የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ የቀረበለትን የሽብር ወንጀል ምርመራ መዝጋቱ ተነገረ

ኢሳት (ጥቅምት 3 ፥ 2008) በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረበለትን የሽብር ወንጀል ምርመራ መዝጋቱን የተጠርጣሪው ጠበቃ ለኢሳት ገልጹ። የኮሎኔል ደመቀ ጠበቃ አቶ መከተ ካሳሁን ለኢሳት እንደገለጹት ቀደም ሲል በሰው መግደል ወንጀል የተጠረጠሩት ደምበኛቸው የምርመራ መዝገብ መስከረም 18: 2009 ተዘግቷል። ይህም የሆነበትም ምክንያት ዕቃቤ ህግ የምርመራ መዝገቡ ባለቀበት 15 ቀናት ውስጥ በህጉ መሰረት ባለመክፈቱ እንደሆነ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር  የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ትጥቅ ለማስፈታት ከሄዱ ወታደሮች ጋር ተዋግተው በርካታ ወታደሮችን ገደሉ

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን የመከለከያ ጄኔራሎች፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦች፣ የልዩ ሃይል አዛዦች እና የአማራ ክልል አዛዦች ጎንደር ሲኒማ አዳራሽ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከብአዴን አመራሮች ጋር አድረገውት በነበረው ስብሰባ ፣ ህዝቡ በሰላም ትጥቁን እንዲፈታ ለማግባባት የሞከሩ ቢሆንም ፣ በስብሰባው የተሳተፉት ሰዎች ግን  “ በገንዘባቸው የገዙትን የራስ መጠበቂያ መሳሪያ አስረክቡ ብለን ...

Read More »

በባህርዳር የስራ ማቆም አድማው በጉልበት ለማስቆም የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት ሁለት ቀናት በተሳካ ሁኔታ የተካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ለማስቀረት ገዢው ፓርቲ እየወሰደ ባለው እርምጃ ከ20 በላይ ነጋዴዎች የታሰሩ ሲሆን፣ የተወሰኑ ሱቆችም በግዳጅ ድርጅታቸውን እንዲከፈቱ ተደርጓል። በከተማው የሚካሄደውን  አድማ ለማስቆም ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ጫና በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ የመጣው ይምጣ በሚል በድፍረት አሁንም አድማውን ተግባራዊ እያደረጉ ያሉ ድርጅቶች በርካታ ናቸው።

Read More »

የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችና በርካታ ወጣቶችን ለማፈን የሚደረገው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገሪቱ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር መውደቋ በተነገረ ማግስት፣ አገዛዙ የተቃዋሚ መሪዎችን፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን መርተዋል፣ አስተባብረዋል እንዲሁም ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እየተያዙ ወደ እስር ቤት እየተላኩ ነው። በመላው አገሪቱ የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያሳዩት አፈናው በመላ አገሪቱ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶች አፈናውን በመፍራት ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች አካባቢዎች በመሸሽ ...

Read More »

ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ከየመን እስር ቤት አመለጡ

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ የመን በሻብዋ ግዛት ዋና ከተማ አታቅ ከሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ቁጥራቸው ከ1 ሺህ 400  በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ረቡዕ ማለዳ በእስር ቤቱ ጠባቂዎች እርዳታ አምልጠው መውጣታቸውን የአገሪቱ የደኅንነት ባለስልጣናት አስታወቁ። ሰደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ወደ የመን በመግባታቸው ምክንያት መታሰራቸውን እና ወደ ትውልድ አገራቸው ለመላክ ወደ ማእከሉ መግባታችውን የተደራጁ ታጣቂዎች ከእስር ቤት ...

Read More »

መለስ ዜናዊ ኦሮሞን አንደ ህዝብ ጠባብ ነው የሚል ሰነድ አዘጋጅተው እንደነበር አቶ ጁነዲን ሳዶ ገለጹ

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ኦሮሞን አንደ ህዝብ ጠባብ ነው የሚል ሰነድ አዘጋጅተው እንደነበር አቶ ጁነዲን ሳዶ ገለጹ። በሁኔታው የተቆጩ በዝቅተኛ ዕርከን ላይ የሚገኙ የኦህዴድ ካድሬዎች ሰነዱ እንዲቃጠል መጠየቃቸውንም አስታውሰዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ከተዛወረ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ የተደረገው ቅንጅት አዲስ አበባ ላይ በማሸነፉ እንደሆነም ተመልክቷል። የምርጫ 97 ማግስት ለኢህአዴግ ሰዎች ...

Read More »

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን የዘንድሮው የማርቲን ኤናልስ ሶስት አሸናፊዎች መካከል መሆናቸው ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) ባለፈው አመት ከ18 ወራት እስራት በኋላ ከተመሰረተባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ በነጻ የተሰናበቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን የዘንድሮው የማርቲን ኤናልስ ሶስት አሸናፊዎች መካከል አንዱ በመሆን ማክሰኞ በስዊዘርላንድ ሽልማትን ተቀበሉ። ይኸው አመታዊ ሽልማት አስር ታዋቂ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በጋራ የሚያዘጋጁት ሲሆን ሽልማቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ጥረት ላደረጉ አካላት የሚበረከት መሆኑ ታውቋል። ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ጋራ የክብር ...

Read More »

በባህርዳር በተፈጸመ የእጅ ቦንብ ጥቃት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች ተገደሉ

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) በባህርዳር ከተማ የጸጥታ ቁጥጥር በማድረግ ላይ በነበሩ የአጋዚ ወታደሮች ላይ ሰኞ ምሽት በተፈጸመ የእጅ ቦንብ ጥቃት ሁለት አባላት መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። ወታደሮቹ በከተማዋ ቀበሌ 05 ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተሽከርካሪ በመዘዋወር ላይ እንዳሉ የእጅ ቦንብ እንደተወረወረባቸውና ከሞቱን ሁለቱ ወታደሮች በተጨማሪ የተጎዱ መኖራቸውን ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ እማኞች አስረድተዋል። የፍትህና የነጻነት ሃይሎች በሚባሉ አካላት ተፈጽሟል ...

Read More »

ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ግዛት ሚኒሶታ ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን ገቢው ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በቅርቡ አካሄዱ። የኢሳትን ስድስተኛ አመት በማስመልከት በተካሄደው በዚህ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ኢሳት እያደረገ ያለውን መረጃ የማድረስ ጥረት በተለያዩ መንገዶች ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን የዝግጅቱ አስተባባሪ ለኢሳት አስታውቀዋል። በዕለቱ የታደሙ ኢትዮጵያዊያን ከ62 ሺ ዶላር (ከአንድ ሚሊዮን ብር) በላይ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል ከተሞች አባላትን ለመመልመልና ስልጠና ለመስጠት ሞክረዋል የተባሉ የሽብረተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

ኢሳት (ጥቅምት 2 ፥ 2009) በአሜሪካ ይገኛል ከተባለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የስልክ ግንኙነት በማድረግ በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች አባላትን ለመመልመልና ስልጠና ለመስጠት ሞክረዋል የተባሉ 17 ተጠርጣሪዎች የሽብረተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉት እነዚሁ ተጠርጣሪዎች ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ፣ ሰበታ፣ ጅግጅጋ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች እንደሆነ ረቡዕ ክሳቸው መነበብ መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ...

Read More »