የኢትዮጵያ መንግስት ሰለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብራሪያ መስጠቱ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ኤምባሲዎችና አለም አቀፍ ተቋማት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረቡዕ ማብራሪያ መስጠቱ ታውቋል። በተያዘው ሳምንት ሰኞ የአዋጁ መውጣት ስጋት ያሳደረባቸው እነዚሁ ተቋማት ለመንግስት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ምንጮች ለኢሳት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር ውይይትን ...

Read More »

አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቀች

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) አሜሪካ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ገዥው የኢህአዴግ መንግስት “ራሱን ለመከላከል የወሰደው ስልት ነው” በማለት ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቁ። የሰዎች መሰባሰብን፣ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽና ያለፍርድ ቤት ሰዎችን ለማሰር ስልጣን ያለው አዋጁ በምን ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረገ እንደታሰበ የኢትዮጵያ መንግስት ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል ሲል የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ለአለም አቀፍ መገንኛ ...

Read More »

በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ  ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህር ዳር ከተማ በተደጋጋሚ በተጠሩት የስራ ማቆም አድማዎች አንድነቱን ያሳየው የባህር ዳር ከተማ ማህበረሰብ ለስርዓቱ አንገዛም የሚለውን መፈክር አሁንም በማሳየት የስራ ማቆሙን አድማ ለሁለተኛ ቀን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በትላንትናው እለት በተካሄደው የስራ ማቆም አድማ እንዳይሳተፉ ጫና ተደርጎባቸው ከሰዓት በኋላ የተከፈቱ የአዴት ተራ ሱቆች ዛሬ በእምቢተኝነታቸው በመጽናት ከሌላው  ማህበረሰብ ጋር የአድማው ተሳታፊ በመሆን ሱቆቻቸውን ...

Read More »

ዲላ ከተማና አካባቢው አሁንም አለመረጋጋቱን ነዋሪዎች ገለጹ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲላ የአካባቢው ሹሞች ቀስቅሰው እንዳስነሱት በሚታመነው ግጭት በከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ ብሄረሰቦች ብቻ 23 ሰዎች ሲሞቱ፣ ከገጠሩ ህዝብ ወይም ከጌዲዮ ማህበረሰብ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ወናጎና ሌሎችም አካባቢዎች ግጭቱ መስፋፋቱን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የገቡት የአጋዚ ወታደሮች በቀጥታ እርምጃ በመውሰድ በርካቶችን ገድለዋል። በርካታ ሱቆች፣ የቡና መፈልፈያዎች፣ ሆቴሎች፣ መኪኖችና ሌሎችም የንግድ ድርጅቶች ተቃጥለዋል። በርካታ ዜጎችም ...

Read More »

ፖሊሶች ዲሽ ሲያስወርዱ መዋላቸውን ከተለያ  አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች አመለከቱ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሽኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀ ማግስት ፖሊሶች በተለይ በኦሮምያና በአማራ አንዳንድ ከተሞች ጣራ ላይ እየወጡ ዲሽ ሲያወርዱ ታይቷል። ኢሳትንና ሌሎችን የውጭ ሚዲያ ይከታተላሉ የተባሉ ሰዎች ዲሾቻቸው ከተነቃቀሉ በሁዋላ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የሞባል ኢንተርኔት የስልክ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ የዘጋው ገዢው ፓርቲ፣ በዲሽ ከውጭ አገር የሚተላለፉ ስርጭቶችን በማፈን ህዝባዊ ተቃውሞውን ለማፈን ሙከራ እያደረገ ነው። የጀርመን መሪ አንጌላ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እየከፋ መምጣቱን የአውሮፓ ኅብረት አወገዘ

ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ  የሰብአዊ መብት እና የልማት ኮሚቴ ዛሬ ባከሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ተወያይቷል ፡፡ በኢትዮጵያ በተካሄደው ህዝባዊ አመፅ ስለተገደሉት ንፁሀን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንዲሁም ባለፈው እሁድ በመላው ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስድስት ወራት የሚቆየውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ኤክስፐርቶች፣ ...

Read More »

በምዕራብ አርሲ ዞን ባልና ሚስትን ጨምሮ በትንሹ ሶስት ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በምዕራብ አርሲ ዞን ስር በምትገኘው የቡልቻና ከተማ በመካሄደ ላይ ያለን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ ባልና ሚስትን ጨምሮ በትንሹ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ዕማኞች ለኢሳት አስታወቁ። በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ የደረሰውን ዕልቂት ተከትሎ በምስራቅና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ስር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ በአዲስ መልክ መቀስቀሱ ይታወቃል። ይኸው ተቃውሞ በቡልቻና ከተማ ከቀናት በፊት መካሄድ መጀመሩን ለዜና ...

Read More »

አንጌላ መርከል መንግስት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄን በሚያቅርቡ ሰዎች ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ እንዲያቆም አሳሰቡ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርከል መንግስት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄን በሚያቅርቡ አካላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ እንዲያቆም ማከሰኞ አሳሰቡ። ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋ በመሆን የጋራ መግለጫን የሰጡት መርከል “ችግር/ጥያቄ ካላቸው ሰዎች ጋር መወያየት ይኖርባችኋል” ሲሉ ለአቶ ሃይለማሪያም በመግለጫው ስነስርዓት ወቅት መናገራቸው ሮይተርስ ዘግቧል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚወስዱትን ድርጊት የኮነኑት ...

Read More »

በጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት ከሚሰራው የህወሃት ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ተለይተው ታወቁ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) በሳምንቱ መጨረሻ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ለማካሄድ መወሰኑ ተመለከተ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢሳት ባደረሰው መረጃ መሰረት አዲስ ከተዋቀረውና በህወሃት ሰዎች በሚመራው ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ታውቀዋል። ከመከላከያ ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከደህንነት የተውጣጣውና በህወሃት ሰዎች በመሪነት በብዛት የሚሳተፉበት ኮማንድ ፖስት በአማራ ክልል ትጥቅ ለማስፈራት እንቅስቃሴ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ሊያባብሰው ይችላል ተባለ

ኢሳት (ጥቅምት 1 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያባብስ እንደሚችለው ሂውማን ራይትስ ዎች ማከሰኞ አስታወቀ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለያዩ ቦታዎች ይሰፍራል ተብሎ የሚጠበቀው የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ በፊት ይወስድ የነበረውን የሃይል ዕርምጃ በማጠናከር ተጨማሪ አፈናን አግባራዊ እንደሚያደርግ የስብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልጸዋል። በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት ከዜጎቹ የተነሱ ...

Read More »