የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ህገመንግስቱን ጨምሮ የፖለቲካ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ አቀረቡ

ኢሳት ( መስከረም 13 ፥ 2009) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ህገመንግስቱን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ስርዓቶች ማሻሻያ እንዲደረግ ለመንግስት ጥያቄያቸውን አቀረቡ። ላለፉት 5 ቀናቶች ሲካሄድ በቆየው አገር አቀፍ የመምህራን መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የዩኒቨርስቲው መምህራን የጋራ አቋም በመያዝ አበይት የተባሉ ጥያቄዎች ለመንግስት እንዲቀርብላቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ከዜና ክፍላችን ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ መምህራን አስረድተዋል። የመንግስት ተወካዮች ለመወያያ ያሏቸውን ነጥቦች ለመምህራኑ ቢያቀርቡም ተሳታፊ ...

Read More »

በጎንደር ጸዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ አቶ አለምነህ ዋሴ የተባሉት የሃገር ሽማግሌ በደህንነቶች ታፈኑ

ኢሳት ( መስከረም 13 ፥ 2009) በጎንደር ጸዳ ወረዳ አካባቢ የሃገር ሽማግሌ የነበሩት በህወሃት ደህንነቶች ታፈኑ።  አቶ አለምነህ ዋሴ የተባሉት የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የጸዳ ወረዳ ተወካይ በደህንነቶች የታፈኑት አዲስ አበባ ለስራ በሄዱበት ሆቴል ውስጥ ነው። እስካሁን የት እንዳሉ ያልታወቁት አቶ አለምነህ፣ ቤተሰቦቻቸው እየፈለጓቸው እንደሆነ ተነግሯል። ህወሃት መራሹ መንግስት በርካታ ዜጎች በተለያየ ስፍራ እየታፈኑ እየተወሰዱ ሲሆን፣ የት እንዳሉ የማይታወቁ ...

Read More »

በኦሮሚያ ምስራቅ አርሲ አራት የአጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደላቸው ተገለጸ

ኢሳት ( መስከረም 13 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዛሬ አርብ እለት አራት የአጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደላቸው ታወቀ። አንደኛው ደግሞ መማረኩን የአይን ምስክሮች በምስል አስደግፈው ለኢሳት አድርሰዋል። የተማረከው የሰራዊት አባል ለማስለቀቅ በሚል ተጨማሪ ሃይል ወደ ስፍራው መድረሱና ተኩስ መቀጠሉን ለመረዳት ተችሏል። በምስራቅ አርሲ አጄ አካባቢ ልዩ ስሙ ቀሲሳ ተራራ በተባለ አካባቢ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በሚል በአጋዚ ...

Read More »

የስራ ማቆም አድማው ለአምስተኛ ቀን ቀጥሎአል

መስከረም ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ለ5ኛ ቀን ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ዛሬም የንግድ ድርጅቶችን ለማስከፈት ጥረት ሲያድረጉ ቢውሉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። እሁድ ማንኛውም የንግድ ድርጅት ይከፈታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣  የንግዱ ማህበረሰብ ህዝባዊ እንቢተኝነቱን በመምራትና በማስተባበር እያደረገ ያለው ድጋፍ አስገራሚ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ሰዎች ገልጸዋል። በጎንደር፣ ...

Read More »

በአምባ ጊዮርጊስ አካባቢ የነበሩ ወታደሮች ጠፉ

መስከረም ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ለዛሬ አጥቢያ በአምባጊዮርጊስ አካባቢ ጥበቃ ሲያደርጉ ከነበሩት ወታደሮች መካከል በርካታ ወታደሮች ጠፍተው ማደራቸውን የደረሰን መረጃ የመለክታል። ለደህንነት ሲባል ቁጥር እንዳይጠቀስ የጠየቁት የመረጃ ምንጮች፣ ከጠፉት ወታደሮች መካከል አንደኛው ዛሬ  መንገድ ላይ በመያዙ በአሳሽ ወታደሮች ክፉኛ ተደብድቦ ሆስፒታል ገብቷል። ሌሎቹ ግን ማምለጣቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በፍኖተሰላም ሰሞኑን 8 ወታደሮች መጥፋታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ...

Read More »

በባህር ዳር ከተማ ድባንቄ መድሃኒ አለም በመባል በሚታወቀው የቀብር ቦታ ሌሊት ሌሊት ያልታወቁ ሰዎች እንደሚቀበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ተናገሩ፡፡

መስከረም ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃይማኖቱ አባቶች እንደሚሉት  በየቀኑ ከሶስት እስከ አምስት የሚደርሱ አስክሬኖችን የመንግስት ወታደሮች ማንም በማያይበት  ሰዓት አምጥተው የቀብራሉ፡፡ አባቶቹ  በሌሊት ማህሌት ለማድረስ በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት ከባህር ዳሩ መኮድ የጦር ካምፕ አካባቢ በሚመጡ ፒክ አፕ መኪናዎች ተጭነው የሚመጡ አስክሬኖች እንደሚቀበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ ባህርዳርን ጨምሮ ከተለያዩ የአማራ ከተሞች በሰላማዊ ሰልፍ ተሳትፋችኋል በሚል የሚታፈሱት ወጣቶች አስከሬን ...

Read More »

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተመድ ጉባዔ ላይ የማህበራዊ ድረገጾች በሃገሪቱ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ

ኢሳት (መስከረም 12 ፥ 2009) በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የማህበራዊ ድረገጾች በሃገሪቱ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ሲሉ ቅሬታን አቀረቡ። በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ዙሪያ አጨቃጫቂ ነው የተባለ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። በዚሁ የማህበራዊ ድረገጾች ዙሪያ በጉባዔው ንግግርን ያደረጉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ድርጊቱ የተለያዩ ...

Read More »

በጎንደር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ቃጠሎ ሊያደርሱ ነበር የተባሉ ሰዎች ተያዙ

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 4 ቀናት የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ በምትገኘው ጎንደር ከተማ ትናንትና ዛሬ የገበያ ቦታዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችን እንዲሁም መስሪያ ቤቶችን ሊያቃጥሉ ነበር የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ግለሰቦቹ በህወሃት የተላኩ መሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ከትግራይ ክልል እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት የይለፍ ወረቀት እንዳላቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል። የአንዲት ሴትና የአንድ ወንድ ወጣት መያዛቸውን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ወላጆች ፌደራል ፖሊሶችን ምከሩልን ሲሉ ተናገሩ

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለተሞች የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወላጆች ለስብሰባ እየተጠሩ ልጆቻቸውን እንደሚክሩ ተነግሮአቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረገው ቅስቀሳ አገራችንን ለብጥብጥ እየዳረጋት በመሆኑ፣ ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት በሚገቡበት ወቅት ረብሻ እንዳያስነሱና ማህበራዊ ሚዲያውን እንዳይከታተሉ ምከሩዋቸው ሲሉ ተናግረዋል። በእዛኛው ወላጅ የሚጣ ለውጥ የለም በሚል ስብሰባውን አለመሳተፋቸውን የገለጹት ወላጆች መንግስት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ የተነሱትን ችግሮች ...

Read More »

በፍኖተሰላም 8 ወታደሮች እስከ እነ ሙሉ ትጥቃቸው በመጥፋታቸው እየተፈለጉ ነው

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ላይ ለጥበቃ የተሰማሩት ወታደሮች መጥፋታቸው ታውቋል። አካባቢው በአጋዚ ወታደሮች እየታሰሰ ሲሆን እስካሁን ድረስ ያሉበት አልታወቀም። ከጠፉት 8 ወታደሮች መካከል አንዷ ሴት ናት። በሌላ በኩል የአማራ ክልል አዲስ የአድማ በታኞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል። ክልሉ ባጋጠመው ከፍተኛ የአድማ በታኝ ሃይል የተነሳ አዲስ ቅጥር ለመፈጸም ማስታወቂያ አውጥቷል። ማስታወቂያው ከመስከረም 12 ...

Read More »