ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ስታዲየም እና ዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ሰኞ የኢድ አልድሃ በዓልን ለማክበር የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ በመጠየቅ የተቃውሞ ጥያቄን አቀረቡ። የቀይ ቀለም ምልክትን የያዘ ወረቀት በመያዝ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የበዓሉ ታዳሚዎች፣ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሌሎች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳስበዋል። የሙስሊሙን ትግል በማስተባበር ላይ ...
Read More »ህዝቡ የስልጣን ባለቤት አለመሆኑ አገሪቷን ለችግር እንደዳረጋት የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ገለጸ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የህዝብ ስልጣን ባለቤትነት አለመከበር እንዲሁም የዕኩልነትና የእኩል ተጠቃሚነት መርህ አለመተግባርና ዜጎችን ሁሉ ሊያሳትፍ የሚችል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ላለችበት አሳሳቢ ሁኔታ መንስዔ መሆኑን ገልጿል። በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአመታት የተከማቸ የህዝብ ብሶት ውጤት ነው ያለው ኮሚቴው፣ በስልጣን ላይ ያለው ገዢው መንግስት ለዘመናት የህዝብን ጥያቄን ሲያጣጥል ቆይቷል በማለት ...
Read More »በጎንደር የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ቀይ ፊኛ ከመልቀቃቸው በተጨማሪ፣ እጃቸውን አጣምረው ተቃውሞ አሰሙ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) የዘንድሮውን የኢድ አል አድሃ በዓል ለማክበር በጎንደር ከተማ የተሰባሰቡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ ባለስልጣናት ባለኮከብ ባንዲራን ይዘው እንደወጡ የተሰጣቸውን መልዕክት ሳይቀበሉ መቅረታቸው ታውቋል። ለበዓሉ አከባበር የታደሙት የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ወደጎን በመተው በዕለቱ የተቃውሞ መልዕክት ነው ያሉትን ቀይ ፊኛ ወደሰማይ ሲለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ መልዕክት ለዜና ክፍላችን ደርሷል። ቀይ ፊኛን ወደ ሰማይ መመልቀቁ ጎን ለጎን ታዳሚዎች እጃቸውን ...
Read More »ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውን መንግስትን ይቅርታ አልጠየቅሁም አለ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲዘግብ በአሸባሪነት ተከሶ በእስር ቤት ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አለመጠየቁን ገለጸ። ጋዜጠኛ ዩሱፍ ሙያውን ሽፋን በማድረግ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት በሚል ክስ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ቤት አመታትን አስቆጥሯል። ከ4 አመታት በላይ በእስር የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው በመክሮ ሊፈታ ወራት ሲቀሩት ከአዲሱ ዓመት ጋር በተየያዘ በምህረት በሚል ከተለቀቁት መካከል ...
Read More »አትሌት ታምሩ ደምሴ የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን የተቃውሞ ድርጊት መድገሙን አለም አቀፍ መገኛኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በመካሄድ ላይ ባለው የፓራ ኦሎምፒክ በ 1ሺ 500 ሜት የብር ሜዳልያን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምሩ ደምሴ በመንግስት የሚፈጸሙ ግድያዎችን በመቃወም የአትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ድርጊት መድገሙ አለም አቀፍ መገኛና ብዙሃን ከስፍራው ዘገቡ። ሰኞ በውድድሩ ሜዳልያን ለማግኘት የበቃው አትሌቱ በአለም አቀፉ ደረጃ ተመሳሳይ መልዕክትን ካስተላለፉ አትሌቶች መካከል አራተኛው ለመሆን መብቃቱን ኢንዲፔንደንት የተሰኘ ጋዜጣ ...
Read More »ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚገኝ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009) ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ሲካሄድ የቆየው ከቤት ያለመውጣትና የንግድ እንቅስቃሴ የማቆም አድማ ሰኞ ድረስ መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በአምቦና በዙሪያ ባሉ አካባቢዎች እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው አድማ ለሰባተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው። በተለያዩ ከተሞች አድማን እያደረጉ ያሉት ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸሙትን ድርጊት እንዲያቆሙና ...
Read More »በኢድ አል አደሃ አረፋ አከባበር ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 1 ሺህ 437ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በአል በመላው አገሪቱ በሰላምና በተቃውሞ ተከብሯል። በአዲስ አበባ በአሉ ያለምንም ችግር የተከበረ ሲሆን፣ በጎንደር፣ ድሬዳዋ፣ አወዳይና ሻሸሜ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቷል። በጎንደር ከተማ ሙስሊሙ በአሉን ለማክበር በወጣበት ወቅት በመላው አገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ግድያ በጽኑ የሚያወግዙ መፍክሮችን ከማሰማት በተጨማሪ ለኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ያለውን አጋርነት እጆቹን ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ እምቢተኝነት የተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ወጣቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዳስከፋቸው የወጣቶቹ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡
መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህር ዳር ከተማ በመንገድ ላይ ሲዘዋወሩ የተያዙትን እነዚህ ወጣቶች ከባህር ዳር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የወንዳጣ እስር ቤት ታጉረው ከሰነበቱ በኋላ፣ የስርዓቱ ቃል አቀባይ በሆኑ ና አብረው የታሰሩ በመሰሉ ከሃዲዎች ተገኘ በተባለው መረጃ ብቻ ተመርጠው ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ የጦር ካምፕ ማሰልጠኛ ተወስደው በከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው በሚወጡ መረጃዎች መረዳታቸውን ...
Read More »በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተባለ
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለአፍሪካ ህብረትና ለተለያዩ አለም አቀፍ አካላት ልዩ ትኩረት እየሆነ መምጣቱንና ተቃውሞ ሰላማዊ ምላሽ ካላገኘ በመላው ሃገሪቱ ተቃውሞ ሊቀሰቅስ እንደሚችል የቱርክ የዜና አገልግሎት አርብ ዘገበ። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባልተለመደ መልኩ በሃገሪቱ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ስጋቱን እየገለጸ እንደሆነ ያወሳው አናዱሉ የዜና አውታር፣ ተቃውሞው አሁንም ድረስ ...
Read More »በጀርመን በርሊን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ
ኢሳት (ጳጉሜ 4 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በጀርመን በርሊን ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ግድያና አፈና በመቃወም አርብ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። በበርሊን ከተማ በሚገኘው የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ተሰባስበ የነበሩት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮች በማስተጋባት የጀርመንንና ሌሎች ሃገራት መንግስታት በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ ልዩ ትኩረትን እኝዲሰጡ ጠይቀዋል። በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተለያዩ አላማ ያላቸው ...
Read More »