ኢሳት (መስከረም 25 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል በአዲስ መልክ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃን እንዲወስዱ ረቡዕ በድጋሚ አሳሰበ። ከቀናት በፊት በቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ያወሳው የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርጊቱን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በምስራቅ አርሲ ዞን ስር በምገኙ የሻሸመኔ፣ ...
Read More »በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ህዝባዊ ተቃውሞች ተጠናክረው ቀጥለዋል
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም ፋብሪካዎችና ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ከፍተኛ ተቃውሞ በተካሄድባቸው ወንጂ እና ሶደሬ አካባቢዎች የአጋዚ ወታደሮች በተኮሱዋቸው ጥይቶች ቁጥራቸው በው ያልታወቀ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የስኳር ፋብሪካው ንብረት የሆነው የሸንኮራ አገዳ እርሻ እንዲሁም የሼክ ሙሃመድ አላሙዲ የከብት እርባታ ድርጅት መውደሙን የካባቢው ነዋሪዎች ...
Read More »የአውሮፓ ኅብረት የእርቅ ሂደት እንዲጀመር ጠየቀ
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመታዊው የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ባሕላዊ ክብረበዓል ላይ ለሞቱና አካላቸውን ላጡ ጉዳተኞች እና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሃዘን የገለጸው ህብረቱ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ሁሉንም ያሳተፈ እርቅ ያስፈልጋል ብሎአል። በዚህ በኩል ህብረቱ ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጿል። በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፓርላማ አባሏ ወ/ሮ አና ጎሜዝ በኢሬቻ በአል ላይ የተፈጸመውን እልቂት በማስመልከት ለፓርላማ ...
Read More »ገዢው ፓርቲ የሞባይል አፈና አካሄደ
መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በኦሮምያ እና በአዲስ አበባ አካባቢዎች የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። በአማራ ክልል ህዝባዊ ንቅናቄዎች በሚካሄዱበት ወቅት በተመሳሳይ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል። በአዲስ አበባ እና ዙሪያ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የፎቶ ግራፍ እና የቪዲዮ መልክቶችን መላክ አለመቻላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ፍጥነት ቢቀንስም የኢንተርኔት ...
Read More »የህብረተሰባዊነት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (መስከረም 25 ፥ 2009) ሃገራችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬ፣ ጀግና እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን መካከል በግንባት ቀደምትነት የሚጠቀሱት የህብረተሰባዊነት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ በአሜሪካ አገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የደረሰን መረጃ የመለክታል። ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ከኢትዮጵያ አየር ሃይል የበረራ ጀግኖች መካከል አንዱ ነበሩ። የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከመቀላቀላቸው በፊት በ1956 ዓም ሃረር አካዳሚ ...
Read More »በአዲስ አበባ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009) የእሬቻ ዕልቂትን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በመዛመት ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ማክሰኞ በመዲናይቱ አዲስ አበባ መቀስቀሱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ረፋድ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ በአየር ጤና ብስራተ-ገብርዔል አካባቢ ተዛምቶ ማምሸቱ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በስም ያልገለጧቸው ሃይሎች ሁከት ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል ሲል ማክሰኞ ምሽት ድርጊቱን አረጋግጧል። በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተስተዋለውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ ...
Read More »በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009) ማክሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች የተጀመረው ተቃውሞ በዙሪያዋ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች መዛመቱን እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ማከሰኞች ረፋድ በከተማዋ ልዩ ስሙ ሞጆ መንደር እንዲሁም አየር ጤና አካባቢ ታይቶ የነበረው ተቃውሞ በቡራዩ አለም ገና እና በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ተባብሶ መቀጠሉን እማኞች ገልጸዋል። በቡራዩ ከተማ የተጀመረውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ ወደ ከተማዋ የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶች ...
Read More »በአርሲ እና በቦረና ዞኖች በሚገኙ ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተባብሰው መቀጠላቸው ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል ዕሁድ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ማክሰኞ ሶስተኛ ቀን በአርሲ እና በቦረና ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተባብሱ መቀጠሉን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። በቡሌ ሆራ ማክሰኞ ጠዋት በነዋሪዎችና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና የወረዳው ፖሊስ ጣቢያ በተቃውሞ ምክንያት መውደሙን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ዕሁድ በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን ...
Read More »በእሬቻ በዓል ላይ የጸጥታ ሃይሎች የከፈቱት የተኩስ ዕርምጃ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ
ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009) በቢሾፍቱ ከተማ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አደጋ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን ለመቆጣጠር ሲሉ በከፈቱት የተኩስ ዕርምጃ መሆኑን መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ማክሰኞ አስታወቀ። ፍሪደም ሃውስ የተሰኘው ይኸው የሰብዓዊ መብት ተቋም የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ፈቃደኛ መሆን ይኖርበታል ሲል ጥሪውን አቅርቧል። የመንግስት ባለስልጣናት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች በበዓሉ አከባበር ...
Read More »የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ያለውን የመብት ትግል እንደሚደግፉ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ገለጹ
ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ያለውን የመብት ትግል እንደሚደግፉ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ገለጹ። ህዝቡ በደል ሲበዛበትና ስቃይ ቢበረታበት መነሳቱን ለዜና ሰዎች ገልጸዋል። የአፋርም ህዝብ በትግሉ ተገቢ ሚናውን እንደሚጫወት አስታውቀዋል። የአፋር ህዝብ መንፈሳዊ መሪ የሆኑትና ከአባታቸው ከሱልጣን አሊሚራህ መንበሩን የተረከቡት ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ፣ የአፋር ህዝብ እየደረሰበት ያለው በደል እጅግ የበረታ መሆኑን በዝርዝር አመልክተው፣ የአፋር ህዝብ እንደኦሮሞችና እንደ አማሮች ...
Read More »