በቅርቡ የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) በደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢ በቅርቡ የተከሰተው አዲስ የድርቅ አደጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦች ህይወትን አደጋ ላይ እንደጣለ  ተመድ ገለጸ። በአካባቢው የተከሰተውን ይህንኑ አዲስ የድርቅ አደጋ ተከትሎ በቤት እንስሳት ላይ አሉታዊ ጉዳት መከሰት መጀመሩን ያስታወቀው ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል 10 በመቶ የሚሆኑ የአርብቶ አደሩ እንስሳቶች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት እንደሚፈልጉ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። ይኸው የድርቅ ...

Read More »

የአፍሪካ ሃገራት ከአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት ለመውጣት እያካሄዱ ያለው ዘመቻ ተወገዘ

ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009) የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአፍሪካ ሃገራት ከአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት ለመውጣት እያካሄዱ ያለውን ዘመቻ አወገዘ። የአህጉሪቱ ሃገራት ከአባልነት ለመውጣት እየወሰዱ ያለው እርምጃ ከተጠያቂነት በማምለጥ የተያዘ ስልት ነው ሲሉ የኮሚሽኑ ሃላፊ ዘይድ ራድ አል ሁሴን  ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸውን ቢቢሲ ሃሙስ ዘግቧል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባ በመሰብሰብ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ከህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ጋር በቀብትያ ሁመራ እና አጎራባች ቀበሌዎች  እየተዋጋ ነው

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ እንደገለጹት፣ አባሎቻቸው በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ለወራት ሲደራጁና ሲያደራጁ ከቆዩ በሁዋላ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ ከትናንት ጀምሮ በቃፍታ ሁመራ እና በአከር አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። አደንድን በሚባል አካባቢ ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጦርነት 48 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን የገለጹት አስተባባሪው፣ ከትናንት ...

Read More »

በአባይ ግድብ አካባቢ ያለው የስራ እንቅስቃሴ መዳከሙን ጋዜጠኞች ገለጹ ።

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹ በአባይ ግድብ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ቆሟል የሚል ወሬ በስፋት እየተወራ ነውና ወሬውን አክሽፉ!” ተብለው ለጉብኝት የተላኩት ጋዜጠኞች ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ ባለማየታቸው የሚወራው ትክክል መሆኑን አረጋጋጥው መመለሳቸውን ለኢሳት ገለጹ። ሰሞኑን ወደ አባይ ግድብ የተላከው የ መንግስት ጋዜጠኞች ቡድን ለጉብኝት በቆየበት አንድ ቀን፤ ምንም አይነት ስራ ሲሰራ አለመመልከቱን ገልጿል፡፡ ‹‹ ለአንድም ...

Read More »

በሶማሊያ ክልል በኮሌራ ወረሽኝ 35 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን አካባቢዎች በኮሌራ በሽታ 35 ሰዎች መሞታቸውንና ድርቁን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እየተፈጠረ መሆኑን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አስታወቀ። በድርቁ ምክንያት እንስሳት እየሞቱ ነው። የምግብ እጥረት ተጠቂ የሆኑት የኦጋዴን ነዋሪዎች አፋጣኝ እርዳታ ካላገኙ አደጋው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ለጋሽ የረድኤት ድርጅቶች ለነዋሪዎቹ የሚያደርጉትን ሰብዓዊ እገዛዎች እንዳያሰራጩ ...

Read More »

በኢንተርኔት አፈና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች ።

ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዜጎቻቸው ላይ አፈና በማድረግ የመረጃ እቀባ ከሚያደርጉ አገራት ውስጥ ቻይና፣ ሶሪያ እና ኢራንን በመከተል ኢትዮጵያ በዓለም አራተኛ፣ በአፍሪካ ደግሞ በአንደኝኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ፍሪደም ሃውስ አስታውቋል። በኢንተርኔት ስርጭት ሁዋላ ቀር የሆነችው ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዜጎቿ ላይ በምታደርገው እቀባዎችና አፈናዎች ግን ቀዳሚ ሆናለች ብሎአል። አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በመላው ...

Read More »

የብሪታኒያ ማሰራጫ ጣቢያ (BBC) አማርኛ፣ ኦሮሞኛና ትግሪኛን ጨምሮ በ 11 ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) የብሪታኒያ አለም አቀፍ ማሰረጫ ጣቢያ (BBC) ሶስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ጨምሮ በ11 የተለያዩ ሃገራት ቋንቋዎች በፈረንጆች አዲስ አመት የራዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት እንደሚጀመር ይፋ አደረገ። የማሰራጫ ጣቢያው ከአንድ አመት በፊት አገልግሎቱን ለመጀመር ይረዳው ዘንድ እቅዱን ለብሪታኒያ መንግስት አቅርቦ በጀትን በመጠባበቅ ላይ እንደነበር ይታወሳል። ለቀረበው ጥያቄ ይሁንታ ያገኘው የብሪታኒያ አለም አቀፍ የማሰራጫ ጣቢያ በጥቂት ወራት ውስጥ በኦሮምኛ፣ ...

Read More »

በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በመንግስት መካከል ሊካሄድ የታቀደ ስብሰባ መሰረዙ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በመንግስት መካከል ባሉ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ረቡዕ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ የነበረ ስብሰባ ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙ ተገለጸ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቋቋመው የዳያስፖራ ማህበር ጽ/ቤት ከ1ሺ በላይ ሰዎች ይታደሙበታል ተብሎ የተጠበቀው የውይይት መድረክ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሊካሄድ አለመቻሉንና ስብሰባው ለሌላ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ተቋማት አስታውቋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ...

Read More »

ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) በቅርቡ ተግባራዊ የተደርገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ገለጹ። የአዋጁ መውጣት በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ስጋትን እንዳሳደረ የሚናገሩት እነዚሁ አካላት በተለይ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሃገራት ወደ ሃገር ቤት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ መቀነስ ማስመዝገቡን አስረድተዋል። በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲካሄድ የቆየው ...

Read More »

አልሸባብ ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቲጌሎ ከተማ ማክሰኞ ተቆጣጠረ

ኢሳት (ህዳር 7 ፥ 2009) የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቲጌሎ ከተማ ማክሰኞ መቆጣጠሩ ተገለጸ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎችን መልሶ መያዝ የጀመረው ታጣቂ ሃይሉ በባኩል ግዛት የምትገኘውን የቲጌሎ ከተማ ለመቆጣጠር ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥና የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊት መፈጸሙን መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ ትገኛለች የተባለችው የቲጌሎ ከተማ በቅርቡ ...

Read More »