መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች በአየር ጤና ፣ ጆሞ፣ አስኮ ፣ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ኮልፌ፣ በአለም ገና፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሎአል። በርካታ ንብረት ወድሟል። የንግድ ድርጅቶች ተዘግተዋል። ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አቁመዋል። መርካቶ የሚገኙ ሱቆችና ሆቴሎች ተዘግተዋል። ቡሌቦራ ከተማም እንዲሁ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን የትናንትናውን ጨምሮ 2 ...
Read More »የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባቸውን ጀመሩ
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 36ቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ በክልሉ ፕ/ት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ጠንካራ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ክልሉን በደንብ አልመራነውም ልንለቅ ይገባል በማለት ሁሉም አባላት ተጠያቂዎች መሆናቸውን ገልጿል። አቶ ገዱ ብአዴን ለክልሉ ያመጣው ልማት የለም፣ ተገኘ የተባለውም ለውጥ ዘመን ያመጣው ነው ብለዋል ።
Read More »የእስራኤል መንግስት ዜጎቹ ወደ አማራን ኦሮሚያ ክልሎች እንዳይጓዙ አስጠነቀቀ
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስመልክቶ የእስራኤል መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤላዊያን ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከሚያደርጓቸው ጉዞዎች እንዲታቀቡ አሳሰበ። የውጭጉዳይ ሚንስተር መስሪያ ቤቱ ከሁለቱ ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ፣ በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬኒያ ድንበር አስር ኪሎሜትሮች በሚገኙ አካባቢዎች እንዳይሄዱ አስጠንቅቋል። በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ የተፈጸመውን እልቂት ተከትሎ በአካባቢው ሰላም በመደፍረሱ ዜጎቹ ...
Read More »መምህር ስዩም ተሾመ ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ እስካሁን ያለበት አይታወቅም
መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአንቦ ዩንቨርሲቲ ወሊሶ ካንፓስ መምህር እና በተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ በዓምደ መረብ ጸሃፍነት በመሆን በኢትዮጵያ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ አፈናዎችና ኢሕገመንግስታዊ የመብት ጥሰቶችን በመጋለጥ የሚታወቀው መምህር ስዩም ተሾመ ከመኖሪያ ቤቱ በደኅነትና በአጋዚ ወታደሮች ታፍኖ ተወስዷል። እስካሁንም ታፍኖ ከተወሰደ ከተወሰደ በኋላ ያለበት ሁኔታ እንደማይታወቅና ለፍርድ አለመቅረቡ እንዳሰጋው ሲፒጄ አስታወቀ። ስዩም ተሾመ ስለመብት በመጻፉ ...
Read More »በቢሾፍቱ ሰኞ ረፋድ ድረስ 23 ተጨማሪ አስከሬኖች መገኘታቸው እማኞች ገለጹ
ኢሳት (መስከረም 23: 2009) ሰኞ ረፋድ ድረስ ተጨማሪ 23 አስከሬን በእሬቻ በዓል አከባበር ስፍራ በነበረ ጉድጓድ ውስጥ መውታጣቸውን እማኞች ለዜና ክፍላችን አስታውቀዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የበዓሉ ታዳሚዎች ዕሁድ ምሽት ጀምሮ የሞቹ ሰዎችን ለማፈላለግ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ በአጠቃላይ ተጨማሪ የ26 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ገልጸዋል። መንግስት ድርጊቱን ለመሰፋፈን ጥረት በማድረግ ላይ በመሆኑ እማኝነታችንን መስጠት እንፈልጋለን ያሉት ግለሰቦች በስፍራው የነበረው ጉድጓድ ...
Read More »በእሬቻ በዓል ላይ ባለቤታቸውንና አንድ ልጃቸውን ያጡት አንድ የሰንዳፋ ከተማ ነዋሪ በመንግስት የተወሰደው ጭፍጨፋ “የውጭ ወራሪ ሃይል” ድርጊት ይመስል ነበር ሲሉ ገለጹ
ኢሳት (መስከረም 23: 2009) ከ30 አመት በላይ በትዳር አብረው የኖሩ ባለቤታቸውንና አንዲት ልጃቸውን በአደጋው ያጡ የሰንዳፋ ከተማ ነዋሪ እሁድ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተወሰደውን ዕርምጃ “የውጭ ወራሪ ሃይል” ድርጊት የሚመስል ነበር ሲሉ ገለጹ። የዘጠን ልጅ አባት የሆኑትን በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ የሚገኙት አቶ ደረጀ ኡርጊ በሞት የተለዩአቸውን ባለቤታቸውንና የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበረችን ልጃቸው ከአፍንጫቸው ጥቁር ፈሳሽ ይወጣ እንደነበር ከዜና ክፍላችን ጋር ...
Read More »በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአውስትራሊያ መንግስት ህወሃት/ኢህአዴግ የሚፈጽመውን የዘር ጭፍጨፋ እንዲያስቆም መጠየቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 23: 2009) ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ የሆነ ኢትዮጵያውያን የሃገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ በመፈጸም ላይ ነው ያሉትን የሩዋንዳ አይነት የዘር ማጥፋፍ ድርጊት ለማስቆም ዕርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውን የአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን ሰኞ ዘገቡ። ዕሁድ በቢሾፍቱ ከተማ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ተቃውሞ ተከትሎ በመዲናይቱ ሲድኒ ከተማ የሃዘን መግለጫ ስነስርዓትን ያካሄዱት ኢትዮጵያውያን በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በዘር ማጥፋት ድርጊት መሰማራቱን እንደገለጸ SBS የቴሌቪዥን ...
Read More »ከእሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ የተገደሉ ሰዎችን ድርጊት በማውገዝ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሄዱ
ኢሳት (መስከረም 23: 2009) በቢሾፍቱ ከተማ ዕሁድ ከእሬቻ በዓል አከባበር ጋር በተገናኘ የተገደሉ ሰዎችን ድርጊት በማውገዝ በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በሃዘን ድባብ ውስጥ በምትገኘው የደብረዘይት ከተማ እንዲሁም ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተሞችና በምስራቅ አርሲ ዞን ከእሁድ ጀምሮ ህዝቡ ተቃውሞን እያሰማን እንደሚገኝ ነዋሪዎችን ለኢሳት አስታውቀዋል። በምስራቅ አርሲ ዞን ስር በሚገኙ የገጠር ከተሞች እንዲሁም በሻሸመኔና አጎራባች ...
Read More »በቢሾፍቱ ከተማ በእሬቻ በዓል ላይ የሞቱ ተጨማሪ አስከሬኖች መገኘታቸው ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 23: 2009) በቢሾፍቱ ከተማ ዕሁድ ከእሬቻ በዓል አከባበር ጋር በተገናኘ የሞቱ ሰዎች ተጨማሪ አስከሬን ሰኞ ጠዋት መገኘቱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡ በርካታ ሰዎች በሆራ ሃይቅ ዙሪያ በመሰባሰብ በሞት የተለዩ ሰዎችን በመፈለግ ላይ ሲሆኑ በትንሹ የ10 ሰዎች አስከሬን ከ24 ሰዓት በኋላ መገኘቱን የከተማዋ ነዋሪዎች አስታውቀዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ባይሳ በበኩላቸው፣ አደጋው በደረሰ ማግስት ...
Read More »በኢሬቻ በአል ላይ የደረሰውን እልቂት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞች ተካሄዱ
መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 22 በቢሾፍቱ በኢሬቻ በአል ላይ በተገኙ በመቶዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ እልቂት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። ዜናው ከፈጠረው ድንጋጤ በተጨማሪ ፣ በበርካታ ከተሞች ህዝቡ ቁጣውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጽ አርፍዷል። እናቶችና አባቶች ለኢሳት ስልክ በመደወል ሀዘናቸውን መቋቋም እንደተሳናቸው ሲገልጹ አርፍደዋል። በቡሌ ሆራ መላው የከተማው ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ በመውጣት ተቃውሞውን ...
Read More »