ኢሳት (መስከረም 30 ፥ 2008) የግብጽ መንግስት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጣልቃ አለመግባቱን ሰኞ ለኢትዮጵያ በሰጠው ምላሽ አስተባበለ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባ አህመድ አቡ ዘይድ ሃገራቸው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳልገባች በመግለጽ በሁለቱም ሃገራት መካከል በከፍተኛ አመራሮች ምክክር በመካሄድ ላይ መሆኑን ለአዣንስ ፍራስ ፕሬስ አስታውቀዋል። የኢትጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ግብጽ በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ...
Read More »“የቢሾፍቱ እልቂት ከደረሰ በሁዋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል”
መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያንንና የአለምን ህዝብ ድንጋጤ ውስጥ የከተተው የቢሾፍቱ እልቂት ከተከሰተ በሁዋላ የተነሱ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ለማፈን የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የኢሳት ወኪሎች ያሰባሱበዋቸው መረጃዎች አመልክተዋል። ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ በተካሄደባቸው በምስራቅ ሸዋና በምዕራብ አርሲ እልቂቱ ከፍተኛ እንደነበር ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በሊበን ዝቋላ ወረዳ ለተከታታይ 5 ቀናት በተደረገው ...
Read More »ገዢው ፓርቲ ከወጣቶች ጋር እርቅ ለመፍጠር ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ አንዳሳ በሚባለው አካባቢ ከጎበዝ አለቆች ጋር እርቅ መፍጠር እንፈልጋለን በሚል ገዢው ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ ወጣቶች ውድቅ አደረጉት። ወጣቶቹ፣ ማንኛውም ሰው፣ ፖሊስም ሆነ ወታደር ረብሻ ቢፈጥር እርምጃ እንወስዳለን በማለት የተማማሉ ሲሆን፣ አካባቢያችንን ከእንግዲህ እኛ የመረጥናቸው እንጅ እናንተ የምትመርጡት አያስተዳድረውም በማለት በፖሊሶች እና በአመራሮች ላይ ድንጋይ በትኖ አባሯቸዋል። ...
Read More »የኩዌት መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ እገዳ ጣለ
መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ተከትሎ የደኅንነት ስጋት እየጨመረ ስለመጣ ኩዌታዊያን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ሲሉ በኢትዮጵያ የኩዌት አንባሳደር ራሽድ አልሃጅሪ አስጠነቀቁ። ኩዌታዊያን በኢትዮጵያ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጉዞዎች እንዲሰርዙና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትም ዜጎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች በአፋጣኝ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲሉ አንባሳደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በመላው ኢትዮጵያ እሁድ እለት ለስድስት ወራቶች ...
Read More »ተመድ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግር እያሳሰበኝ ነው አለ
ኢሳት (መስከረም 27 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግር እያሳሰበው መሆኑን ገለጸ። የኮሚሽኑ ቃል-አቀባይ ሪፖርት ኮልቪል ከጄኔቫ እንደገለጹት በእሬቻ በዓል ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን እልቂት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል እና በደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ ያለው የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መጥቷል። በተለይም በቢሾፍቱ እሬቻ በዓል ላይ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በውል አለመታወቁ እና በመንግስት ላይ እምነት መታጣቱ የጸጥታ ...
Read More »በምዕራብ አርሲ የአጋዚ ወታደሮች ከፍተኛ ጭፍጨፋ ማካሄዳቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
መስከረም ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርሲ ነገሌ እሰከ ዛሬ የቀጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ ከ 40 በላይ ሰዎች መግደላቸውንና በርካታ ዜጎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሻላ ወረዳ አጄ ከተማ ደግሞ 48 ሰዎች መገደላቸውንና የአካባቢው አርሶአደር ታጣቂዎች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃም 22 የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውንም ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል ። ህጻናት፣ አዛውንት፣ ነፍሰጡሮች ሳይቀሩ መገደላቸውን ከዚህም በላይ ...
Read More »በጌዲዮ ዞን ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ የንግድ ድርጅቶች ወደሙ
መስከረም ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በዲላ 6 ሰዎች ተገድለዋል። በዲላና በይርጋጨፌም የንግድ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ግጭቱ የብሄር ግጭት መልክ እንዲይዝ ሆን ተብሎ መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከ1997 ዓም ጀምሮ በዚሁ ቦታ የተነሳ ግጭት መነሳቱን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ችግሩ እንዳይፈታ በማድረጉ የአሁኑ ግጭት መቀስቀሱን ገልጸዋል ።
Read More »ኢንጂነር ሃይሉ ሻወል ትግሉ ፍሬ ሊያፈራ በደረሰበት ሰአት ቢለዩንም፣ አላማቸውን ከግብ እናደርሳለን ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ
መስከረም ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መኢአድን እና ቅንጅትን በመመስረትና በመምራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት የኢንጂኒየር ሃይሉ ከዚህ አለም መለየታቸውን ተከትሎ በአንድ ወቅት የትግል አጋራቸው የነበሩት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተሰማቸውን ከፍተኛ ሀዘን ገለጸዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ኢ/ር ሃይሉ የታገሉለትን አላማ ከግብ እንደሚያደርሱም ገልጸዋል ። በርካታ ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ሃይሉ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በማህበራዊ ሚዲያ በመግለጽ ላይ ናቸው።
Read More »ታዋቂው የፖለቲካ መሪ ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ኢሳት (መስከረም 27 ፥ 2009) በ1928 ዓም በአዲስ አበባ የካ በሚባለው አካባቢ የተወለዱት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሃሙስ መስከረም 26 ቀን 2009 ዓም በ80 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመአድ መስራች፣ ቀጥሎም የመኢአድ በኋላም የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ህይወታቸው ያለፈው ህክምና ሲከታተሉ ከነበሩበት የባንኮክ ታይላንድ ሆስፒታል መሆኑ ታውቋል። የሲቪል ምህንድስና ሙያተኛ ...
Read More »በሰበታ ከተማ 11 ፋብሪካዎች መውደማቸው ተገለጸ
መስከረም 26 ፥ 2009) ከአዲስ አበባ ከተማ ርቀት ላይ በምትገኘው የሰበታ ከተማ ከቀናት በፊት ተካሄዶ በነበረው ተቃውሞ 11 ፋብሪካዎች መውደማቸውንና የንግድ ተቋማት ዝግ ሆነው መቀጠላቸው ታውቋል። በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን ዕልቂት ተከትሎ ሰበታ ከተማን ጨርምሮ በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄደ መሰንበቱ ይታወሳል። ከዚህ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ 11 ፋብሪካዎች እንዲሁም 60 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፖሊስ ሃሙስ ገልጿል። የጨርቃ ጨርቅ የታሸገ ውሃ ...
Read More »