ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ ያገረሸውን የእርስበርስ ጦርነት እና ድርቅ ሸሽተው ከሶማሊያ የተሰደዱ ተፈናቃዮች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አሳዋኝ ወደምትገኘው ዶሎአዶ ከተማ እየፈለሱ መሆኑን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። ግጭቱን ሸሽተው ለመጡ ተፈናቃዮች በዶሎ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ሕጻናት እና አዛውንት ለ ከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ተገልጿል።
Read More »በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው ፥ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ይቅርታ ጠየቀ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2008) ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር አዛዦች አንዱ በሆነው በሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የለውጥ ደጋፊዎች ሃዘንና ቁጭታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በሌላም በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ አሁንም መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ዝግጅት ክፍሉ የሟቹ ቤተሰቦቹንና ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠየቀ። የቀድሞ የደርግ መንግስት ለመጣል በተደረገው ትግል በብዓዴን/ኢህአዴግ ትግል ...
Read More »ቱርክ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ ትችላለች ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) ቱርክ ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመደራደር የተገባላት ቃል ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ እንደምትችል አሳስባለች። ባለፈው አመት የሶሪያ ስደተኞች ቱርክን በመጠቀም ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ሲገቡ የነበረ ሲሆን፣ ህብረቱ ቱርክ ሰደተኞቹን በሃገሩ እንድታቆይ የጥቅማ-ጥቅም ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል። ቱርክ የሃገሩ ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ አውሮፓ እንዲገቡና ሃገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ...
Read More »ቻይና በጅቡቲ ወታደራዊ ጣቢያን ለማቋቋም መወሰኗ በህንድ ላይ ስጋት አሳድሯል ተባለ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) ቻይና በጎረቤት ጅቡቲ የባህር ሃይል ወታደራዊ ጣቢያን ለማቋቋም መወሰኗ በህንድ በኩል የደህንነት ስጋት ማሳደሩ ተገለጠ። የቻይና ወታደራዊ ባለስልጣናት በበኩላቸው ሃገሪቱ በጅቡቲ እየገነባች ያለው ይኸው ወታደራዊ የማዘዣ ጣቢያ ለሰላም ማስከበርና በሰብዓዊ ዕርዳታ ስራዎች እገዛን የሚያደርግ መዕከል እንደሆነ አስታውቃለች። በተያዘው ሳምንት በጅቡቲ ጉብኝትን ያደረጉ ከፍተኛ የቻይና ወታደራዊ ባለስልጣናት ሃገራቸው ቁልፍ ይዞታ ላይ ትገኛለች በምትባለው ጅቡቲ ወታደራዊ ይዞታን ...
Read More »በሶማሊያ የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ሃይል በአልሸባብ የተያዙ ቦታዎችን ለማስለቀቅ 40ሺ ወታደሮች ያስፈልጉኛል አለ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን የተያዙ ቦታዎችን ነጻ ለማውጣት ተጨማሪ ከ40ሺ በላይ ወታደሮች እንደሚያስፈልጉት ገለጸ። የሰላም አስከባሪ ልዑክ በአሁኑ ሰዓት ወደ 21ሺ አካባቢ የሰላም አስከባሪ አባላት ቢኖሩትም ሁሉንም የአልሸባብ ይዞታዎችን ለመቆጣጠርና መልሶ ለመያዝ አለመቻሉን የልዑኩ ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ዘ-ኢስት አፍሪካን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የልዑኩ ቃል አቀባይ የሆኑት ...
Read More »በጋምቤላ የአየር ክልል ጥሰዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የነበሩ ፓይለቶች ፈቃድ ተሰጥቷቸው እንደነበር ይፋ አደረጉ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) በጋምቤላ ክልል በህገወጥ መንገድ የሃገሪቱን የአየር ክልል ጥሳችሁ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ፓይለቶች የመንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው እንደነበር ይፋ አደረጉ። በውድድር ላይ የነበሩት እነዚሁ ከ40 የሚበልጡ ፓይለቶች የኢትዮጵያ አቪየሽን ባለስልጣን ሊያደርጉ ለነበረው የአውሮፕላን በረራ ፈቃድ ሰጥቷቸው እንደነበር መግለጻቸውን ዴይሊ ሜይል የተሰኘ የብሪታኒያ ጋዜጣ ዘግቧል። ይሁንና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለፓይለቶቹ ቡድን ፈቃድን ከሰጠ በኋላ ...
Read More »አቶ ጌታቸው አምባዬ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ መሆናቸው ተገለጸ
ኢሳት (ኅዳር 16 ፥ 2009) በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባወቀሩት ካቢኔ ውስጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው አምባዬ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ አለመሆናቸው ታወቀ። የቅርብ ምንጮች እንደገለጹት ባለስልጣኑ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ ይገኛሉ። ሹመቱ የተሰጣቸው በውጭ ሃገር በህክምና ላይ መሆናቸው እየታወቀ መሆኑን መረዳት ተችሏል። በቅርቡ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በነበሩት ...
Read More »በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮችና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና ሌሎችም ቦታዎች በአርበኞች ግንቦት7 ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የአርበኞች ግንቦት 7 አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መከበቡብ እንዳወቀ ራሱን ሰውቷል። ቀደም ብሎ በኢህአዴግ መከላከያ ውስጥ ሲያገለግል ቆይቶ፣ በስራዊቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነትና በህዝቡ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ መቋቋም ተስኖት፣ አርበኞች ግንቦት 7ትን የተቀላቀለው ...
Read More »ወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) በአዳማ ተቃውሞ ገጠመው
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከሰኞ እስከ ዓርብ ኢህአዴግና የከተማው መስተዳድር በአዳማ ከተማ ከኢህአዴግ አባላትና ደጋፊ የከተማው ነዋሪዎች ጋር ስለ ወታደራዊ እዙ ተግባርና ኃላፊነት፣ ስለተደረገው ሹም ሽር እንዲሁም የክልሉንና የከተማዋን ልማትና ጸጥታ ሁኔታ በሚመለከት በተደረገው ስብሰባ ላይ ያልተጠበቀ ተቃውሞ ተነስቷል። በዚህ መድረክ የተሳተፉት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ቢሆኑም የከተማዋ የኮማንድ ፖስት ኃላፊ ማንነት እንደተገለጸ ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉት ፍተሻዎች የህብረተሰቡን ኑሮ እያወኩ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በሚደረጉ ፍተሻዎች ነዋሪው እየታወከ መሆኑን በባህርዳር የጣናና ሽምብጥ ክፍለከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ተናገሩ፡፡ በውድቅት ሌሊት የመንግስት ወታደሮችና ታጣቂዎች በወደ ግለሰቦች ቤት በመግባት ‹‹ፍተሻ እናካሂዳለን!!›› በማለት ከሌሊት እስከ ንጋት ድረስ ሲያንገላቷቸው ያድራሉ፡፡በተለይ በጣና ክፍለ ከተማ ቀጠጢና በተባለ መንደር የሚገኙ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ወደ ሆቴል ...
Read More »