ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥቅምት 1 እስከ 5 በተጠራው የአማራ ክልል የስራ ማቆም አድማ በከተማዋ የሚገኙ ሱቆች ሙሉ በሙሉ የተዘጉ ሲሆን በሶስቱም የባህር ዳር ታላላቅ ገበያዎች ማለትም በአባይ ማዶ በቅዳሜ ገበያና በኪዳነ ምህረት ገበያዎች ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያሳዩ የመጀመሪያው ቀን ተጠኗቋል፡፡ በዋናው የቅዳሜ ገበያ ውስጥ የሚገኙ የአዳራሽ ሱቆችና ልዩ ልዩ የሸቀጥ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በመዘጋት ...
Read More »በታች አርማጭሆ አንድ የፌደራል ፖሊስ ሲገደል በጠገዴም ሌላ ጥቃት ተፈጸመ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርማጭሆ ወረዳ በቅርቡ ከአገዛዙ ታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ ራሳቸውን ያደራጁ የክልሉ ነዋሪዎች ትናንት ሁለት የፌደራል ፖሊሶችን ጭኖ በሚሄድ አንድ መኪና ላይ በፈጸሙት ጥቃት አንደኛው ሲገደል ሌላው ፖሊስ ቆስሏል። በጠገዴ ደግሞ የመንገድ ስራ ለማስጀመር ወደ አካባቢው በተንቀሳቀሱ ባለስልጣናት ላይ ለመውሰድ የታሰበው እቅድ ባለስልጣናቱ መንገድ ቀይረው በመጓዛቸው ሳይሳካለቸው መቅረቱን የገለጹት እነዙህ ሃይሎች፣ ይሁን ...
Read More »የጀርመን መንግሥት መሪ አንጌላ መርክል የኢትዮጵያ መንግሥት ፖለቲካውን ክፍት እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጀርመን መሪ አንጌላ ሜርክል በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፖለቲካ አፈና ወጥቶ ህዝቡ የሚሳተፍበትን መንገድ እንዲፈልግ እና የጸጥታ ኀይሎች ተቃውሞ በሚያሰሙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ የኀይል ርምጃዎች ከመውሰድ እንዲታቀቡ ጠይቀዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከአንድ ዓመት በላይ የኾነው ፖለቲካዊ ቀውስ ከ500 በላይ ለሚኾኑ ንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ኾኗል ብለዋል። ከጠቅላይ ሚንስትር ኀይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በመኾን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሜርክል ፣ ኢትዮጵያ የገቡት በመዲናይቱ አዲስ አበባ ዙርያ የተነሳው ትኩስ ተቃውሞ እና ግጭት በአገሪቱ ላይ ጥላውን ባጠላበት ማግሥት ነው። የዐመጹ ...
Read More »በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድረጉ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ በኮሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት ፊት ለፊት ባደረጉት ተቃውሞ፣ የኮሪያ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን እርዳታ እንዲያቆም፣ ለአገዛዙ በኢንፎርሜሽንና ደህንነት በኩል የሚሰጠውን ስልጠና እንዲያቆም ጠይቀዋል። አገዛዙ ከሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ እየገዛ በህዝብ ላይ እልቂት እየፈጸመ ነው ሲሉ ኢትዮጵያውያን አክለው ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ሁላችንም ፈይሳ ሌሊሳ ነን፣ የኦሮሞ ፣ የአማራ ፣የኮንሶ፣ የጋምቤላ ደም ደማችን ነው ...
Read More »የቀድሞው የቅንጅት ሊ/መንበር የነበሩት ኢ/ር ሃይሉ ሻውል የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የታዋቂው ፖለቲከኛ ኢ/ር ሃይሉ ሻወል የቀብር ስነስርዓት በቅድስት ስላሴ ሲፈጸም ቤተሶቦችና የቅርብ ዘመዶቻው ፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞች እና የትግል ጓደኞቻቸው ተገኝተዋል። ኢ/ር ሃይሉ ከምርጫ 97 ውዝግብ ጋር በተያያዘ ገዢው ፓርቲ ለ2 አመታት ያክል አስሯቸው ቆይቷል።
Read More »የኢትዮጵያ ወታደሮች ከተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢዎች እየወጡ ነው ተባለ
ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) ኤል-አሊ ተብሎ በሚጠራ መንደር ለረዥም ጊዚያት ቁልፍ ነው የተባለውን ወታደራዊ ቦታ ይዘው የነበሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች በቅርቡ ሞኮኮሪ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ለቀው እንዲወጡ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ሪፖርትን አቅርቧል። የሶማሊያ የደህንነት ባለስልጣናት አልሸባብ የተሰኘው ታጣቂ ሃይል የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰፍረው የነበረውን ቁልፍ ወታደራዊ ጣቢያ ተከታታይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለአለም አቀፍ መገኛኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁልፍ ከተባሉ ቦታዎች ለቀው ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች አደጋ ውስጥ እንደሆኑ ሪፕሪቭ የተሰኘው ተቋም ገለጸ
ኢሳት (መስከረም 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ደህንነት አድጋ ውስጥ እንደከተተ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሰኞ አስታወቀ። መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ሪፕሪቭ ተቋም የሃገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ ግምት ውስጥ በመክተት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻችና ይፋዊ ጥያቄን እንዲያቀርብ አስቧል። በኢትዮጵያ ተግባራዊ ...
Read More »የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚገኙ አለም አቀፍ ተቋማት ከመንግስት ማብራሪያ መጠየቃቸው ተነገረ
ኢሳት (መስከረም 30 ፥ 2008) መንግስት ለስድስት ወር የሚቆይ የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አለም አቀፍ ተቋማትና የሃገር ውስጥ ተወካዮች በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ጠየቁ። ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ይኸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለም አቀፍ ህጎችና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚጥስ አይደለም ቢባልም የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው አለመረጋጋት በኢንቨስትመት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ
ኢሳት (መስከረም 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አለመረጋጋት በሃገሪቱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንና ለውጭ ባለሃብቶች ስጋር መፍጠሩን አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትና ባለሙያዎች ገለጹ። ይኸው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በሚደረገው ጥረት ላይ ሁለገብ የሆኑ መሰናክሎች እንደፈጠረ ብሪታኒያ ለንደን ከተማ በሚገኘው ብሉምበርግ ኢንተሊጀንሲ አለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ማርክ ቦህሉንድ ለብሉምበርግ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት የማሻሻያ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጠየቀ
ኢሳት (መስከረም 30 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በሃገሪቱ የማሻሻያ ዕርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲደረጉ ሰኞ ጠየቀ። በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በተያዘው ወር ሁለተኛ መግለጫውን ያወጣው ህብረቱ ሁሉንም ወገኖች የሚያሳትፍ የማሻሻያ ዕርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቡን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ጋዜጣ ህብረቱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው አለመረጋጋት ስጋቱን ገልጾ የነበረውን የኢትዮጵያ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት ...
Read More »