የአባይ ግድብ በግብፅ ውሃ ይዞታ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርስ የግብፅ ውሃ ምህንድስና ባለሙያዎች ገለጹ

ኢሳት (ህዳር 5 ፥ 2009) የግብፅ የውሃ ምህንድስና ባለሙያዎች በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ ወደ ግብፅ የሚፈስ ውሃን በአመት በ12 ቢሊዮን ኩዩቢክ ሜትር ይቀንሳል ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ። ሁለቱ ሃገራት ግድቡ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ለማስጠናት ከሁለት አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ላይ ቢደርሱም የግብፅ ባለስልጣናት ጥናቱ ሳይጀመር ግድቡ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው ሲሉ አስታውቀዋል። በካይሮ ዩኒቨርስቲ የውሃ ሃብት ፕሮፌሰር የሆኑት ናድር ኑረዲን ...

Read More »

የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (ህዳር 5 ፥ 2009) በአትላንታ የተካሄደው የኦሮሞ መሪዎች ጉባዔ በማህበረሰቡ ዙሪያ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ጥሪ በማድረግ የአቋም መግለጫ አወጣ። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከህዳር 11 እስከ ህዳር 13 በአትላንታ ከተማ የተካሄደው የኦሮሞ መሪዎች ጉባዔ ህዝቡ የህወሃትን አገዛዝ ለማስወገድ የሚያደርገውን ትግል እየደገፉ ያሉ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ከልዩነት ይልቅ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ስለሚልቅ ወደ አንድነት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል። ጉባዔው ...

Read More »

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ማሻሻያ እንዲደረግ ካናዳ ጠየቀች

ኢሳት (ህዳር 5 ፥ 2009) ሰሞኑን የካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስቴፋኒ ዲዮን በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ተከትሎ ሃገሪቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓቱ ማሻሻያ እንዲደርግበት ጥሪን አቀረበች። በሚኒስትሩ ዲዮን የተመራ የልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማካሄዱ ይታወሳል። በሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ መግለጫን ያወጣው የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፖለቲካ ስርዓቱ ማሻሻያ በተጨማሪ ...

Read More »

በእንቀሽ በወታደሮችና ራሳቸውን ባደራጁ ሃይሎች መካከል ያለው ፍጥጫ እንደቀጠለ ነው።

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ለሳምንት የዘለቀው ፍጥጫ ዛሬም ቀጥሎአል። የቡድኑ አስተባባሪ ለኢሳት እንደገለጸው፣ ቀደም ብሎ ተደርጎ በነበረው የተኩስ ልውጥ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አካባቢውን ከበው በመጠባበቅ ላይ ቢሆንም፣ ጫካ የገቡት ሃይሎች አሁንም በጥሩ ...

Read More »

የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የደፈጣ ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር የሃለጋ ክንፍ ታጣቂዎች በዱሁሁን አውራጃ ውስጥ በገጠር መንደሮች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ነበሩ ባላቸው የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።በዱሁሁን በሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አስገድዶ መድፈር፣ ድብደባ እና የጅምላ እስራት ሲፈጽሙ ከነበሩት ውስጥ በደፈጣ ውጊያ 5ቱ መገደላቸውንና 7 ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደርዊ ክንፉ ገልጿል። አስቸኳይ ...

Read More »

የአማራ ክልል በትምህርት ተሳትፎና ተደራሽነት ማስመዝገብ የሚገባውን ውጤት ለመድረስ አለመቻሉ ተነገረ፡፡

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉት የትምህርት እርከኖች ባለፉት አመታት ከታሰበው ግብ ለመድረስ እንዳልቻለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለጹ፡፡ አቶ ብናልፍ ሰሞኑን ከትምህርት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ስለዓለፈው ዓመት የትምህርት አፈጻጸም በተወያዩበት ጊዜ እንደተናገሩት አጠቃላይ የርብርብ ማዕከል ይሆናል ተብሎ በተያዘው ዕቅድ መሰረት በቅድመ መደበኛ፣በመጀመሪያ ደረጃ፣በሁለተኛ ...

Read More »

ካናዳ በኢትዮጵያ ሁሉንም ያሳተፈ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሄድ ጠየቀች

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታዎች እያሳሰበው መምጣቱንና በሰላማዊ እና ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ የአገሪቱን ችግሮችን ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይቶች በማካሄድ ፖለቲካዊ ተሃድሶ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተነሱት ሕዝባዊ አመጾች ምክንያት ብዙ ዜጎች በመገደላቸው በአካባቢዎቹ አለመረጋጋቶች ተፈጥረዋል። ሁኔታዎቹ ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው አስቀድሞ መፍትሔ እንዲበጅላቸው ሲሉ በካናዳ መንግስት የውጭ ...

Read More »

የመን በእስር ላይ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች 150 ዎቹን  ወደ አገራቸው መለሰች

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሕርና በረሃ አቆራርጠው በሕገወጥ መንገድ ወደ የመን ገብተዋል ያለቻቸውን ቁጥራቸው 150 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም (IOM) አማካኝነት ወደ ትውልድ አገራቸው መላካቸውን የመን አስታውቃለች። በቀይ ባህር ዳርቻ በምትገኘው የወደብ ከተማዋ ሁዴዳ እስር ቤት ውስጥ  ከሚገኙት እስረኞች መካከል 150 በጎ ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከአይኦኤም ጋር በመተባበር  ወደ ትውልድ ...

Read More »

የዞን 9 ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ በጸጥታ ሃይሎች መታሰሩ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 2 ፥ 2009) የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን የሆነው በፍቃዱ ሐይሉ አርብ ህዳር 2 ቀን 2009 አም ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤቱ እያለ “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋል” በሚል ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ሃይሎች መወሰዱን የአገር ቤት ምንጮቻችን ለኢሳት ገልፀዋል። ከሌሎች የዞን ዘጠኝ ጦማሪያዎችና ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ለአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ በዋስ የተለቀቀውና አቃቤ ህግ ይግባኝ የጠየቀበት ጦማሪ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ የወጣው በአገር ውስጥ በተፈጠረ ቀውስ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 2 ፥ 2009) በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን እስላማዊ አማጺ ቡድንን ለመዋጋት ወደ ሶማሊያ የገባው የኢትዮጵያ ጦር፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአራት የሶማሊያ ስትራቲጂያዊ ከተሞች ለቆ መውጣቱ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠር የጦር ሰራዊቷን ከሶማሊያ ማስወጣቷ፣ በአገር ውስጥ ከተፈጠረው ቀውስ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአፍሪካ ቀንድ ተንታኞች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት በአሁኑ ወቅት ሶማሊያን ለቆ እየወጣ ያለበት ሁኔታ አገር ውስጥ ...

Read More »