መስከረም ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሲደረግ የነበረው የመምህራን ስብሰባ እንዲቋረጥ የተደረገው መምህራን ተቃውሞአቸውን በዝምታ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው። ስብሰባውን የሚመሩት የአማራ ክልል ም/ሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን ለተስብሳቢው ችግራችን ስር የሰደደነው ለውጥ እናደርጋለን ከአባላት ውጭ ያሉትን ሁሉ እንሾማለን ፤ አባል እናጠራለን ቢሉም ሰሚአጥተው፤ ከግማሽ ቀን በላይ በተደረገው የዝምታ አድማ በቀረቡት ሰነዶች ...
Read More »ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ወርዶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የትግራይ ተወላጆች ጠየቁ
መስከረም ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 34 የትግራይ ተወላጆች ባወጡት መግለጫ ፣ “ህወሓት/ኢህአዴግ ተቋማዊ ባደረገው የዘውግ ፖለቲካ ምክንያት ህዝባችን ተከፋፍሎ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ በተወሰኑ ክልሎች እንደ ባዕድ የሚታዩበት ሁኔታ “ እንዲከሰት አድርጓል ብለዋል። “ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን ፍፁማዊ ለማድረግ ሃይማኖትን በመሳሪያነት ስለሚጠቀም በክርስቲያኖች ውስጥና በሙስሊሞች ውስጥም ወደ ግጭት የሚያመራ ክፍፍል ፈጥሯል” የሚሉት የተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ አክቲቪስቶችና ...
Read More »የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት -ኦህዴድ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከሥልጣናቸው ተነሱ
መስከረም ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ርእሰ መስተዳድርና የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድርና ምክትላቸው ወይዘሮ አስቴር ማሞ ከሥልጣውናቸው የተነሱት የኦህዴድ ማዕከላቅዊ ኮሚቴ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለስድስት ቀናት ባካሄደው ግምገማ ላይ ነው። በምትካቸውም አቶ ለማ መገርሳ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የመንግስት ሚዲያዎች አቶ ሙክታር ከድርና ...
Read More »በስፔንና ደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ሰነስርዓት አካሄዱ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በስፔን እና ደቡብ ኮሪያ መዲና ሴ’ኦል ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት በመፈጸም ላይ ያሉ ግድያዎችን በማውገዝ በሀገሪቱ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ሰነስርዓት ማካሄዳቸው ከሃገራቱ ለኢሳት የደረሱ መርጃዎች አመልክተዋል። በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤን በማስገባት ያላቸውን ተቃውሞ ያቀረቡ ሲሆን፣ የሃገሪቱ መንግስትም ያቀረቡትን ተቃውሞ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲከታተላቸው አሳስበዋል።
Read More »በባህር ዳርና በጎንደር ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ እንደሚገኝ ተነገረ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በመፈጸም ላይ ያሉ ግድያዎችን በመቃወም ሰኞ በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ማክሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታውቋል። በየከተሞቹ ያሉ የንግድ ቢሮዎች የስራ ማቆም አድማ የጀመሩ ድርጅቶች አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ግፊትን በማድረግ ላይ ቢሆንም የንግድ ተቋማቱ ባለቤቶችና ባለንብረቶች ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የትራንስፖርት እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለሁለተኛ ...
Read More »በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቤተ-እስራዔላውያንና ኢትዮጵያውያን እንዳሳሰባቸው ዘጄሩሳሌም ፖስት ዘገበ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት እየፈጸመ ያለው ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በእስራዔል በሚኖሩ ቤተ-እስራዔላውያንንና ኢትዮጵያውያን ዘንድ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ዘጄሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ መክሰኞ ዘገበ። በዚሁ የመንግስት ድርጊት ቁጣ ያደረባቸው ከ250 በላይ ቤተ እስራዔላውያን ቴላቪቭ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ጋዜጣው ማክሰኞ ለንባብ ባበቃው እትሙ አስፍሯል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የፖለቲካና የልማት አጋር በመሆኗ ...
Read More »በባህር ዳር ሆምላንድ ሆቴል ነጋዴዎችን ያሳተፈ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በባህር ዳርና በጎንደር ሰኞ ዕለት የተጀመረው አድማ በቀጠለበት ወቅት በባህር ዳር ሆምላንድ ሆቴል የተጠራው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ም/ጠ/ም/ር እና የብአዴን ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን በመሩት በዚሁ ስብሰባ ላይ የተጠሩት ነጋዴዎችና የአካባቢው ታዋቂ ሰዎች ሃገር የመምራት ብቃት ስለሌላችሁ ስልጣን ልቀቁ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ሰብሳቢዎቹን “አሁን እናንተ አማራ ናችሁ ወይ?” በማለት አስተያየት የሰጡ ተሰብሳቢ ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተቃጠሉ የመኪና ጋራዥ ባለቤቶች አንዱ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በባህር ዳር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተቃጠሉ የመኪና ጋራዥ ባለቤቶች አንዱ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የትግራይ ተወላጅ የሆኑትና በባህር ዳር ከተማ ለረጅም አመታት የኖሩት በህዝብ ዘንድ አለሙ ገንዳ በሚል የሚታወቁት አቶ አለሙ ካህሳይ የታሰሩት በሳምንቱ መጀመሪያ ነው። ግለሰቡ የተጠረጠሩትና ለእስር የተዳረጉት ባለፈው ቅዳሜ የአመፅ ወረቀት ሲበትኑ መያዛቸውን ተከትሎ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። አቶ አለሙ ካህሳይ ...
Read More »መንግስት በኮንሶ ብሄረሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑ ተነገረ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በደቡብ ክልል የሰገን ህዝቦች ዞን ስር የሚገኙ የኮንሶ ብሄረሰብ አባላት ሰሞኑን በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች የተከፈተባቸው ዘመቻ መቀጠሉንና ሰኞ በትንሹ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ለኢሳት አስታወቁ። የህዝብ ተወካይ ኮሚቴ አባላትን ለመያዝ በሚል ሰኞ በዞኑ ስር በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች በተፈጸመ ጥቃቅን ህይወቱ ያለፈው የአንድ ነዋሪ፣ አስከሬኑ ከአንድ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋም አጠገብ ተጥሎ መገኘቱን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን ...
Read More »ለአስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ለተጋለጡ መቅረብ የነበረበት የጥራጥሬና ቅባት እህሎች መቋረጡን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ ለምግብ እርዳታ ከተጋለጡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በመስከረም ወር መቅረብ የነበረበት የጥራጥሬና ቅባት እህሎች መቋረጡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታወቁ። በስድስት ክልሎች 9.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ተረጂዎች አሁንም ድረስ የእርዳታ አቅርቦትን በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም ድጋፉ በተያዘው መስከረም ወር በአቅርቦት እጥረት ምክንያት መስተጓጎሉን ድርጅቱ ገልጿል። ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለውን ይህንኑ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች አቅርቦት በቀጣዮቹ ሶስትና ...
Read More »