ከ40 ሚሊዮን የሚበልጡ ታዳጊ ኢትዮጵያውያን መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው እንደማያገኙ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ህዳር 6 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ከ40 ሚሊዮን የሚበልጡ ታዳጊ ህጻናት ከመሰረታዊ ፍላጎቶች መካከል አብዛኛውን የማያገኙ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ማክሰኞ ይፋ አደረገ። መጠለያ፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ ትምህርት፣ መረጃ እንዲሁም የህጻናት ጥበቃ መሰረታዊ ፋላጎቶች ተብለው ቢቀመጡም በኢትዮጵያ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት የዚህ ተጠቃሚ ሊሆኑ አለመቻላቸውን ድርጅቱ በደቡብ አፍሪካ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል። ከሰሃራ በታች ካሉ ከ20 አገራት መካከል ኢትዮጵያ ለታዳጊ ...

Read More »

ከየመን በግዳጅ ተባረው በጅቡቲ ከሰፈሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል 24ቱ መሞታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 6 ፥ 2009) ከየመን በግዳጅ እንዲወጡ ተደርገው በጎረቤት ጅቡቲ ከሰፈሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል በትንሹ 24ቱ መሞታቸው ተገለጸ። መቀመጫውን በስዊሰርላንድ መዲና ጄኔቫ ያደረገው የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (IOM) የመን ስደተኞቹን በሃይል ወደፈለጉበት ቦታ እያጓጓዘች ያለችው ድርጊት እጅጉን አሳስቦት እንደሚገኝ ማክሰኞ አስታዉቋል። ባለፈው ሳምንት 82 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በጀልባ ተጭነው በጅቡቲ ያለማንም ታዛቢነት ያለ በቂ ምግብና መጠለያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን የስደተኛ ...

Read More »

የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ የአንድ አመት እስር ተፈረደበት

ኢሳት (ህዳር 6 ፥ 2009) የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የስም ማጥፋት ክስ ቀርቦበት በነበረው የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ አመት የእስር ቅጣት አስተላለፈ። ከሳሽ አቃቤ ህግ ጋዜጠኛው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አመራሮች ላይ የተሳሳተ መረጃን በማሰራጨትና የስም ማጥፋት ድርጊትን ፈጽሟል ሲል ባለፈው አመት የጥፋተኝነት ብይን መስጠቱ ይታወሳል። ከዚሁ ክስ ጋር በተገናኘ ባለፈው ሳምንት ለእስር ተዳርጎ የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ዞን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ታሰሩ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮማንድ ፖስት ስም የደቡብ ኦሞን ዞን የሚመሩት የህወሃት የደህንነት ሰራተኞች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችንና ወጣቶችን እየያዙ በማሰር ላይ ናቸው። የኦሞ ህዝብ ዲሞክራሲ ህብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ተጠሪ መምህር አለማየሁ፣ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የዞን ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው እንዲሁም የኦሞ ህዝብ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዳዊት ካብት ይመር ትናናት ከንጋቱ 12 ሰአት ...

Read More »

በደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱ ተዘገበ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመረጃ ኔትወርክ እንዳስታወቀው በኦሮምያ በተለይም በቦረና አካባቢ፣ በደቡብና ሶማሊ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት ተከስቷል። አርብቶአደሮች እንስሶቻቸውን ይዘው ምግብ እና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ አፋጣኝ አለማቀፍ እርዳታ ካልተገኘ ድርቁ የከፋ ጉዳት ያስከትላል ብሎአል። የአለማቀፉ የምግብ ድርጅት ለአስቸኳይ እርዳታ በሚል 14 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ...

Read More »

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሁለት ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ አደረጉ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አምባገነኑ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስራት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማውገዝ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ እያደረጉ ነው። ቁጥራቸው ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በስዊድን ፓርላማ ፊት ለፊት ቀዝቃዛው በረማው የአየርንብረት ሳይበግራቸው ለወገኖቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ከተለያዩ የሲቪክ ማኅበረሰቦች የተውጣጡት እነዚህ የርሃብ አድማ ...

Read More »

የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ የአንድ ዓመት እስር እና የገንዘብ መቀጮ ተፈረደበት

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አራዳ የሚገኘው 6ኛ የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ወንጀል ችሎት ህዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ ዓመት እስር እና የ1 ሽህ 500 ብር በግል እና በድርጅቱ ስም ደግሞ የ10 ሽህ ብር መቀጮ እንዲከፍል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፎአል። ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁን ለእስራት ...

Read More »

አልሸባብ ወደ ማእከላዊ ሶማሊያ እየገሰገሰ ነው

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ቁጥጥር ስር የነበሩ የሶማሊያ ግዛቶች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። በደባቡባዊ እና ማእከላዊ ሶማሊያ አካባቢዎች በኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ጦር እጅ የነበሩ አስር ከተሞችን አሸባሪው አልሸባብ ዳግም በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን አልጀዚራ ከስፍራው ዘግቧል። ባለፈው ወር ብቻ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር የለቀቋቸው አራት ከተሞች ሙሉ ...

Read More »

በደቡብ ኢትዮጵያ በስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ቱሪስቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 5 ፥ 2009) በደቡብ ክልል ሚዛን ከተማ አካባቢ በጉብኝት ላይ የነበሩ 10 የስሎቫኪያና የቼክ ሪፐብሊክ ቱሪስቶች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ዝርፊያ ተፈጽሞባቸው ሹፌራቸው መገልደሉ ተገለጸ። የቼክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቀናት በፊት በክልሉ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩት ቱሪስቶች በታጠቁ ሃይሎች ገንዘብን ጨምሮ የባንክ መገልገያ ካርዶችና ሌሎች ንብረቶቻቸው እንደተወሰደባቸው ሰኞ ይፋ አድርጓል። የቼክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ የሆኑት ኢሬና ቫሌንቶባ፣ ዝርፊያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ማዕድን ፈልጋ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ኩባንያ ፕሮጄክቱን መንግስት እንዲረከብለት ጠየቀ

ኢሳት (ህዳር 5 ፥ 2009) በቅርቡ በኢትዮጵያ የአፋር ክልል የጀመረውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር የማዕድን ፍለጋ ስራ ለማቋረጥ የወሰነ አንድ የእስራዔል ኩባንያ መንግስት ፕሮጄክቱን እንዲረከብለት ጠየቀ። I.C.L. የተሰኘ ይኸው አለም አቀፍ ኩባንያ የማዕድን ፍለጋ ስራውን ከተረከበው ሌላ ኩባንያ ጋር የተገናኘ 55 ሚሊዮን ዶላር የግብር ክፍያ ያለአግባብ ተጠይቄያለሁ በማለት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታን መቅረቡ ይታወሳል። የእስራዔሉ ኩባንያ የኢንቨስትመንት ስራውን ለማቋረጥ የወሰደውን ውሳኔ ...

Read More »