሪዎች ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የህብረተሰቡ ክፍሎች ‹‹ ሎቶሪ በመግዛት ወገኖቻችን የሚያልቁበትን ጥይት መግዢያ ለህውሃት መንግስት አናቀብልም ›› በማለት ለመግዛት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡ የሎቶሪው እጣ መውጪያ አንድ ቀን ቢቀረውም በርካታ የሎቶሪ ትኬቶች በእጃቸው ላይ እንዳለ አዟሪዎች ገልጸዋል፡፡

Read More »

አገዛዙን የሚያገለግሉ ፖሊሶች ስርዓቱን እየከዱ በመጥፋት ላይ ናቸው

ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ሶስት የአማራ ከልል ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የተሰወሩ ሲሆን፣ በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ ሪፖርቶች እየቀረቡ ነው። የፌደራል ፖሊስ አባላት  ስርዓቱን ከመንበሩ የሚያወርደው ሰራዊቱ እንደሆነና ይህም ብዙ ጊዜ እንደማይፈጅባቸው በአጽንኦት  እየተናገሩ ነው፡፡በተለይ የደቡብ ክልል ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትበከፍተኛ ደረጃ በህውሃት አመራሮች መማረራቸውን በግልጽ የሚናገሩበት ወቅት መድረሳቸውን የፌደራል ፖሊስ አባላት ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ወደ ህዝብ ትግል ለመቀላቀልበውስጣቸው እየተዘጋጁ መሆኑን የሚናገሩት አባላቱ፣  ስርዓቱ ‹‹የተነቃነቀ ጥርስ ›› ሆኗል  ብለው ያምናሉ፡፡ የወያኔ አመራሮች በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ላይ በመመሆናቸው በየጊዜው የሚያደርጉትንእያሳጣቸው መሆኑ፣  ሰራዊቱ በስርዓቱ ላይ እምነት እንዲያጣ እያደረገው መሆኑን እነዚሁ የሰራዊቱ አባላት ይናገራሉ።

Read More »

በዛንቢያ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ሞቱ

ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዛንቢያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ላይ እያሉ የመኪና አደጋ ካጋጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ ሁለቱ በደጋው ወዲያውኑ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከአደጋው የተረፍት 12ስደተኞች በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም እርዳታ ወደ ዋናከተማዋ ሉሳካ ተወስደዋል። የሁለቱ ሟች ኢትዮጵያዊያን አስከሬን እስካሁን ድረስ በሚንባላ ጄኔራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የዛንቢያ ስደተኞች ጉዳይ ከአይኦኤም ጋር በመተባበር አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ጥረት እየተደረገ  ነው። በተጨማሪም በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ዛንቢያ ከገቡ 38 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ ሃሙስ እለት 19 የሚሆኑት ምንነቱ ባልታወቀ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አይኦኤምአስታውቋል። ዛንቢያ ውስጥ በእስር ላይ ከሚገኙት 76 ስደተኞች ውስጥ 38 የሚሆኑት ከአደጋ የተረፉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በመጀመሪያው ዙር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ሉሳካ ታይምስአክሎ ዘግቧል። በተጠናቀቀው 208 ዓ.ም አያሌ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በስደት ላይ በሚያጋጥማቸው አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሽዎች የሚቆጠሩት ወጣቶች አስታዋሽ በማጣት በተለያዩ አገራት በእስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ነው።

Read More »

በአውሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገራት የሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን ለሰዓታት ተቆጣጠሩ

  ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) በአውሮፓ ብሪታኒያ፣ ጀርመንና ስዊድን ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያን መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ይፈጽመዋል ያሉትን ግድያና አፈና በመቃወም ሃሙስ በየሃገራቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን ለሰዓታት ያህል ተቆጣጠሩ። በሶስቱ ሃገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ላይ በተመሳሳይ ዕለት እርምጃውን የወሰዱት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ጸረ-መንግስት አድማዎችን ሲያስተጋቡ ማርፈዳቸውን ከየሃገራቱ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። ስዊድን መዲና ስቶኮልም ከተማ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቆጣጥረው ያረፈዱት ...

Read More »

በአማራና ኦሮሚያ የተጀመረው የስራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነገረ

ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ የአማራና የኦሮሚያ የክልል ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆምና  ከቤት ያለመውጣት አድማ መቀጠሉ ታውቋል። ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙት የአምቦና አካባቢዋ የንግድ ድርጅቶችን የመዝጋቱ ተቃውሞ ሃሙስ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ከሃገር በት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። በተመሳሳይ ሁኔታም በሻሸማኔ ከተማ እንዲሁም በምስራቅና ምዕራብ ኦሮሚያ ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የአገልግልት መስጫ ተቋማት ስራቸው ተስተጓጉሎ መቀጠሉን ነዋሪዎች ...

Read More »

የተመድ ልዑኳን ቡድን ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንና፣ ዩጋንዳን ሊጎበኝ ነው

ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ በደቡብ ሱዳንና ዩጋንዳ ጉብኝንትን እንደሚያደርግ አስታወቀ። የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች በሃገሪቱ በሚያደርጉት የ19 ቀናቶች ቆይታ የፖለቲካ አመራሮችን የማህበረሰብ ተወካዮችንና ስደተኞችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመገናኘት ውይይት እንደሚያካሄዱ ታውቋል። በደቡብ ሱዳን ያለው ግጭት ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት መሆኑን ሲገልፅ የቆየው ኮሚሽኑ በኢትዮጵያና በዩጋንዳ የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ስጋት ...

Read More »