ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቱሪዝም ገቢ ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ ተከትሎ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ተወካዮች ወደ ብሪታኒያ መጓዛቸው ተገለጸ። መቀመጫቸውን በብሪታኒያ ያደረጉ በርካታ አለም አቀፍ አስጎብኚ ተቋማት በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ይኸው አዋጅ፣ በጎብኚዎች ላይ የደህንነት ስጋት አሳድሯል በማለት ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉብኝት መሰረዛቸው ይታወሳል። የአስጎብኚ ድርጅቶቹ የወሰዱት ዕርምጃ በቱሪዝም ገቢው ላይ ከፍተኛ ...
Read More »በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ውጥረትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ
ኢሳት (ህዳር 1 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎ ቢገኝም፣ በሃገሪቱ ፖለቲካዊ ውጥረትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጠ። ለአንድ አመት ያህል በተለያዩ ክልሎች ሲካሄድ ከነበረው ከዚሁ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በንፁሃን ሰዎች ላይ የተፈጸመን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ ማጣራት እንደሚያስፈልግም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ ለኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበው ጥሪ አመልክቷል። በአሁኑ ወቅት ...
Read More »በወገራ ወረዳ በእንቃሽ በተደረገው ውጊያ የተገደሉት የመንግስት ታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ኅዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጦርነቱ የተካፈሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት በእንቃሽ በህዝብ በሚደገፉት የነጻነት ሃይሎች በአንድ ወገን የመንግስት ታጣቂዎች በሌላ ወገን ባደረጉት ውጊያ 23 የመከላከያ፣ 4 የጸረ ሽምቅና 3 የአካባቢ ሚሊሺያ ወይም ጉጅሌ ተገድለዋል። 25 የሚሆኑ ወታደሮች የተማረኩ ሲሆን፣ ከ20 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። በውጊያው መትረጊስ፣ ክላሽንኮቭ፣ አብራራውና ሌሎችም የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች ከአንድ የመገናኛ ሬዲዮ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ሪፖርት አዳመጠ
ኢሳት (ጥቅምት 30 ፥ 2009) የአውሮፓ ህብረት በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ረቡዕ ዋና መቀመጫ በሚገኝበት የብራሰልሷ መዲና ብራሰልስ ልዩ ሪፖርትን የማድመጥ መድረክ አካሄደ። በዚሁ መድረክ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ፊዴራሊስት ኮንግሬስ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ እንዲሁም አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአካል በመገኘት በህብረቱ አባላትና አመራሮች ማብራሪያን ሰጥተዋል። በመድረኩ ማብራሪያን ያቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋት ከቁጥጥር ውጭ ...
Read More »ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጥቃት ተሰነዘረበት
ኢሳት (ጥቅምት 30 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ አጸፋ እንደተሰነዘረባቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጹ። በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ በተካሄደው ጦርነት 30 ታጣቂዎችና ወታደሮች ከነመሳሪያቸው መማረካቸውን የነጻነት ሃይሎች ተናግረዋል። ተጨማሪ 3 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ አካባቢው ተጉዘዋል። በተለይም አንቃሽ በተባለ ቦታ ላይ ሽፍቶችን ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን የነጻነት ሃይሎች እና የመንግስት ወታደሮች ለሁለተኛ ቀን ተዋጉ
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የህወሃት/ ኢህአዴግን አገዛዝ በመሳሪያ ሃይል ለመታገል ወደ ጫካ የወጡ የነጻነት ሃይሎች በየጊዜው ከመንግስት ወታደሮች ጋር እየተታኮሱ ሲሆን፣ ትናንት በወገራ ወረዳ እንቃሽ በሚባለው አካባቢ የተደረገው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ መዋሉንና በርካታ የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። የተወሰነ የመንግስት ታጣቂዎች አስከሬን ጎንደር ከተማ ገብቷል። የነጻነት ሃይሎች እንደሚሉት ምንም አይነት ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ምክንያት በፓኪስታን ማረፉ ተሰማ
ኢሳት (ጥቅምት 30 ፥ 2009) ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን ከ300 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ላይ እንዳለ በፓኪስታን በቴክኒክ ችግር ተገዶ አረፈ። 335 መንገደኞችንና 12 የበረራ ባለሙያዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በነዳጅ መያዣው ላይ የነዳጅ መፍሰስ አጋጥሞት በአስቸኳይ ለማረፍ መገደዱን የፓኪስታን የአቪየሽን ባለስልጣናት ረቡዕ ይፋ አድርገዋል። የመንገደኞች አውሮፕላኑ በፓኪስታን የፑንጃብ ግዛት በምትገኘው የላሆር ከተማ አለም አቀፍ ...
Read More »የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ ማሽነፋቸውን ተከትሎ የአለም ኢኮኖሚ እየዋዠቀ ነው ተባለ
ኢሳት (ጥቅምት 30 ፥ 2009) የአሜሪካው የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ለመሆኝ መብቃታቸውን ተከትሎ በአውሮፓና በተለያዩ የአለማችን አህጉራት ኢኮኖሚያዊ መዋዠቅ መከሰቱ ተነገረ። ባልተጠበቀ ሁኔታ ለድል በቅተዋል የተባሉት እና የፖለቲካ ዕውቀት የላቸውም የሚል ስሞታ ሲቀርብባቸው የነበሩት ተመራጩ ፕሬዚደንት ተግባራዊ አደርገዋለሁ ሲሉ የነበሩት የኢኮኖሚና ኢሚግሬሽን ፖሊስ ለአለም ሃገራትና ለአሜሪካ አዲስ ምልከታ መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል። በአለም ዙሪያ ግዙፍ የሚባሉ የንግድ ...
Read More »በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ የአደራ መንግስት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ
ኢሳት (ጥቅምት 30 ፥ 2009) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በማውገዝ የአደራ መንግስት እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ። በኦሃዮ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ከጥቅምት 23-26 2009 ባደረገው ስብሰባ በሌሎች የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ጭምር እንደተወያየ ለኢሳት የላከው መግለጫ ያስረዳል። በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የተመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህወሃት አገዛዝ በህዝቡ ላይ በጫነው ...
Read More »በአዲስ አበባ ሁለት ግብጻውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 29 ፥ 2009) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደርጉ ሁለት ግብጻውያን ባልታወቀ ምክንያት ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። በጸጥታ ሃይሎች ለእስር ከተዳረጉት ሁለት ግብጻውያን መካከል አንደኛው ካዛንቺስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የራዲሰን ብሉ ሆቴል ረዳት ዋና ስራ አስፈጻሚ መሆናቸውን በሃገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች ዘግበዋል። ከአራት አመት በፊት ግብፅ ከሚገኘው ተመሳሳይ ሆቴል ወደ ኢትዮጵያ ተዛውረዋል የተባሉ ታሃ-ማንሱር በስራ ላይ እያሉ ...
Read More »