መስከረም 26 ፥ 2009) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በኦሮሚያ ክልል ዳግም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ክልሉን አጠቃላይ ቀውስ ውስጥ መክተቱንና ድርጊቱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ሃሙስ ገለጠ። በአብዛኛው የክልሉ ዞኖች ውስጥ ህዝባዊ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ መንግስት ተቃውሞን ለመቆጣጠር የሃይል ዕርምጃና የጥይት አማራጮችን እየወሰደ እንደሚገኝ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ከኢሳት ጋር በወቅታዊ የኦሮሚያ ክልል ዙሪያ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። በምስራቅ አርሲ ...
Read More »በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ቀጥለዋል
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከኢሬቻ በአል ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን እልቂት ተከትሎ በኦሮምያ የተቀጣጠለው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን፣ በምእራብ አርሲ አጄ ከተማ ደም አፋሳሽ ሆኖ መቀጠሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ የጦር መሳሪያ የነገቡ ነዋሪዎች ራሳቸውን ለመከላከል ከአጋዚ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውንና ቁጥራቸው 17 የሚሆኑ ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።በመጀመሪያው ዙር የመጡ ወታደሮች ...
Read More »በኢሬቻ በአል ላይ የተሰው ኢትዮጵያውያንን አላማ ከግብ እንደሚያደርሱ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በኤሪቻ በአል ላይ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ገልጸው ንቅናቄያቸው“ ወገኖቻችን የተሰውለትን የፍትህ፣ የነፃነትና የእኩልነት ዓላማ ከዳር እስከሚደርስ ድረስ እስከመጨረሻው የደም ጠብታ እንታገላለን ብለዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ዝግጅታችንን በቶሎ አጠናቀን ሊደበቅ በማይችልበት ሁኔታ በግልጽ የምንወጣበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ ያሉ ሲሆን፣በወያኔ ስር ተጠርንፎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደር አሁንም ...
Read More »ገዢው ፓርቲ የኒዮርክ ታይምስና ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኞችን ኒዮርክ ላይ ጠርቶ ገለጻ ሰጠ
መስከረም ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኒዮርክ የሚገኘው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቆንስላ ኒዮርክ ታይምስና ዋሽንግተን ፖስት የተባሉት ታዋቂ የመገናኛ ብዙሃንስለኢትዮጵያ መልካም ዘገባ እንዲያቀርቡ ማነጋገሩን አምባሳደር ተቀዳ አለሙ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከላኩት እና ኢሳት እጅ ከገባው የአመታዊ የስራ ሪፖርት ለመረዳት ተችሎአል። አምባሳደር ተቀዳ New York Times እና Washington Post የተሰኙ 2 የሚዲያ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር ...
Read More »የእስራዔል መንግስት ቤተ-እስራዔላውያን ኢትዮጵያውያን ወደ እስራዔል ማጓጓዝ እንዲጀምር ይፋ አደረገ
መስከረም 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ባለው የጸጥታ ችግር ዜጎች ወደ አማራ ክልል እንዳይጓዙ የሰጠውን የእስራዔል መንግስት ዕሁድ ጀምሮ ቤተ-እስራዔላውያን ኢትዮጵያውያን ወደ እስራዔል ማጓጓዝ እንዲጀምር ሃሙስ ይፋ አደረገ። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከበጀት ምደባ ጋር በተያያዘ ተፈጥሯል ባሉት ምክንያት ቤተ-እስራዔላውያኑን የማጓጓዙ ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ከወራት በፊት ውሳኔ ማስተላለፋቸው ይታወሳል። ይሁንና የእስራዔል የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የፊታችን ዕሁድ በመጀመሪያው ጉዞ 78 ተጓዦች ወደ ...
Read More »በፖታሽ ማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራ የእስራዔል ኩባንያ ፕሮጄክቱን መዝጋቱን አስታወቀ
መስከረም 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በፖታሽ የማዕድን ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ የእስራዔል ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስት የገባውን ቃል ተግባራዊ አላደረገም በማለት ፕሮጄክቱን ለመዝጋት ወሰነ። ኩባንያው የደረሰውን ውሳኔ ተከትሎ ለፕሮጄክቱ የመደበው 179 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ እንዳይንቀሳቀስ ሲል ነው ዮርክ ከተማ ለሚገኘው የአለም አቀፉ የንግድ ልውውጥ ማዕከል ማስታወቁን ግሎብስ የተሰኘ የእስራዔል የቢዝነስ መጽሄት ሃሙስ ዘግቧል። ILC የሚል መጠሪያ ያለው ኩባንያው የኢትዮጵያ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለ5ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ
መስከረም 26 ፥ 2009) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ዳግም የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሃሙስ ለአምስተኛ ቀን ቀጥሎ በአርሲ ዞን ስር በምትገኘው የአጄ ከተማ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ነዋሪዎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ በቢሾፍቱ ከተማ ከእሬቻ አከባበር ወቅት ጋር በተገናኘ የደረሰውን ዕልቂት ተከትሎ በምዕራብና ምስራቅ አርሲ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ መቀስቀሱን መዘገባችን ይታወሳል። ይኸው ተቃውሞ ዕልባትን ...
Read More »በእሬቻ የተወሰደውን የግድያ ዕርምጃ በተመለከተ ማጣራት እንዲካሄደበት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ
ኢሳት (መስከረም 25 ፥ 2009) በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ የደረሰው ዕልቂትና በተለያዩ ከተሞች የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን ለመቆጣጠር እየወሰዱት ነው ያለው የሃይል ዕርምጃ ሙሉ ማጣራት እንዲካሄደበት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ረቡዕ ጠየቀ። የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን ዕርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ያሳሰበው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በተፈጸሙ ግድያዎች ዙሪያ ማጣራት እንዲካሄድበት ግዴታ እንዳለበት ገልጿል። በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን ዕልቂት ተከትሎ ...
Read More »በኢትዮጵያ ኢንተርኔት መቋረጡን ቢቢሲ ዘገበ
ኢሳት (መስከረም 25 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ማክሰኞ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግልቶ ማቋረጡን የብሪታኒያው አለም አቀፍ የማሰራጫ ጣቢያ (BBC) ረቡዕ ዘገበ። ተቃውሞውን ምክንያት በማድረግ በተወሰደው በዚሁ ዕርምጃ በመደበኛና በተንቀሳቃሽ የስልክ አገልግሎት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሲያገኙ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አገልግሎቱ እንደተቋረጠባቸው ታውቋል። በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ የላቀ ነው የተባለን የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ...
Read More »በቢሾፍቱ ከደረሰው የሞት አደጋ የተረፉትን ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት በፍለጋ የተሰማሩ ሰዎች ሆስፒታሎችና ፖሊስ ጣቢያዎችን እየጠየቁ መሆኑ ተነገረ
ኢሳት (መስከረም 25 ፥ 2009) ከቀናት በፊት በቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ በእሬቻ በዓል ወቅት ከተፈጠረው ዕልቂት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት ያልቻሉ በርካታ ሰዎች ለአራተኛ ቀን በከተማዋ በሚገኙ ሆስፒታሎችና ፖሊስ ጣቢያዎች ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸው ታወቀ። የከተማዋ ሆስፒታል ህክምና የተደረገላቸው ወደ 100 አካባቢ ሰዎች ህክምናቸውን ጨርሰው እንደወጡ ቢያሳውቅም አሁንም ድረስ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ የገቡበት ያልታወቀ የቤተሰብ አባሎቻቸውን በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል። ...
Read More »