የመልቀቂያ ወረቀት ያቀረቡ በርካታ ወታደሮች በመለስ አጽም እየተባሉ እንዲቆዩ እየተለመኑ ነው

መስከረም ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የ7 አመታት የከንትራት ጊዜያቸውን የጨረሱ ወታደሮች መልቀቂያ በብዛት እያስገቡ ቢሆንም፣ አዛዦቹ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶ እግራቸው ስር በማንጠፍ “ የመለስን ፎቶ ተራምደኸው እለፍ፣ በመለስ አጽም ይዘንሃል” እየተባሉ ኮንትራታቸውን እንደሚያራዝሙ የመከላከያ ምንጮች ገለጹ” በአሁኑ ሰአት መከላከያው ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ወታደሮች በአማራ ...

Read More »

በጎንደር መስተዳድሩ ተቃውሞ ባሰሙ ድርጅቶች ላይ ቅጣት እየጣለና ድርጅቶች እንዳይከፈቱ እያገደ ነው

መስከረም ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ትግል ተከትሎ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለሳምንታት ያካሂዱት የስራ ማቆም አድማ ያበሳጫቸው የክልሉ ባለስልጣናት፣ የንግድ ድርጅቶች እየመረጡ በመክፈትና እየመረጡ ቅጣት በመጣል ፣ ህዝቡን ለመከፋፈል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነዋሪዎችን አበሳጭቷል። አንዳንድ የባጃጅ አሽከርካሪዎች 500 ብር እና ለሁለት ሳምንታት ያክል ስራ እንዳይሰሩ የታገዱ ሲሆን፣ አንዳንድ ሆቴሎች ደግሞ እንዳይፍቱ ...

Read More »

ከሶማሊ ፣ ድሬዳዋና ሌሎች ብሄረሰቦች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌ የተባሉ ሰዎች ወደ ትግራይ በመሄድ ለህወሃት ድጋፋቸውን እንዲገልጹ እየተደረገ ነው

መስከረም ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጥር አነስተኛ ብሄረሰቦችን ይወክላሉ የተባሉ የአገር ሽማግሌዎች እየተመረጡ ወደ መቀሌ በመሄድ በኦሮምያና አማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በማውገዝ ለህወሃት ያላቸውን ድጋፍ ይገልጻሉ ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉ አስተዳዳሪዎች የአገር ሽማግሌዎችን መርጠው ወደ መቀሌ በመላክ፣ ከአማራ ክልል ተፈናቀሉ ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች ድጋፋቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ህወሃት ከአማራ እና ኦሮሞ ህዝብ ውጭ ሌሎች ክልሎች ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ነው

መስከረም ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት ስታደርግ ነበር በሚል በመንግስት የደህንነት ሃይሎች ከመንገድ ላይ ታፍኖ የተወሰደውና በሃሰት የሽብር ክስ ተከሶ  ከዓመት ከመንፈቅ በላይ በእስር ሲንገላታ የቆየው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ ለሕይወቱ አስጊ በሆነ ጽኑ ሕመም ላይ መሆኑ ታውቋል። በእነ ከድር መሀመድ የክስ መዝገብ በሽብር ክስ የተከሰሰው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ከቂሊንጦ የእሳት አደጋ ቢተርፍም ...

Read More »

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት 8 የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2009) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰርቀሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በነዋሪዎችና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 8 የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉት በስፍራው ወርቅ ለማውጣት በሚል በቅርቡ ከ1ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች መስፈራቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ አለመግባባት መሆኑ ተነግሯል። በዚሁ ግጭት ከተገደሉት የጸጥታ ሃይሎች በተጨማሪ ከ20-30 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ ...

Read More »

ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ተሰጣቸው ተባለ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 20089) ከ30 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሃሙስ የሌተናል፣ የሜጀርና፣ የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው መንግስት አስታወቀ። በሃገሪቱ ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሾመ የማዕረግ እድገት ተሰጥቷቸዋል ከተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች መካከል የሜጀር ጄነራልነት ማዕረግ የነበራቸው ገብራት አየለ ቢጫ በብቸኝነት የሌተናል ጀኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። በብርጋዴር ጀነራልነት ሲያገለግሉ ነበር የተባሉ 12 ወታደራዊ መኮንኖች ደግሞ የሜጀር ጀኔራልነት ሹመትን ያገኙ ሲሆን፣ 25 ኮሎኔሎች እንዲሁ ...

Read More »

በቃሊቲ በሚገኙ እስረኞች ላይ የሚደረገው ጫና መቀጠሉ ተነገረ

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2009) በቃሊቲ ወህኒ ቤት በሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚፈደረገው ጫና እና ማሰቃየት መቀጠሉ ታወቀ። የ18 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት ላለፉት 5 አመታት በዚህ ወህኒ ቤት በሚገኘው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉን እንዲሁም የማበሳጨት ዕርምጃዎች መጨመራቸውን መረዳት ተችሏል። በቅድሚያ የጻፋቸውን ማስታወሻዎች፣ በኋላም ማናቸውንም የጽህፈት መሳሪያና ባዶ ወረቀቶች ጭምር የነጠቁት የእስር ቤቱ አዛዦች የተለያዩ ...

Read More »

ለቻይና ኩባንያ ልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ሊሰጥ የታቀደው መሬት ለኑሮ ምቹ አይደለም ተባለ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአንድ የቻይና ኩባንያ ለልማት ሊሰጥ ካሰበው ቦታ ላይ እንዲነሱ ጥያቄ የቀረበላቸው በርካታ አርሶ አደሮች ሊሰጣቸው የታቀደው ተለዋጭ ቦታ ለኑሮ ምቹ አይደለም በማለት ተቃውሞን አቀረቡ። የከተማዋ አስተዳደር ሁአጂየን ለተሰኘው ኩባንያ በተለይም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለቆዳ ኢንዱስትሪ ፓርት ግንባታ 164 ሄክታር መሬት ባለፈው አመት ማስረከቡ ይታወሳል። የከተማዋ አስተዳደር ...

Read More »

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነጻነት ከሌለባቸው አገራት አንዷ ናት ሲል አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት የሌለባቸው ሃገራት ተብለው ከተፈረጁ የአለማችን ሃገራት መካከል አንዷ ሆና መገኘቷን አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም ይፋ አደረገ። ከ90 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ሃገሪቱ ላለፉት 10 አመታት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን አስመዝግባለች ተብላ ቢነገርላትም፣ ኢኮኖሚያዋ በአብዛኛው ነጻ ያልሆነ ሆኖ በጥናት መገኘቱ በ186 ሃገራት ላይ ያካሄደውን የጥናት ግኝት በህዝብ ያቀረበው ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን የተሰኘ ተቋም አስታውቋል። በነፍስ ...

Read More »

የጅምላ እስርና ግድያ እየፈጸሙ ያሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግድያና ጅምላ እስር እየፈጸሙ ያሉ ባለስልጣናት ሆነ የጸጥታ ሃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ጠየቀ። አለም አቀፍ ህብረት ለኢሳት በላከው መግለጫ ህዝብን ማገልገል የሚገባው መንግስት ዜጋውን እየጨፈጨፈ መቀጠል ስለለለበት ስልጣንን መልቀቅ ይኖርበታል ብሏል። ከዚህ በኋላም የሚፈጸም ግድያና ጅምላ እስር በአስቸኳይ እንዲቆም አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ...

Read More »