በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።  በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ረቡዕ ዕለት አንድ የጭነት መኪና በተወሰደበት ዕርምጃ መቃጠሉንም የአይን ዕማኞች ገልጸዋል። በተበታተነ መልኩ ሲካሄዱ የነበሩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአንድ ዕዝ በተቀናጀ መንገድ እንዲካሄዱ ስምምነት ላይ መደረሱንም በበረሃ የሚገኙት ታጣቂዎች ከኢሳት ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል።  በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር በየአካባቢው ተደራጅተው በጎበዝ ...

Read More »

አንድ እንግሊዛዊ አብራሪ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከገባ በኋላ የገባበት አለመታወቁ ተነገረ

ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) እድሜ ጠገብ በሆኑ አውሮፕላኖች በሚደረገ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረ አንድ የብሪታኒያ ፓይለት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከገባ በኋላ የገባበት አለመታወቁን የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አስታወቁ። የ72 አመቱ ሞሪስ ኪርክ የአፍሪካ ጉዞን በሚሸፍነው ውድድሩ ከጎረቤት ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እያለ ግንኙነቱ ተቋርጦ ያለበት ሁኔታ አለመታወቁን ዴይሌ ሜይል ጋዜጣ ዘግቧል። የ72 አመቱ ፓይለት በውድድሩ እያለ እንደ ...

Read More »

38 እስረኞች በቂሊንጦ እስር ቤት እሳት በማስነሳት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) በቅርቡ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰን የእሳት አደጋ እንዲነሳ አድርገዋል የተባሉ 38 እስረኞች ክስ ተመሰረተባቸው። ከሳሽ አቃቢ ህግ 38ቱ ተከሳሾች ከጥር ወር 2008 ዓም ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ግንቦት ሰባትና፣ በአልሸባብ የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈጸም በእስር ቤቱ በተለያዩ ወንጀሎች በእርማት ላይ ያሉ እስረኞችን በድብቅ በመመልመል አመጽ ለመፍጠር መረጃን ሲለዋወጡ ነበር ሲል በክሱ አመልክቷል።  ይሁንና ተከሳሾቹ ...

Read More »

ሪክ ማቻር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የተደረገው የመግቢያ ቢዛን ማግኘት ስላልቻሉ ነው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር ከቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የተደረገው የኢትዮጵያ የመግቢያ ቢዛን ማግኘት ስላልቻሉ ነው ሲል የአማጺ ቡድኑ አመራሮች ረቡዕ አስታወቁ። የአማጺ ቡድኑ ሃላፊዎች ሪክ-ማቻር በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል መባሉን በማስተባበል ድርጊቱ ቪዛን ቀድሞ ካለማግኘት ጋር የተፈጠረ ሁኔታ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል። ስማቸውን መግለጽ ...

Read More »

አልሸባብ ከአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጋር ውጊያ ማካሄዱ ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ የተለያዩ ግዛቶች መውጣቱን ተከትሎ አልሸባብ የተሰኘው ታጣቂ ሃይል ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጋር ውጊያ ማካሄዱ ተገለጸ። በታችኛው የሸበሌ ግዛት ተካሄዷል በተባለው በዚሁ አዲስ ግጭት አብዛኞቹ የኬንያ ወታደሮች የሆኑ የሰላም አስከባሪ አባላት ከታጣቂ ሃይሉ ጋር ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አልሸባብ የተሰኘው ታጣቂ ሃይል በኬንያ ወታደሮች ቁጥጥር ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አማራ ክልል ዞኖች እንዳይጓዙ አሳሰበ

ኢሳት (ኅዳር 14 ፥ 2009) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና ራሳቸውን ባደራጁ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ግጭት ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በክልሉ በሚገኙ አምስት ዞኖች እንዳይጓዙ አሳሰበ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ለዜጎቹ ባሰራጨው መረጃ ወደ አገው አዊ፣ ባህር ዳር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደርና በደቡብ ጎንደር ዞን አካባቢዎች የጥንቃቄ ዕርምጃ ...

Read More »

ሪክ ማቻር ከቦሌ አውሮላን ማረፊያ ተይዘው ወደ መጡበት ደቡብ አፍሪካ እንዲመለሱ ተደረገ

ኢሳት (ህዳር 13 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ከደረሱ በኋላ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደ መጡበት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲመለሱ ማድረጋቸው ተገለጸ። የአማጺ ቡድኑ መሪ ሪክ ማቻር ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት የቡድኑ ጽ/ቤት ዋና መቀመጫ ወደ ሚገኝበትና ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ ባለው የደቡብ ሱዳን የፓጋክ ግዛት የመሄድ እቅድ እንደነበራቸው የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ...

Read More »

ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አባልነት ለመመለስ ኢትዮጵያ እንድታግባባ መጠየቋ ተገለጸ

ኢሳት (ህዳር 13 ፥ 2009) ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉት የሞሮኮ ንጉስ በሃገሪቱ የነበራቸው ቆይታ ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አባልነት ለመመለስ እያደረገች ላለው ጥረት የማግባባት ስራን ለማከናወን እንደነበር ተገለጠ። ለዚሁ ዘመቻ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል የድጋፍ ቃል የተገባላቸውን ንጉስ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት የ2.3 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረማቸውን አፍሪካ ቢዝነስ የተሰኘ መጽሄት ዘግቧል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሞሮኮ ከሁለት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አቶ ኢሳያስ ባህሬ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

ኢሳት (ህዳር 13 ፥ 2009) ላለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አቶ ኢሳያስ ባህሬ ከሃላፊነታቸው ተነሱ። የባንኩ ሃላፊ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የተደረገበት ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን፣ ከስራ ስለመሰናበታቸው የሚገልጽ የጽሁፍ ደብዳቤ ከፋይናንስ መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካዔል ተፈርሞ የደረሳቸው መሆኑን በሃገር ቤት ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከተያዘው ሳምንት ጀምሮ ለስምንት አመታት ያህል ጊዜ ካገለገሉበት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተነሱት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት በግማሽ ሊቀንስ ይችላል ተባለ

ኢሳት (ህዳር 13 ፥ 2009) የአለም ባንክ በተያዘው የፈረንጆች አመት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት በመንግስት ከተቀመጠው በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል ይፋ አደረገ። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስቶ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሃገሪቱ ዕድገት በ12 በመቶ ያድጋል ሲሉ ለሃገር ውስጥ በመገናኛ ብዙሃን ብዙሃን መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንና የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሩዋንዳና ታንዛኒያ በአማካኝ የስድስት በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ ሲል ...

Read More »