ህወሃት/ኢህአዴግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በውጭ ዜጎች ላይ የጣለውን የጎዞ እገዳ አነሳ

ኢሳት (ጥቅምት 29 ፥ 2009) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ ሃገር ተወካዮች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ሲያቀርቡ የቆዩትን ቅሬታ ተከትሎ መንግስት በጉዞ እንቅስቃሴያቸው  ላይ የጣለውን እገዳ ማንሳቱን ማክሰኞ አስታወቀ። የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ የምዕራባውያን ሃገራት በዲፕሎማቶች ላይ የተጣለውን እገዳ በዕለት ከእለት ስራቸው ላይ ኣሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ሲገልፅ መቆየታቸውን የሚታወስ ነው። በዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ቢነገርም የውጭ ሃገር ተወካዮች ...

Read More »

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁኔታ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ የብሪታኒያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ

ኢሳት (ጥቅምት 29 ፥ 2009) የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የሃገሪቱ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ሁኔታ ተከታትሎ ለህዝብ በአስቸኳይ ይፋ እንዲያደርግ በድጋሚ ጥሪን አቀረቡ። የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች በብሪታኒያ ባለስልጣናት በኩል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደማይገኙ መረጃን ቢሰጡም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ማረጋገጫ አለማግኘቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ከነሃሴ ወር ጀምሮ አቶ ...

Read More »

የተከዜ ሃይል ማመንጫ ሶስት ተርባይኖች ስራ ማቆማቸው ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 29 ፥ 2009) ከስምንት አመት በፊት በ360 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የተከዜ ሃይል ማመንጫ ግድብ አጋጥሞታል በተባለ የቴክኒክ ችግር ከአራት ተርባይኖች ሶስቱ ስራ ማቆማቸው ተገለጸ። የሃይል ማመንጫ ጣቢያው ባለፈው አመት በድርቅ ምክንያት የውሃ እጥረት አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም፣ ግድቡ ያለ በቂ ውሃ የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያመነጭ በመደረጉ በተርባይኖች ላይ የመሰንጠቅ አደጋ እንደደረሰ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ማክሰኞች አስታወቀ። 300 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ...

Read More »

በማሳቹሴትስ ግዛት ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ

ኢሳት (ጥቅምት 29 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት የሆኑ ኢትዮጵያውያን ገቢው ኢሳትን ለመደገፍ የሚውል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ አካሄዱ። በቦስተን ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በታደሙባት በዚሁ ዝግጅት ወደ 40ሺ ዶላር (800ሺ ብር በላይ) ሊሰባሰብ መቻሉን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገልጸዋል። የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በከተማዋ በተካሄደው በዚሁ የገቢ ማሰባሰቢያ ስነስርዓት ላይ ኢሳትን በመወከል ጋዜጠኛ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በሁዋላ የሞጣ መምህራን  አድማ በመምታት የመጀመሪያዎቹ ሆኑ

ጥቅምት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም አይነት የስራ ማቆም አድማ ማድረግም ሆነ መሰብሰብ ህገወጥ መሆኑን ዝርዝር መመሪያ ካወጣ የሞጣ ከተማ መምህራን የስራ ማቆም አድማ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነዋል። መምህራኑና ተማሪዎች ትናንት የጀመሩትን ተቃውሞ ዛሬ ትምህርት  በመዝጋት የቀጠሉ ሲሆን፣ የከተማዋ ባለስልጣናትና የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተማሪዎችን እና መምህራንን በማስፈራራት ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም። መምህራኑና ...

Read More »

የደህንነት መስሪያ ቤቱ የነጻነት ታጋዮችን በድለላ ለማስገባት የጀመረው ጥረት እስካሁን ውጤት አላመጣም

ጥቅምት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ በረሃዎች የሚንቀሳቀሱ በርካታ የነጻነት ሃይሎችን በማታለል እጃቸውን ለህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት  የነጻነት ሃይሎች ውድቅ አድርገውታል። ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች ጋር በተያያዘ አገዛዙ የወሰደው እርምጃ በርካታዎች ጫካ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። በጎንደር የተካሄዱትን ታውሞዎች ተከትሎም፣ ብዙ ወጣቶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጫካ የገቡ ሲሆን፣ በአገዛዙ ወታደሮችና ድርጅቶች ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲን መውረራቸው ተገልጸ

ኢሳት (ጥቅምት 28 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሃገራቸው መንግስት ሊሰጠን የሚገባውን ጥቅማጥቅም አዘግይቶብናል በሚል በአዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ላይ ወረራን ፈጸሙ። ተማሪዎቹ በሃገራቸው ኤምባሲ ላይ የፈጸሙትን ወረራ ለማክሸፍ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ ወደ 42 የሚደርሱ ተማሪዎች ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል። ስሙን መግለጽ ያልፈለገ የተማሪዎች ተወካይ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውንና የኤምባሲው ሰራተኞች የሃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ...

Read More »

በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ መከሰቱ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 28 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች አዲስ የድርቅ አደጋ መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ይፋ አደረገ። የብሄራዊ አደጋ መከላከያ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በ212 ወረዳዎች ላይ ባካሄዱት የሰብል እርሻ ጥናት አዲሱ ድርቅ መከሰቱ ሊታወቅ እንደቻለ ተቋማቱ በጋራ አስታውቀዋል። በዚሁ ጥናት ውስጥ ተካተው ከነበሩት ወረዳዎች መካከል 93 የሚሆኑን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ እንዳጋጠማቸው ለመረዳት ...

Read More »

መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን ኢትዮጵያ እንድታከብር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጠየቀ

ኢሳት (ጥቅምት 28 ፥ 2009) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብርና በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የጣለውን ዕገዳ በአስቸኳይ እንዲያነሳ ሰኞ ጥሪን አቀረበ። የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ በሃገሪቱ ሰፍኖ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ዕልባት ለመስጠት ሁለገብና ውጤታማ የሆነ ምክክር መካሄድ እንዳለበት ማሳሰባቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባራዊ አድርጎ የሚገኘው መንግስት የሃገሪቱ ዜጎች መረጃን የማግኘት እና የማህበራዊ ...

Read More »

የአፋር ህዝብ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ትግል የሚቀላቀልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ገልጹ

ኢሳት (ጥቅምት 28 ፥ 2009) የአፋር ህዝብ እየደረሰበት ያለው መከራ ከምንጊዜውም በላይ እየከፋ በመምጣቱ የኦሮሞዎችንና የአማራዎችን እንዲሁም የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ትግል የሚቀላቀልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ገልጹ። የአፋር ህዝብ ሱልጣን በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት የቀድሞ ዲፕሎማትና የክልሉ ፕሬዚደንት ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ፣ በቅርብ ወራት ውስጥ የአፋርን ህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ እናያለን ሲሉ ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል። ሱልጣን ሃንፍሬ አሊምራህ በዋሽንግተን ዲሲ ...

Read More »