የአፍሪካ አባል ሃገራት በጋዜጠኞች ላይ የሚወስዱትን አፈናና ግድያ እንዲያቆሙ ተጠየቁ

ኢሳት (ጥቅምት 24 ፥ 2009) በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ውስጥ በቅርቡ ውክልናን ያገኘው የአውሮፓ ህብረት የአህጉሪቱ አባል ሃገራት በጋዜጠኞች ላይ የሚወስዱትን አፈናና ግድያ እንዲያቆሙ አሳሰበ። በአፍሪካ ህብረት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ልዩ ጥበቃና ከለላ እንደሚደረግለት ቢደነገግም አሁንም ድረስ የጋዜጠኞች እስራትና ወከባ እንዲሁም አፈና ሊቆም አለመቻሉን የአውሮፓ ህብረት ከአዲስ አበባ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በጋዜጠኞች ላይ ወከባን እየፈጸሙ ያሉ ሃገራት ከድርጊታቸው መታቀብ ለአህጉራዊና ...

Read More »

የንግድ ድርጅቶች በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 24 ፥ 2009) በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የአገልግሎት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ። የእንግዶች መቀነስ ከተጠበቀው በላይ እየሆነ መምጣቱን የገለጹት የሆቴል ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት ዕልባት ባለማግኘቱ ኪሳራን እያደረሰባቸው እንደሆነ ገልጸዋል። ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል በተለይ የሆቴል ድርጅቶች እየደረሰባቸው ያለውን ኪሳራን ግምት ውስጥ በማስገባት በግብር ክፍያቸው ላይ ማስተካከያን እንዲያደርግላቸው ...

Read More »

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን ያለህጋዊ ፈቃድ ይሰጣሉ በተባሉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ

ኢሳት (ጥቅምት 24 ፥ 2009) የአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን ያለህጋዊ ፈቃድ ይሰጣሉ በተባሉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች አስታወቁ። የጸጥታ ሃይሎች የቤት ለቤት ፍተሻን ጭምር እያካሄዱ ባለው በዚሁ ዘመቻ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከተቋማቱና ከግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠቀም ያልተጠበቀ ፍተሻን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የቀጠለው ህዝባዊ ዕምቢተኝነትና የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ መመሰረት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 24 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ውስጥ የቀጠለው ህዝባዊ ዕምቢተኝነትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እንዲመሰረት ምክንያት መሆኑን ድርጅቱ አስታወቀ። ባለፈው ዕሁድ በይፋ መመስረቱ የተገለጸው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አሁን የተፈጠረው ህብረት ሃገር ቤት እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ዕምቢተኝነት የወለደው ጭምር በመሆኑ እስከዛሬው የተለየ መሆኑን አመልክተዋል። የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያው ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት ...

Read More »

በአባይ ግድብ ተቀጥረው የሚሰሩ ከ30 በላይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ታፍነው ተወሰዱ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሚፈለጉት መካከል ግድቡ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤት ስራ አስኪያጅም ይገኙበታል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓም በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከ30 በላይ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ተይዘው ሲታሰሩ፣ የአካባቢው የንግድ ባንክ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊያዙ ሲሉ አምልጠዋል። በርካታ ወታደሮች ወደ አካባቢው በመሰማራት በሜቴክ እና በሳሊኒ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ቤት የማፍረሱ ዘመቻ ተጀመረ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ቤት የማፍረሱ እንቅስቃሴ እንደአዲስ ተጀምሯል። በለገጣፎና አካባቢዋ ዛሬ በርካታ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትና ቀይ ኮፍያ ለባሽ የአጋዚ ወታደሮች በብዛት ቁጥጥር ሲያደርጉ ውለዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች አገዛዙ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ማንኛውንም አይነት ተቃውሞ ማድረግ ስለማይችሉ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ቤት የማፍረሱ ዘመቻ ...

Read More »

አልሸባብ ለኢትዮጵያ ሲሰልሉ ነበሩ የተባሉ አምስት ሶማሊያዊያንን አንገት ቀላ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር ላለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እና ለሶማሊያ መንግስት በመረጃ እና ስለላ ስራ ላይ በመሰማራት ድጋፍ ሰጪ ሆነው ሲያገለግሉ ነበሩ ያላቸውን አምስት ሶማሊያዊያንን አንገት መቅላቱን አልሸባብ አስታውቋል። አልሸባብ የታይግሎ ከተማን ከተቆጣጠረ ወዲህ በከተማ ያለው ድባብ አስፈሪ ነው። አምስቱን ሰላማዊ ንጹሃን ዜጎችን ጨምሮ ነጋዴዎችና ...

Read More »

የባህር ዳር ወጣቶች የብዓዴን ሃላፊዎች በሚኖሩበት ኪቤአድ ግቢ ቦምብ አፈነዱ

ኢሳት (ጥቅምት 23 ፥ 2009) በባህርዳር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የነዋሪዎችና የነጋዴዎችን መታሰር በመቃወም የከተማዋ ወጣቶች ቦንብ ማፈንዳታቸውን ተነገረ። ወጣቶቹ እርምጃውን የወሰዱት ቀበሌ 03 በሚገኘው የአቶ ገለታ እና አቶ ስለሺ በተባሉ የብአዴን ባለስልጣናት መኖሪያ ቤቶች ግቢ ውስጥ ነው። ኪቤአድ ግቢ አካቢቢና በባህር ዳር ማዘጋጃ ዙሪያ የተጣሉት ቦምቦች ስላደረሱት ጉዳት የተባለ ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጢስ አባይ ከተማ የጎበዝ አለቃ ...

Read More »

የግብፅ ተቋማት ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች እርዳታ እንደሚለግሱ በቂ መረጃ አለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ገለጹ

ኢሳት (ጥቅምት 23 ፥ 2009) የግብፅ ተቋማት ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች እርዳታ እንደሚለግሱ በቂ መረጃ አለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ገለጹ። አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስታቸው ከግብጽ መንግስት ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሰሩ ጸረ-ልማት የግብፅ ተቋማትን እየለየን ነው ሲሉ ተናግረዋል። የፓርላማ አባላት ላነሱት ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ኢትዮጵያ ለግብፅ መንግስት ቀጥተኛና ግልጽ ጥያቄ ማቅረቧን ገልጸው፣ የግብፅ መንግስት እነዚህ ሃይሎች በእኛ ስር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ አመራሮች የፊታችን አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታወቁ

ኢሳት (ጥቅምት 23 ፥ 2009) በአራት ድርጅቶች በቅርቡ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ አመራሮች የፊታችን አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመስጠት የፈለጉት ህብረታቸው ወደፊት ለመስራት ያቀዳቸውን ጉዳዮች ለማብራራት መሆኑን አስታውቀዋል። በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬስ ክለብ ከእኩለ-ቀን ጀምሮ በሚሰጠው የንቅናቄው አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር መሪዎች አቶ ሌንጮ ለታና ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ የአፋር ህዝባዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ...

Read More »